Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

Alamat saluran: @ethiopian_digital_library
Kategori: Pekerjaan
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 65.82K
Deskripsi dari saluran

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru 18

2024-03-02 10:38:34 በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተከስቷል በተባለ የኮሌራ በሽታ ከ400 የማያንሱ ተማሪዎች መያዛቸውን በተቋሙ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ከተከሰተ አንድ ሳምንት ሆኖታል ስለተባለው በሽታም ሆነ ስለደረሰ ጉዳት ከዩኒቨርሲቲው እንዲሁም ከክልሉ ጤና ቢሮ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱን ሬዲዮ ጣቢያው ገልጿል። 

ይሁን እንጂ አስተያየት የሰጡ ተማሪዎች በበሽታው ተይዘው ህክምና ሲደረግላቸው ከነበሩት መካከል አንዳንዶቹ እያገገሙ ይገኛሉ ብለዋል።

በዩኒቨርሲቲው ተከሰተ ስለተባለው ወረርሽኝ ለተማሪዎች በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። በሽታው "በውኃ ብክለት" ወይም "የግል ንፅህና ባለመጠበቅ" የመጣ ነው የሚሉ አስተያየቶች ተሰምተዋል።

በዚህም ምክንያት ተማሪዎች ወደ መመገቢያ አዳራሾች ሲገቡ ለጥንቃቄ እንዲታጠቡ ሲደረግ ነበር ተብሏል።

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የፊታችን እሑድ እንደሚያስመርቅ ይጠበቃል። #ዶይቼ_ቬለ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.3K views07:38
Buka / Bagaimana
2024-02-29 15:05:14 For English Tips, Quizzes,Tutorials and Materials!
@ethiopian_english_academy
13.4K views12:05
Buka / Bagaimana
2024-02-29 14:52:21 በሕይወታችን መፍታት ያለብን ሁኔታ እንዳለ ከተሰማን በቅድሚ የችግሩን ምንነት መለየት አለብን፡፡

ችግራችን ከአራቱ አያልፍም ፡፡


1. ዓላማን ያለማወቅ ችግር (ራእይን መለየት፣ ለራእዩ የሚመጥን የራስ በራስ ምልከታ ማዳበር፣ ወደራእዩ መንቀሳቀስ)

2. የክህሎት ችግር (ስልጠናን መውሰድ፣ ማንበብ፣ እውቀትን ተግባራዊ ማድረግ)

3. የዲሲፕሊን ችግር (አመለካከትን በመቀየር፣ ቀስ በቀስ በመጀመር፣ ሰዎች በሃላፊነት እንዲጠይቁን ማድረግ)

4. የባህሪይ ችግር (ያለንን የሕይወት ፍልስፍና በማስተካከል፣ ጓደኛን በመቀየር፣ የምንውልበትን አካባቢ መቀየር)

Credit : Dr. Eyob Mamo

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
12.8K viewsedited  11:52
Buka / Bagaimana
2024-02-29 14:40:33 ደግለራሱና ክፉለራሱ

በአንድ ወቅት ደግለራሱና ክፉለራሱ አብረው ጉዞ ጀመሩ (የስማቸውም ትርጉም ‘መልካም ሰው ይሸለማል’ እና ‘ክፉ ሰው ይቀልጣል’ ማለት ነው፡፡)

እኩለ ቀን ሲሆንም ከአንድ ዛፍ ስር ተቀምጠው የደግለራሱን ምግብ በሉ፡፡ በሚቀጥለውም ቀን ይህንኑ በማድረግ አሁንም የደግለራሱን ምግብ ሲበሉ በሶስተኛውም ቀን ይኸው ተደገመ፡፡ በመጨረሻም የደግለራሱ ምግብ ስላለቀ ደግለራሱ ክፉለራሱን ምግብ እንዲሰጠው ሲጠይቀው ከለከለው፡፡
ክፉለራሱም “አንድ አይንህን አውጣና ምግብ እሰጥሃለው፡፡” አለው፡፡

