Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

Alamat saluran: @ethiopian_digital_library
Kategori: Pekerjaan
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 65.82K
Deskripsi dari saluran

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru 20

2024-02-17 17:28:57
ለጤግሮስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተፃፈውን የትብብር ደብዳቤ ስለመሻር ይመለከታል

ጤግሮስ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤት መምህራንና አስተዳደር ሠራተኞችን ልዩ የመኪና እና የጤና ሽፋን ስጦታ ለመስጠትና ተጠቃሚ ለማድረግ በቁጥር ጤ117/0099/16 በቀን 29/04/2016ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ በጠየቁን መሠረት በቁጥር አ11/9641/አ28-40/35 በቀን 03/05/2016ዓ.ም የትብብር እና የድጋፍ ደብዳቤ ለትምህርት ቤቶች እንዲፃፍላቸው መፃፋችን ይታወቃል፡፡

ነገር ግን የተፃፈውን የትብብር ደብዳቤ እንደ እውቅና እና ዋስትና እንደሰጠናቸው እንዲሁም ደብዳቤውን ባልተገባ መንገድ እና ትርጉም እየተጠቀሙበት ስለሆነ ይህ ደብዳቤ በዚህ የተሻረ መሆኑን እየገለፅን ማህበሩ በተቋም ስም መነገዱን ትቶ እንደ ማንኛውም ማህበር ግለሰቦችን ከትምህርት ተቋም ውጭ አሳምኖ መሥራት የሚችል መሆኑ ታውቆ በትምህርት ተቋም ውስጥና በተቋማት ስም ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ የማይችል መሆኑን እናሳስባለን፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
19.5K viewsedited  14:28
Buka / Bagaimana
2024-02-17 15:01:35 የመምህርነት ሙያን የሚቀላቀለው ሰው በእጅጉ እየቀነሰ ነው !

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ፕርሃኑ ነጋ የመስሪያ ቤታቸውን የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባሳለፍነው ሀሙስ የካቲት 7/2016 አቅርበው ነበር ። በዚህ ወቅት ከተናገሩት መካከል የሚከተሉት 2 ነጥቦች ተጠቃሽ ናቸው።

የመምህርነት ሙያን የሚቀላቀለው ሰው በእጅጉ እየቀነሰ መምጣቱን የተናገሩት ፕሮፌሰሩ የመምህራን ጉዳይ የጥራት ብቻ ሳይሆን አሁን በቅርብ ባደረግነው ጥናት ያየነው በቅርብ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የመምህራን እጥረት ይገጥመናል ብለዋል። ለዚህ እንደ ምክንያት የተነሳው የደመወዝ ክፍያው ከሙያው ጋር የሚመጥን ባለመሆኑ ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

በመውጫ ፈተና ከ25% በታች ተማሪዎችን ማሳለፍ የቻሉ የግል ዩኒቨርስቲዎች ፍቃዳቸው እንደማይታደስ ሚንስትሩ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
19.7K viewsedited  12:01
Buka / Bagaimana
2024-02-05 13:52:33 የወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ቅሬታ

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ የ2016 ተመራቂ ተማሪዎች የመመረቂያ ጊዜያችን ያለ አግባብ ተራዝሞብናል በማለት ቅሬታቸውን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡

ተመራቂ ተማሪዎቹም ጥያቄያችን መልስ ያግኝ በሚል ትምህርት ማቆም አድማ እንዳደርጉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡ ተማሪዎቹ በ2016 መመረቅ ሲግባን 2017 መጨረሻ ወር ላይ ትመረቃላችሁ እየተባልን ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

በሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ያሉ ተመራቂ ተማሪዎች በዚህ ዓመት ቢመረቁም እኛ ግን እንድ አመት እንዲጨመርብን ተደርገናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ይህ ጉዳይ እኛ ተማሪዎች ላይ ብቻ ሳይሆን ወላጆቻችን ላይም ጫና የሚያሳድር በምሆኑ ከወዲሁ ችግሩ ይቀረፍልን ብለዋል፡፡

