Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

Alamat saluran: @ethiopian_digital_library
Kategori: Pekerjaan
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 65.82K
Deskripsi dari saluran

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru 8

2024-05-24 09:37:12
AI Teacher Robot in Kerala, India

AI መምህርት ሮቦት በኬረላ፣ ሕንድ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
8.1K viewsedited  06:37
Buka / Bagaimana
2024-05-24 09:10:51
8.1K views06:10
Buka / Bagaimana
2024-05-24 09:10:36 የዕጩ ዶክተሩ የመጨረሻ ማስታወሻ !!!

ሞት የማይቀር ዕዳ መሆኑን ባውቅም ቀጠሮ ተሰጥቶት ቀን ሲቆረጥ ግን ያስፈራል! ይገርማል! ሞት እንዲህ ያስፈራል ? በጣም ፈራሁ !መኖር ለካ እንዲ ያጓጓል ? በእውነት ጓጓሁ ! ፤ ልጆቼ አሳሱኝ! እንደ አዲስ ናፈቁኝ ! ትንሹ ወንድ ልጄ ! እህቶቹ ፤ ውዴ ፣ ጓደኞቼ ፣ዘመዶቼ ፣ የልጅነት አብሮ አደጎቼ ፤ባልደረቦቼ ፣የሀገሬ ልጆች ያደኩበት መንደር ሁሉም ናፈቁኝ ! እጣፈንታዬን ረገምኩት !

ወንድሞቼ ሆይ ዛሬ ጭላንጭል የመኖር ዕድል እና ዘላለማዊ እንቅልፍ በህይወቴ ተፋጠዋል ። ሁለት ምርጫ ይባል እንጂ ነገሩስ ምርጫ አይደለም ። ለአንድ ተራ አስተማሪ ሚሊዮን ብር ከፍሎ ህይወቱን ማዳን እንዴት ይቻለዋል ? ከፍቶኛል! ሆድ ብሶኛል ! ! ወንድማችሁ በጥልቅ ሀዘን ውስጥ ነኝ ።

ግን ሀዘኔን ለማን ልስጥ ? ሰው ተቸግሯል ! የቸገረውን ሰውስ ምን ብዬ ላስቸገር ? ግን ነብስናትና ጨነቀኝ !! ያለኝን ሀብትና ንብረት በመሸጥ የኩላሊት እጠበት በሳምንት ሦስቴ እያደረኩ ከልጆቼ ጋር ያለኝን እድሜ ላማራዝምና ህይወቴን ለማቆየት ሞከርኩ ጣርኩ ! ወዳጆቼን ፣ ጓደኞቼን አስቸገርኩ ያው ትርፉ መከራን በቤተሰቤና ወዳጆቼ ላይ ማዝነብ ሆነ ፤ የእውነት !አሁን ደከመኝ ! አልቻልኩም ! የጥቁር አንበሳ ሆስፒታልም ከንግዲህ በዲያሊስስ መቆየት አትችልም አቅሙ ካለህ ወደ ውጪ ሄደክ... አለኝ ። ወይ አቀም ! እቅሜና ተስፋዬ አምላኬና ወገኖቼ ብቻ ናቸው ። ዝም ካላችሁኝ በዝምታ አንቀላፋለሁ ከራራላችሁልኝ ደግሞ በእናንተ በኩል ይሰራል !

የሆነ ጊዜ ያነበብኩት አንድ የመቃብር ላይ ጽሁፍ ትዝ አለኝ ጽሁፉ " አሞኛል ብዬ ነግሪያችሁ ነበር " ይላል

ያው እኔም ቢቀለኝ ብዬ ነው የነገርኳችሁ ።

ወንድሞቼ ሆይ አሞኛል !

ከፉ ደዌ ከምወዳቸው ልጆቼ ሊለየኝ ነውና እርዳታችሁ ያስፈልገኛል ! በፍጹም ተስፋ አልቆርጥም ህይወቴ እስካለች ተስፋ አደርጋለሁ ግን
አ ሞ ኛ ል ቢሆንም ከህመሜ ድኜ ዶክትሬቴን ተቀብዬ ለምስጋና በዚሁ እመለስ ይሆናል !?

እሱ ካለ ?
ሀብት ንብረት የለኝም ያፈራሁት ሀብት ልጆቼ ተማሪዎቼ ብቻ ናቸው !
ወንድማችሁ እጩ ዶ/ር መ/ር አዲሱ ዳንኤል
ከአርባምንጭ ትምህርት ኮሌጅ !
ስልክ+251916881107

አዲሱ ዳንኤል ሻሎ
የባንክ አካዉንት
1. ንግድ ባንክ
1000032842392
2. አቢስንያ ባንክ
S/A 5442672
3. ቡና ባንክ
1869501007218
7.8K viewsedited  06:10
Buka / Bagaimana
2024-05-24 08:57:57 እንኳን ከኳስ ከጥይትም እናመልጣለን #Just_for_fun

ከዕለታት አንድ ቀን አፄ ኃይለሥላሴና የኬንያው ፕሬዝደንት ጆሞ ኬንያታ የአገሮቻቸው ብሔራዊ ቡድኖች የእግር ኳስ ግጥሚያ ሲያደርጉ ይመለከቱ ነበር፡፡

ታዲያ ሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ ጨዋታው ይጠናቀቃል፡፡ በመጨረሻም የጨዋታው ዳኛ ሁለቱ መሪዎች እንደ ግብ ጠባቂ ሆነው ጨዋታው ይዳኛል ብለው ወሰኑ፡፡