ከዚያም ደግለራሱ አንድ አይኑን አውጥቶ ምግብ አገኘ፡፡ ከዚያም ጉዟቸውን ቀጥለው በሚቀጥለውም ቀን ክፉለራሱ ምግም አልሰጥም ብሎ ከለከለ፡፡ ደግለራሱ የቀረውን አንድ ዓይኑን አውጥቶ ምግብ ቢያገኝም አሁን ዓይነ ስውር ሆነ፡፡
ክፉለራሱም ጉዞውን ሲቀጥል ደግለራሱ ሌሊቱን ዛፍ ላይ ሊያሳልፍ ወጣ፡፡ በዚህ ጊዜ ሰይጣኖቹ ከዛፉ ስር ይጫወቱ ስለነበረ ስለዛፉ ቅጠሎች የተለያዩ ክፍሎች ሲያወሩ ሰማ፡፡

ከሰይጣኖቹ አንዱ “ይህ የሞት መድኃኒት ነው፡፡” ሲል ሌላኛው ደግሞ “ያኛው የዛፍ ክፍል ደግሞ ለሆድ ጥሩ ነው፡፡” አለ፡፡ ሶስተኛውም ቀበል አድርጎ “ያኛው ደግሞ ለአይነ ስውርነት መድኃኒት ነው፡፡” አለ፡፡ በማግስቱ ጠዋት ሠይጣኖቹ ሲሄዱ አይነ ስውሩ ደግለራሱ ሰይጣኖቹ የጠቀሷቸውን ቅጠሎች ሁሉ መሞከር ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ አይኑ በራ፡፡ ከዚያም የንጉሱ ልጅ አይነ ስውር መሆኗን ሰምቶ ካዳናት በኋላ አገባት፡፡ ደግለራሱ የገበያ ዳኛም ሆነ፡፡

ታዲያ አንድ ቀን ክፉለራሱ ወደ ገበያ መጥቶ ተገናኙ፡፡ “እንዴት ልትድን ቻልክ?” ብሎ ሲጠይቀው ደግለራሱም ታሪኩን በሙሉ አጫወተው፡፡ የገበያውም ዳኛ እንዴት እንደሆነ ነገረው፡፡ በዚህ ጊዜ ክፉለራሱ ሃብታም ሊያደርገው የሚችል ቅጠል የሚያገኝ መስሎት ወደ ዛፉ ሄደ፡፡
በዚያን ጊዜ ሰይጣኖቹ እንደቀድሞው ጊዜ ስለ መድኃኒት እየተወያዩ ሳለ በድንገት ክፉለራሱ ሃብታም የሚያደርገው ቅጠል የትኛው እንደሆነ እንዲያሳዩት ሲጠይቃቸው ከዛፉ ላይ ጎትተው አውርደው ደብድበው ገደሉት፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
12.9K viewsedited  11:40
Buka / Bagaimana
2024-02-26 16:52:42 ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ የተሰጠውን የመውጫ ፈተና የወሰዱ የግል እና የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡

በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከቅዳሜ የካቲት 16/2016 ዓ.ም ጀምሮ ውጤታቸውን ሲመለከቱ ቆይተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን የወሰዱ የግል እና የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ ጀምሮ መመልከት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ከደቂቃዎች በፊት አሳውቋል፡፡

ውጤት ለማየት ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ

https://result.ethernet.edu.et

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
15.2K views13:52
Buka / Bagaimana
2024-02-26 11:16:34 ሁለቱ ፍቅረኛሞች

በባህር ዳር አካባቢ የሚነገር አንድ ታሪክ አለ፡፡ በአንድ ወቅት ሁለት ፍቅረኛሞች ጣና ሃይቅ ላይ ወደሚገኙት ገዳማት ይሄዳሉ፡፡ የአንዱ ገዳም ስም ደጋ እስጢፋኖስ ይባላል፡፡ ወደዚህም ገዳም በታንኳ ሄዱ፡፡ ከገዳሙ እንደደረሱም ታንኳቸውን ሃይቁ ዳር ትተው በገዳሙ ውስጥ ጥሩ የፍቅር ጊዜ ማሳለፍ ጀመሩ፡፡