ለመመረቅም 3 ሴሚስተር እንደሚቀራቸው ነው ተማሪዎቹ ያነሱት፡፡ ኢትዮ ኤፍ ኤም ጉዳዩን ለማጣራት የየኒቨርስቲው አመራሮችን በተደጋጋሚ ቢያነጋግርም ፍቃደኛ አልሆኑም። #ኢትዮ ኤፍ ኤም
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.6K viewsedited  10:52
Buka / Bagaimana
2024-02-05 10:44:47
ለ2016 ዓ/ም አጋማሽ ዓመት መውጫ ፈተና ለመውሰድ ለተመዘገባችሁ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ

በ2016 ዓ/ም አጋማሽ ዓመት (ከየካቲት 6 - 9 ቀን 2016 ዓ/ም) የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ለመውሰድ የተመዘገባችሁ የባሕር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች፤

1ኛ. የመደበኛ፤ የማታና የክረምት ተማሪዎች ከምትማሩበት አካዳሚክ ክፍል ሬጅስትራር እንዲሁም የርቀት ተማሪዎች ደግሞ ከርቀት ማዕከላት User Name & Password ከጥር 27 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እንድትወስዱ፤

2ኛ. ሁሉም በድጋሚ የመውጫ ፈተና የምትፈተኑ ተማሪዎች እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የምትፈተኑ የማታ፤ የክረምት እና የርቀት ተማሪዎች User Name & Password ለመውሰድ ስትመጡ ለመውጫ ፈተና አገልግሎት ክፍያ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ ኮፒ ይዛችሁ መምጣትና ማስገባት እንዳለባቸሁ እናሳስባለን፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
12.6K viewsedited  07:44
Buka / Bagaimana
2024-02-03 11:47:50
The Top 10 Largest Libraries in the World

1.British Library, United Kingdom, London
2.Library of Congress, United States, Washington, D.C.
3.New York Public Library, United States
4.Russian State Library, Moscow
5.National Library of Russia, Saint Petersburg
6.National Diet Library, Tokyo, Japan
7.Toronto Public Library, Canada, Ontario
8.National Library of China, Beijing
9.Library and Archives Canada, Ottawa, Canada
10.Bibliothèque nationale de France, Paris, France

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
16.6K viewsedited  08:47
Buka / Bagaimana
2024-02-03 10:13:02
ኢትዮጵያን የወከለው የብላክ ላዮን የሰርከስ ቡድን በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ሰፈረ

በጣሊያን በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሰርከስ ኪነ ጥበብ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክሎ የተሳተፈው የብላክ ላዮን ሰርከስ ቡድን የዓለምን ሪከርድ በመስበር በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ መስፈሩ ተገልጿል፡፡

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ በሰርከስ ኪነ ጥበብ የዓለምን ሪከርድ በመስበር የአገራቸውን ሰንደቅ ዓላማ በዓለም መድረክ ከፍ ላደረጉት ለብላክ ላዮን የሰርከስ ቡድን አባላት እውቅናና አቀባበል አድርገዋል፡፡

ሚኒስትሩ የሰርከስ ቡድኑ ባስመዘገበው አስደማሚ ድል የተሠማቸውን ደስታ ገልፀው፤ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰርከስ ማህበራት ጥምረት ፕሬዝዳንት ተክሉ አሻግር በበኩላቸው፤ የቡድኑ ውጤት የመጀመሪያ እንዳልሆነና ከዚህ በፊት በኢትዮጵያውያን ዘጠኝ የዓለምን ክብረ ወሰን መሰበሩን ገልፀዋል፡፡

በሌላ በኩል በፈረንሳይ ሞንተካርሎ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሰርከስ ፈስትቫል ላይ የተሳተፈው አፍሪካን ድሪም የሰርከስ ቡድን የብር ሜዳሊያና ሰርትፊኬት በማግኘት በድል መመለሱን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ #EBC

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
12.8K viewsedited  07:13
Buka / Bagaimana
2024-02-02 14:36:24 ረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት እንድትሰጡ

ትምህርት ሚኒስቴር ረቂቅ መመሪያዎች ላይ አስተያየት መስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አስተያየት እንዲሰጥ መድረክ መመቻቸቱን አሳውቋል።

