Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

Alamat saluran: @ethiopian_digital_library
Kategori: Pekerjaan
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 64.41K
Deskripsi dari saluran

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru

2024-05-07 18:52:25 ግንቦት 1 ቀን ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች ከተማ አቀፍ የሙያ ብቃት ምዘና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በመሆን የሚሰጠውን ከተማ አቀፍ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና አፈጻጸምን አስመልክቶ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ምዘናው መንግስት ለትምህርት ጥራትና መሻሻል ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በተሻለ ለመምራት የሚያስችል መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ መምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ቁልፍ ሚና ያላቸው አካላት በመሆናቸው ምዘና መደረጉ ተገቢና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ዋነኛው ሂደት ነው ብለዋል፡፡ ዶክተር ዘላለም አያይዘውም ፈተናውን በተሳካ መልኩ ለማካሄድ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ በበኩላቸው ምዘናው የመምህራንን የሙያ ብቃት ለማሳደግና እውቅና ለመስጠት ከማስቻሉም በላይ መምህራንና የትምህርት አመራሩን በበቂ ስነ-ልቦና ለማስተማርና ለመምራት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡ የምዘናውን አካሄድ ውጤታማ ለማድረግም የትምህርት አመራሩና የክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊዎች ለተፈታኞች የሚሰጡ ቅድመ ምዘና ገለጻዎች ላይ በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

ምዘናው በፈቃደኝነት ለተመዘገቡ 18 ሺ 591 ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ሃሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በተመረጡ የመፈተኛ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ እንዲሁም በምዘናው ወቅትም ተመዛኞች ስልክም ሆነ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ ግብአቶች ይዘው ፈተና ክፍል መግባት እንደማይችሉ ፣ ተመዛኞች የታደሠ መታወቂያ ይዘው መገኘት እንደሚጠበቅባቸው ፣ ተመዛኞች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት 1:00 ሠዓት ቀደም ብለው (1:30) ላይ የምዘና መስጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት እንዳለባቸው እና አርፍዶ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኛው ገብሩ ፣ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ የባለስልጣን መስራቤቱ ማኔጅመንት አባላት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳና አባላት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እንዲሁም የሁለቱም ተቋማት የክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.6K viewsedited  15:52
Buka / Bagaimana
2024-05-05 18:41:18
በ16 አመቷ ዲግሪ በመያዝ ክብረ ወሰን የሰበረችው ኢትዮጵያዊት

ኢትዮጵያዊቷ ሀና ቴይለር ሽሊትዝ በአሜሪካ ከሚገኘው የቴክሳስ የሴቶች ዩኒቨርሲቲ በ16 አመቷ የሶሺዮሎጂ ትምህርቷን በማጠማቀቅ በእህቷ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን መስበሯ ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም የሀና ወንድም የሆነው ኢያን በ17 አመቱ ፒኤችዲውን ያገኘ መሆኑ ሲነገር ታላቅ እህቷ የሆነችው ሃሌይ ቴይለር በአሜሪካ ታሪክ በእድሜ ትንሿ ተመራቂ ተማሪ በመሆን በህግ ት/ት ዲግሪ የያዘች መሆኑም ተጠቁሟል።

ሀና ገና ስትወለድ እናቷን በቲቢ በሽታ ምክንያት አጥታለች። "የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ግንኙነቴ ነበር ከእናቴ ጋር።፤ ፎቶ እንኳን የለኝም። በሚታከም በሽታ ነው እናቴን ያጣሁት" ስትል ከኒዊስዊክ ጋር በነበሬት ቆይታ ገልጻለች።

የእናቷን ህልፈት ተከትሎ የ10 ወር ህጻን እያለች አሳዳጊዎቿ ወደ አሜሪካ የወሰዷት ሲሆን እሷም በተመሳሳይ ልክ እንደ እናቷ በቲቢ በሽታ ታምማ መቸገሯን ነው ያስታወሰችው።

"የኔ ከቲቢ በሽታ መትረፍ የመዳን ምስክርነት ብቻ ሳይሆን በአሜሪካ ያለው የማኅበረሰብ ጤና አገልግሎት ጥንካሬ ነው። " ስትል ሀና ትናገራለች።

በ ኤክስ ገጿ ስለራሷ ባሰፈረችው አጭር ገለጻ ባዮ " በጉዲፈቻ ከኢትዮጵያ የመጣው፤ ከቲቢ በሽታ የተረፍኩ፤ አሁን በሶሾሎጂ የPHD ትምህርቴን በመከታተል ላይ ያለው፤ ለጤና ፍትኃዊነትና የቲቢ በሽታን ለማጥፋት የምታገል" ስትል አስፍራለች።

 @Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.2K viewsedited  15:41
Buka / Bagaimana
2024-05-04 10:49:32 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2025 አሸናፊዎች ዛሬ ቅዳሜ ምሽት 1:00 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይሆናል!