በዚህን ጊዜ ታዲያ ታንኳቸው በማዕበል በመወሰዷ እነርሱም አብረው ጠፍተዋል በሚል ሰዎች ይፈልጓቸው ጀመር፡፡ ስለፍቅረኛሞቹ መጥፋት በከተማው ዙሪያ ብዙ ነገር ተባለ፡፡

አንድ የከተማው ሰው ስለእነርሱ ብዙ ያውቅ ነበርና ይፈልጋቸው ጀመር፡፡ ወደ ተባለውም ገዳም በመሄድ ሊያገኛቸው ሞከረ፡፡ ልብሳቸውንም ከሩቅ አይቶ ደነገጠ፡፡

እየሮጠም ወደእነርሱ ሲደርስ አብረው ተኝተው ግን ሞተው አገኛቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ገዳሙ አሁን የፍቅር ጠርዝ እየተባለ ይጠራል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.8K viewsedited  08:16
Buka / Bagaimana
2024-02-26 10:53:55
ኢ/ር ቢጃይ ናይከር እረዥም እድሜና ጤና ይስጥህ እንደአንተ አይነት ያሉ ሰዎችን ያብዛልን! የኢትዮጵያ ሀብታሞች ከሱ ብዙ ነገር መማር አለባቸው !

Bejai Nerash Naiker (Vijay)

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.5K viewsedited  07:53
Buka / Bagaimana
2024-02-25 16:34:59 ተረት ተረት - አህያ የበሉ መንገደኞች

ከብዙ አመታት በፊት በድሮ ጊዜ መንገደኞች በጉዞ ላይ ብዙ ቀናትን ያሳልፉ ነበር፡፡ እንዳሁኑ ዘመናዊ መጓጓዣ ስላልነበረ ለሶስት፣ ለአራት አንዳንዴም ለአንድና ለሁለት ሳምንታት ያህል ከቦታ ወደቦታ እየተዘዋወሩ በጉዞ ላይ ያሳልፉ ነበር፡፡ ይህም ጉዞ በመንገዳቸው ላይ እንደሚያጋጥማቸው ሁኔታ ጊዜው ሊያጥር ወይም ሊረዝም ይችላል፡፡

ታዲያ በአንድ ወቅት አራት መንገደኞች በበረሃ እያቋረጡ ሳለ እጅግ በጣም ከመሞቁም በላይ በረሃብ ይቸገሩ ጀመር፡፡ በዚህም ምክንያት ካቀዱት ጊዜ በላይ በመንገድ ላይ ማሳለፍ ስለነበረባቸው ስንቃቸው አልቆባቸው የሚበሉት ነገር አጡ፡፡

በጉዟቸውም ላይ እየተዳከሙ ሄዱ፡፡

በበረሃውም ውስጥ የሚበሉት አጥተውና ሙሉ ለሙሉ ተዳክመው ቁጭ አሉ፡፡ በዚያች ቅፅበት ታዲያ ከየት እንደመጣ ያልታወቀ አንድ ግዙፍ አህያ እያናፋና በትእቢት እየሮጠ ወደ እነርሱ መጣ፡፡ በዚያ በረሃ ውስጥ አህያው ምን በልቶ እንደዚያ እንደጠገበ የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነበር፡፡ ሆኖም አህያው በጣም የጠገበ በመሆኑ እያናፋ ላይና ታች መሮጡን ቀጠለ፡፡