የትምህርት ሚኒስቴር: -

1. የአጠቃላይ ትምህርት የመምህራን የደረጃ እድገት የአፈጻጸም መመሪያ፣

2. የር/መምህራን፣ የም/ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የምልመላ መረጣና ምደባ የአፈጻጸም መመሪያ፣

3. የቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ዕጩ ምምህራን ምልመላና መረጣ የአፈጻጸም መመሪያ፣ የሚሉ 3 መመሪያዎችን አዘጋጅቷል።

መመሪያዎቹ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አስተያየት ሰጥተውባቸው የዳበሩ ሲሆን የፌደራል አስተዳደር ስነ-ስርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012 ክፍል 2 ንዑስ ክፍል 2 አንቀጽ 10 መሰረት የሚዘጋጁ መመሪያዎች ከመጽደቃቸው በፊት ማንኛውም ሰው የሚሳተፍበት የውይይት መድረክ ማዘጋጀትና ግብዓት መሰብሰብ እንዳለበት ስለሚደነግግ ሚኒስቴሩ የውይይት መድረከ አዘጋጀቷል።

በዚህም መሰረት ጥር 30/2016 ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ለባለድርሻ አካላት የገለጻና የውይይት መድረክ ስለተዘጋጀ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በመገኘት አስተያየት እንድትሰጡ ተጋብዛችኋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.0K viewsedited  11:36
Buka / Bagaimana
2024-01-31 18:39:04 የመውጫ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ተራዝሟል - የካቲት 06 እስከ 09/2016 ዓ.ም

የመውጫ ፈተናው ከጥር 27 እስከ የካቲት 01/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም። ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ይፋ ባደረገው መርሐግብር ፈተናው ከየካቲት 06 እስከ 09/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቋል።

ለአዲስ ተፈታኞች ሞዴል ፈተና ከጥር 27 እስከ 30/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። የተፈታኞች ዝርዝር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚላክም ተገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
15.9K viewsedited  15:39
Buka / Bagaimana
2024-01-31 11:22:55
በቀን አንድ ጊዜ የመምህራን ምገባ ተጀመረ

ኦሮሚያ ክልል ላይ መምህራን የሚከፈላቸው ወርሃዊ ደመወዝ በተፈጠረው ኑሮ ውድነት ምክንያት ወር እስከ ወር እያደረሳቸው አይደለም ።

ይሄ ጉዳይ በጣም ያሳሳሰበው የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በቀን አንድ ጊዜ የመምህራን ምገባ ተግባራዊ እንዲሆን አድርጓል።

ይሄ የምገባ ፕሮግራም በሌሎች ክልሎች ባሉ ትምህርት ቤቶችና በዩኒቨርሲቲዎች ሊጀመር ይችላል የሚሉ አሉ::

በተያያዘ ዜና በአፋር ክልል በአይሳኢታ ከተማ መምህራኖች የሁለት ወር ደመወዝ ባለመከፈላቸው ከሰኞ ጀምሮ ትምህርት ተቋርጧል ሲሉ መምህራኖቹ ገልፀዋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
16.6K viewsedited  08:22
Buka / Bagaimana
2024-01-30 12:37:07
እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንዲልኩ

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት የተማሪዎቻቸውን ዝርዝር መረጃ እንዲልኩ ጠይቋል፡፡

ፈቃድ በተሰጣቸው የትምህርት መስኮች በ2016 ዓ.ም ተመዝግብው እየተማሩ ያሉ ተማሪዎችን ዝርዝር መረጃ እና በ2015 ዓ.ም የተመረቁ ተማሪዎች (የመውጫ ፈተና ያለፉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች) ዝርዝር መረጃን እስከ የካቲት 30/2016 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ እንዲልኩ ባለሥልጣኑ አሳስቧል፡፡

ይህም የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠብቅ እንዲሁም የተመረቁ ተማሪዎች መጉላላት እንዳይገጥማቸው ባለሥልጣኑ ለሚያከናውናቸው ተግባራት አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል፡፡ #ETA
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
15.8K viewsedited  09:37
Buka / Bagaimana