ለዲቪ (Diversity Visa) 2025 ማመልከቻ የሞሉ ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።

ማስታወሻ:— የማረጋገጫ ቁጥር ማመልከቻው ሲሞላ የተሰጠ ነው። ይህ ቁጥር የጠፋበት Forgot Confirmation Number በማለት አስፈለጊ መረጃ በመሙላት በኢሜል አዲስ ቁጥር ማግኘት ይቻላል።

ውጤቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ቅዳሜ ሚያዚያ 26/2016 ከምሽት 1:00 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ይሆናል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል ፣ ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው ምንደውለው / ይህን ኢሜል / ቴክስት የምንልከው " በማለት የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁ አሳስቧል።

አንድ አመልካች ዲቪ 2025 ደርሶት እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማወቅ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ  ይሄ dvprogram.state.gov/ESC/ ድረገጽ መሆኑን አስገንዝቧል።

አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ (ኢትዮጵያ ጨምሮ) ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 55 ሺህ ሰዎችን በዲቪ (DV) ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
15.2K viewsedited  07:49
Buka / Bagaimana
2024-05-03 12:33:38
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን እንመኛለን!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
16.3K viewsedited  09:33
Buka / Bagaimana
2024-05-02 18:14:29 ማስታወቂያ

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 - 21/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ለማኔጅመንት (Management)ና አካውንቲንግ (Accounting) ተፈታኞች የonline (zoom) ቱቶሪያል አዘጋጅተናል::

ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ::

Link: https://t.me/+_atK7wICcpEwOThk
14.9K viewsedited  15:14
Buka / Bagaimana
2024-05-02 16:46:31 የመምህራን ደመወዝ በመከፈሉ በወላይታ ዞን የተቋረጠው ትምህርት ተጀምሯል

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን፣ ላለፉት ሁለት ወራት ያህል ታጉሎ የቆየው የመምህራን ደመወዝ በመከፈሉ የተቋረጠው የመማር ማስተማር ሒደት መቀጠሉን፣ የክልሉ የመምህራን ማኅበር አስታወቀ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ዐማኑኤል ጳውሎስ፣ ችግሩ ተፈጥሮባቸው የነበሩት የአንድ ከተማ አስተዳደር እና የ20 ወረዳዎች ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ መመለሳቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

ለደኅንነታቸው ስለሚሰጉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ውስጥ የሚያስተምሩ የአካባቢ ሳይንስ መምህር፣ ለሁለት ወር ያህል የታጎለባቸው ደመወዝ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በመከፈሉ ከሚያዝያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. አንሥቶ ተቋርጦ የቆየው ትምህርት መቀጠሉን በስልክ ተናግረዋል፡፡

መምህራን ወደ ሥራቸው የተመለሱት፣ የሁለት ወር ደመወዛቸው በከፊል እና ሙሉ በሙሉ በመከፈሉ መኾኑን፣ ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁት ሌላው መምህር ገልጸዋል፡፡ #VOA

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
15.4K viewsedited  13:46
Buka / Bagaimana
2024-05-02 14:12:30 እሳት ፣ ውሃ ፣ እውነትና ሃሰት

እሳት፣ ውሃ፣ እውነትና ሃሰት ጓደኞች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ሃሰት በዚህ ጥምረት ደስተኛ ስላልነበረ አንድነታቸውን ማበላሸት ፈልጎ እንዲህ አለ “ለምን ወደ አንድ ስፍራ ተጉዘን እያንዳንዳችን የራሳችንን ግዛት አንመሰርትም? ስለዚህ ተነስተን አብረን እንጓዝ፡፡” ሁሉም በሃሳቡ ተስማምተው ሲሄዱ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሀሰት ወደ ውሃ ጠጋ ብሎ “እሳት ሣሩን፣ ደኑንና ቁጥቋጦውን የሚያቃጥል ቀንደኛ ጠላታችን ስለሆነ ለምንድነው ከእርሱ ጋር ግዛት ፍለጋ የምንሄደው?” አለው፡፡

ውሃም “ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አለ፡፡ ሃሰትም ቀበል አድርጎ “ልንገድለው እንደሚገባ ግልፅ ነው፡፡ እሳትን የማጥፋት ብቸኛ ኃይል ያለህ ደግሞ አንተ ነህ፡፡ እናም ቁጭ ሲል ጠብቀህ እላዩ ላይ ራስህን በመርጨት አጥፋው፡፡” አለው፡፡ ውሃም “ራሴን መሬቱ ላይ ከረጨሁ ተመልሼ ውሃ መሆን አልችልም፡፡” አለ፡፡