ታዲያ በደቡብ የሚገኙት አብዛኛዎቹ ህዝቦች ክርስቲያን ስለሆኑ አህያን መብላት ይቅርና ለመብላት መፈለግም ጭምር በፍጹም የማይታሰብ ነበር፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ ሸሆናቸው ድፍን የሆኑ እንስሳትን መብላት ይከለክል ነበርና ነው፡፡ ስለዚህ ስለሌሎች ጉዳዮች እየተወያዩ ቁጭ አሉ፡፡
ነገር ግን አህያው ማናፋቱን በመቀጠል የተለያዩ ድምጾችን እያሰማ ከፊታቸው መመላለሱን ቀጠለ፡፡ በዚህ ጊዜ አንደኛው ተጓዥ ቀና ብሎ አይቶ “ወንድሞች ሆይ፣ እዚህ በረሃ ውስጥ በረሃብ ከምናልቅ አህያውን በልተን ቢያንስ ወደ መንደራችን ብንመለስስ?” ብሎ ሃሳብ አቀረበ፡፡

ሌሎቹ ሶስቱ ተጓዦች ግን “በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ! እንዴት እንደዚህ ያለውን ነገር ልታስበው ቻልክ?” አሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ሰውየው በድምፅ ብልጫ መሸነፉን አይቶ በዝምታ ቁጭ አለ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን ሁለተኛው ተጓዥ ቀና ብሎ ሲመለከት የአህያውን ጮማና ጡንቻው ተፈልቅቆ ላይ ታች ሲሮጥ አይቶት “እኔ እስማማለሁ፡፡ ይህንን አህያ ካልበላን ሁላችንም እንሞታለን፡፡” አለ፡፡

ሌሎቹ ሁለቱ ግን በእምቢታቸው ፀንተው ቀሩ፡፡

ከዚያ አህያውን ለመብላት የተስማሙት ሁለቱ ተጓዦች አህያውን ይዘው ካረዱት በኋላ ጥጥ የመሰለ ጥሩ ጮማ ስጋና የተለያዩ ነገሮች እንዳሉት አዩ፡፡ አህያውንም ካረዱት በኋላ ትንሽ ጥሬ ስጋ በልተውለት ሌላውን የተለያዩ ምግቦች አዘጋጁበት፤ የተወሰነውን ጥብስ፣ ሌላውን ደግሞ ቅቅልና ሌሎች የተለያዩ የምግብ አይነቶችን አዘጋጁ፡፡ ምግቡንም በሚያዘጋጁበት ወቅት የስጋው ቅባት እየተንጣጣ የተለያዩ ድምጾችን በማሰማት ቹ፣ቹ፣ቹ፣ቹ,,,,,,,,ቹ፣ቹ፣ቹ,,,,, ሲል ሶስተኛው ተጓዥ ምራቁን ማዝረብረብ ጀመረ፡፡

በመጨረሻም ከዚህ በላይ የጮማውን አጓጉዊነት ታግሶ መቆየት ስላልቻለ አራተኛውን ተጓዥ “ና እባክህ! እኛም መብላት አለብን፡፡ ካለበለዚያ እዚህ በረሃብ እንሞታለን፡፡” አለው፡፡

አራተኛው ሰው ግን “እኔ የአህያ ስጋ በፍፁም አልበላም፡፡ ክርስቲያን በመሆኔ በክርስቲያንነቴ እሞታለሁ፡፡ አንገቴ ላይ ያሰርኩትም ማተብ የክርስቲያንነቴ መገለጫ በመሆኑ ለማተቤ ለመሞት ዝግጁ ነኝ፡፡” ብሎ አሻፈረኝ አለ፡፡

ሶስቱ ግን “አይ አንተ ሞኝ ሰው!” ብለው ተሳለቁበት፡፡ ይህንንም ብለው የአህያውን ስጋ በልተው ከጨረሱ በኋላ ጉልበታቸው ስለበረታ መንገዳቸውን ሊቀጥሉ ሲሉ አራተኛው ሰው እጅግ በጣም ስለተዳከመ ሰውየውን እየደገፉት በመጨረሻ ከመንደራቸው ደረሱ፡፡

ታዲያ መንደራቸው ከመግባታቸው በፊት አንዱ ሰው “እስኪ አንድ ጊዜ ታገሱ፡፡ አሁን ከመንደራችን ስንገባ አራተኛው ሰው እኛ የአህያ ስጋ እንደበላን ለመንደሩ ሰው ስለሚነግር ሰው ሁሉ ያገለናልና ምን ብናደርግ ይሻላል?” አለ፡፡

ሶስቱ ሰዎች ትንሽ ካሰቡ በኋላ አንደኛው “አንድ ሃሳብ አለኝ፡፡ እኔ አራተኛውን ሰው ‘የአህያ ስጋ በላ’ ብዬ ሳስወራበት እናንተ ሁለታችሁ ምስክር ትሆናላችሁ፡፡” አላቸው፡፡

እናም በዚህ ተስማምተው ወደ መንደሩ ዘለቁ፡፡

የመንደሩም ሰዎች ተጓዦቹ በሰላም ወደመንደሪቱ በመመለሳቸው ተደስተው ቡና ካፈሉላቸው በኋላ “በሰላም መመለሳችሁ መልካም ነው፡፡ በጣም ስለቆያችሁ የሞታችሁ መስሎን ነበር፡፡” አሉ፡፡

ትልቅ ድግስም ከተደረገ በኋላ ሁሉም ወደየቤታቸው ሄዱ፡፡ በሚቀጥለውም ቀን አንደኛው በስራ ላይ ወደነበሩት ገበሬዎች በመሄድ “አንድ ምስጢር ልንገራችሁ፡፡ ከሄድንበት አገር ወደዚህ እየተመለስን ሳለ እገሌ፣ የእገሌ ልጅ፣ የአህያ ስጋ በላ፡፡” አላቸው፡፡

እነርሱም “ይህ የማይሆን ነገር ነው! እንዴት እንደዚህ ያደርጋል? ይህ በጣም መጥፎ ነገር ነው፡፡” አሉ፡፡

ልክ በዚህ ጊዜ ሌሎቹ ሁለት መንገደኞች መጥተው “አዎን፣ ይህ አሳፋሪ ነው፡፡ እኛ በአይናችን አይተነዋል፡፡ የአህያ ስጋም በልቷል፡፡” ብለው በሃሰት መሰከሩበት፡፡

በዚያችው ቅፅበት ደግሞ አራተኛው ሰው ደርሶ “እንዴት እንደዚህ ብላችሁ ትናገራችሁ? እኔ የእገሌ ልጅ፣ የእገሌ ልጅ፣ የእገሌ ልጅ የአህያ ስጋ በፍፁም ልበላ አልችልም፡፡ ይህንን እናንተም ታውቁታላችሁ፡፡ እንዲያውም የአህያውን ስጋ የበላችሁት እናንተ ናችሁ፡፡” ብሎ ተናገረ፡፡

በዚህ ጊዜ የተሰበሰቡት ሰዎች “አይሆንም! እነዚህ ሶስት ሰዎች ሊዋሹ አይችሉም፡፡ እነርሱ የእገሌ ልጅ፤ የልጅ ልጅ፤ የእገሌ የልጅ፣ልጅ፣ ልጅ፤የእገሌ የልጅ፣ ልጅ፣ልጅ፣ልጅ ስለሆኑ ሃይማኖታቸውን ትተው የአህያ ስጋ አይበሉም፡፡” አሉ፡፡

በዚህ አይነት አራተኛው ሰው ከማህበረሰቡ ተገለለ፡፡ አንድ ሰው ከማህበረሰቡ ሲገለል ሴት ልጆቹ ባል አያገኙም፡፡ ወንድ ልጆቹም ሚስት አያገኙም፡፡ ስለዚህ ሰውየውና ቤተሰቡ ለዘለአለሙ ከማህበረሰቡ ተገለሉ፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.1K viewsedited  13:34
Buka / Bagaimana
2024-02-25 09:08:07
የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የከተማ አቀፍ ፈተና