ሀሰትም “ችግር የለውም፡፡ ተረጭተህ እንዳትበታተን የተወሰኑ ድንጋዮች በዙሪያህ አኖርና በኋላ እሰበስብሃለሁ፡፡” አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ያልጠረጠረው እሳት መጥቶ ቁጭ ሲል ውሃው አንድ ጊዜ በላዩ ላይ ሲረጭ ሃሰት ድንጋዮች ዙሪያውን አድርጎ ውሃውን ከሰበሰበውና እሳትን ካስወገዱ በኋላ አብረው መጓዝ ጀመሩ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሃሰት ውሃውን “ለምን እዚህ ገደል አፋፍ ላይ ቁጭ ብለህ በተፈጥሮ ውበት አትዝናናም?” አለው፡፡

ውሃም አፋፉ ላይ ቁጭ ሲል ሃሰት ቀስ ብሎ ተነስቶ ውሃ የተቀመጠባቸውን ድንጋዮች ከስሩ ሲለቅማቸው ውሃው በመረጨት በዚያው ተበታትኖ ጠፋ፡፡

በመጨረሻም ሃሰት እውነትን ማጥፋት ነበረበትና ወደ አንድ ትልቅ ተራራ በተቃረቡ ጊዜ ሃሰት እውነትን ከተራራው ግርጌ ቁጭ በል ብሎት ከተራራው አናት ላይ ትልቅ አለት ቁልቁል በመልቀቅ እውነትን ሊጨፈልቀው ሲል እውነት ቀልጠፍ ብሎ ማምለጥ በመቻሉ አለቱ ተንከባሎ ሲፈረካከስ ከውስጡ አልማዝ፣ ወርቅና ልዩ ልዩ የከበሩ ማዕድናት ወጡ፡፡ ሃሰትም የእውነትን አስከሬን ሊመለከት በመጣ ጊዜ እነዚህን ሁሉ የከበሩ ድንጋዮች አየ፡፡

እናም “እነዚህ ሁሉ ከየት መጡ?” ብሎ ጠየቀ፡፡ እውነትም “አለቱ እላዬ ላይ ሲወድቅ እነዚህ ማዕድናት ወጡ፡፡” አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ሃሰት “አሁን ደግሞ እኔ ከተራራው ግርጌ ልቀመጥና አንተ አለቱን በላዬ ላይ ልቀቅብኝ፡፡” አለው፡፡ እናም እውነት ወደ ተራራው ጫፍ ወጥቶ ትልቅ አለት ወደታች በለቀቀ ጊዜ አለቱ የሃሰት አናት ላይ አርፎ ሃሰትን ጨፈላልቆ ገደለው፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
15.8K viewsedited  11:12
Buka / Bagaimana
2024-05-02 10:15:45
ዲቪ 2025 ቪዛ ሎተሪ ውጤት ከሁለት ቀን በሗላ ይለቀቃል

2025 Entrant Status Check

DV-2025 Entrants may enter their confirmation information through the link below starting at noon (EDT) on May 4, 2024.

DV-2025 Entrants should keep their confirmation number until at least September 30, 2025.

Link: https://dvprogram.state.gov/

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.1K viewsedited  07:15
Buka / Bagaimana
2024-04-29 15:54:54 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ይሰጣል

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3 እስከ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #Entrance2016

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.0K viewsedited  12:54
Buka / Bagaimana
2024-04-28 13:33:30
ልዩ የመምህራንና የትምህርት አመራር የአቅም ማጎልበቻ የክረምት ስልጠና

ትምህርት ሚኒስቴር በቀን14/08/2016 ዓ.ም በቁጥር፡- 10/242/897/2016 በተፃፈ ደብዳቤ በትምህርት ስርዓቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ መኆኑን በመግለጥ ከዚህም መካከል የመምህራንንና ትምህርት አመራሮችን አቅም ለመገንባት በክረምት ልዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መርሃ ግብርን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለመጀመሪያ ዙር የሚሰጥ ይሆናል::

በመሆኑ በዚህም ዙር በእንግሊዝኛ፣ ሂሳብ፣ በፊዚክስ፣ በኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ የትምህርት መስኮች በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመምህርነትና በትምህርት አመራርነት በመስራ ላይ ያሉት ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡ #የአዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር_ትምህርት_ቢሮ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.4K viewsedited  10:33
Buka / Bagaimana