ከላይ እንደተገለጸው ለ2016 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የከተማ አቀፍ ፈተና ጥያቄዎችን በተመለከተ ፈተናው የሚዘጋጀው በሁለቱም የክፍል ደረጃ ብቻ ሲሆን ይህም ማለት ከ6ኛ እና ከ8ኛ ክፍል ብቻ የሚወጣ መሆኑን ተገንዝባችሁ ትምህርት ቤቶች በዚህ ልክ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡

ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ዋናው ፈተናችሁ የሚወጣው ከ8ኛ ክፍል ብቻ ነው የ7ኛ ክፍልን አይጨምርም። የ6ተኛ ክፍልም በተመሳሳይ የ5ኛ ክፍልን አያካትትም::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.1K viewsedited  06:08
Buka / Bagaimana
2024-02-24 10:54:24 ይሄን እያየ መጪው ትውልድ ለትምህርት ዋጋ ይሰጣል ማለት የማይታሰብ ነው

ሰሞኑን ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ወሎ ደሴ ጎራ ብዬ ነበር ፤ ድሮ አስረኛ ክፍል የወደቀው ጓደኛዬን አገኘሁትና አንድ ሁለት እንበል ብሎ Golden Gate የሚባል ቅንጡ ሆቴል ውስጥ ይዞኝ ገባ ፤ ኑሮ እንደት ነው ስለው እኔ ጋር እጅግ በጣም አሪፍ ነው አለኝ አንተስ ጋር ሲለኝ ምንም አይልም ሶስተኛ ድግሪዬን (ፒኤችዲዬን) እየተማርኩ ነው ስለው ቤት ሰራህ? መኪና ገዛህ ወይ ሲለኝ ኸረ ቤትም አልሰራሁም፣መኪናም አልገዛሁም፣የሚከፈለኝ ወርሃዊ ደመወዝ እራሱ ወር እስከ ወር አድርሶኝ አያውቅም ስለው እጅግ በጣም አዝኖ እናንተ (ሌክቸረሮች ማለቱ ነው) አንደኛ ድግሪ፣ሁለተኛ ድግሪና ሶስተኛ ድግሪ እያላችሁ ትቆጥራላችሁ እኛ (ነጋዴዎች) ደግሞ አንድ ቤት፣ሁለት ቤት፣ሶስት ቤት፣አንድ ቦታ፣ሁለት ቦታ፣አንድ መኪና፣ሁለት መኪና፣ሶስት መኪና ወዘተ እያልን እንቆጥራለን አለኝ ፤ ለማንኛውም እኔ ሶስት መኪናና ሶስት መኖሪያ ቤት አለኝ ሲል አጫወተኝ ፤ የበላነውንና የጠጣነውን ወጭ ከፍሎ አይዞህ ነገ ሌላ ቀን ብሎ አፅናንቶኝ Golden Bus ትኬት በ 1030 ብር ቆርጦ፤ከደሴ ወደ አዲስ አበባ አሳፈረኝ።

ድሮ የተማረ (መንግሥት ሰራተኛ) ከሚከፈለው ወርሃዊ ደመወዝ አጠራቅሞ ቦታ ገዝቶ ቤት ሰርቶ ጥሩ ኑሮ ይኖር ነበር፤የአሁኑ መንግሥት ሰራተኛ ግን አይደለም ከደመወዙ አጠራቅሞ ቦታ ገዝቶ ቤት ሊሰራ ይቅርና የሚከፈለው ወርሃዊ ደመወዝ ወር እስከ ወር በአግባቡ አያደርሰውም።

ይሄን እያየ መጪው ትውልድ ለትምህርት ዋጋ ይሰጣል ማለት የማይታሰብ ነው።
ሙሳ ሙሃባ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.6K viewsedited  07:54
Buka / Bagaimana