በዚህም መሠረት በመጀመሪያ ጆሞ ኬንያታ ግብ ጠባቂ ሆነው የኢትዮጵያው ንጉስ ፍፁም ቅጣት ምት በመምታት ጎል አስቆጠሩ፡፡

ቀጥሎ ፍፁም ቅጣት ምት መምታቱ የኬንያው ፕሬዝደንት ተራ ስለነበር የኢትዮጵያው ንጉሥ ጎል ጠባቂ ሆኑ፡፡

እናም የኬንያው መሪ ኳሱን ለመምታት ከሌላኛው የግብ ክልል ተነስተው ሜዳውን ሙሉ ሲንደረደሩ ባዩ ጊዜ የኢትዮጵያው ንጉሥ ግቡን ትተው ስለሸሹ የኬንያው መሪ ግብ ያስቆጥራሉ፡፡

ኃይለሥላሴም “ለምንድነው የሸሹት?” ተብለው ሲጠየቁ “እኛ ኢትዮጵያውያን እንኳን ከኳስ ከጥይትም እናመልጣለን፡፡” ብለው መለሱ ይባላል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
6.0K viewsedited  05:57
Buka / Bagaimana
2024-05-24 08:45:46 በኦንላይን የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መንግሥት በሚያዘጋጃቸው ኮምፒውተሮች ይከናወናል

በዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀት እንዲሁም በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በተለይ የግል ትምህርት ቤት ተፈታኞች የራሳቸውን ላፕቶፕ እንዲያዘጋጁ ተወስኗሉ የሚሉ መረጃዎች ሲዘዋወሩ ታይቷል፡፡

"ይህንን በተመለከተ ለትምህርት ቤቶች የተላለፈ መልዕክት አለመኖሩንና ወላጆች ኮምፒውተር እንዲያዘጋጁ መጠየቃቸውም ተገቢ አለመሆኑን" የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡

"ፈተናው መንግሥት በሚያዘጋጀው የኮምፒውተር አቅርቦት ይከናወናል" ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ "ተማሪዎች አንብበውና በቂ ዝግጅት አድርገው የተመዘገቡበትን መታወቂያ ብቻ ይዘው መምጣት ነው የሚጠበቅባቸው" ብለዋል፡፡ "ሆኖም ትምህርት ቤቶችም ሆኑ ተማሪዎች የግል ኮምፒውተሮቻቸውን ለፈተናው መጠቀም ከፈለጉ እንደማይከለከሉ" ተናግረዋል፡፡

በኦንላይን ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በልምምድ ላይ እንደሚገኙ ያነሱት ኃላፊው፤ 156 የኮምፒውተር ባለሙያዎች ሰልጥነው በክልሎች ስልጠና እንዲሰጡ መሰማራታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በዘንድሮው ፈተና ልምዶችን በመያዝ፤ በሚቀጥሉት ከ3 እስከ 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የ12ኛ ክፍል ፈተናን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን የመስጠት ዕቅድ መኖሩን ገልፀዋል፡፡

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ እንዲሁም ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
7.4K viewsedited  05:45
Buka / Bagaimana
2024-05-21 16:58:01 ራስ ሐይሉ በጄኔቫ #Just_for_fun

የጎጃም አገረ ገዢ የነበሩ ራስ ሐይሉ ኢትዮጲያን የተባበሩት መንግስታት አባል ለማድረግ ከአፄ ሃይለስላሴ ጋር ወደ ጄኔቫ ይጓዛሉ፡፡ በኋላም ወደ ኢትዮጲያ በመመለስ ላይ እያሉ ሮምን ሲጎበኙ አንድ ሱቅ ውስጥ ገብተው “ይህ መላጫ ስንት ነው?” ብለው ይጠይቃሉ፡፡

“እንደዚህ ያለውን መላጫ በውድ ዋጋ ነው የምንሸጠው፡፡ ለመሆኑ እንደዚህ አይነቱን ውድ መላጫ በድሃ አገራችሁ ላይ ምን ያደርግላችኋል?” ብሎ ሻጩ በማሾፍ ጠየቀ፡፡

ራስ ሐይሉም “ይህ አንተን አያገባህም፡፡ ዋጋውን ብቻ ንገረኝና ሽጥልኝ፡፡ ምን እንደማደርግበት እኔ አውቃለሁ፡፡ የህዝቤም ፀጉር በጣም ለስላሳ ነው፡፡” አሉት፡፡

በዚህም ሁኔታ መላጫውን ገዝተው በመመለስ አዲስ አበባ ውስጥ ፀጉር ማስተካከያ ቤት ከፈቱ፡፡ የራስ ሐይሉ ፀጉር ማስተካከያ ቤት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሳይሆን አይቀርም።

ሮም በነበሩም ጊዜ አንድ ሰው “እናንተ ጥቁር ሰዎች ዝንጀሮ ነው የምትመስሉት፡፡” ሲላቸው ራስ ሐይሉም “አዎ! ሁለታችንም ዝንጀሮ ነው የምንመስለው እኔ ፊቷን ስመስል አንተ መቀመጫዋን ትመስላለህ::” ብለውት ነበር ይባላል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.0K viewsedited  13:58
Buka / Bagaimana
2024-05-21 16:52:19 የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ

በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ አመልካቾች በሙሉ፤ ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 – 21/2016 መሆኑን አውቃችሁ የምዝገባ ክፍያ አምስት መቶ (500.00) ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ

1. ለመጀመሪያ ጊዜ የመጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል።

2. የድጋሚ ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ  አምስት መቶ ብር (500.00 ብር) በቴሌ ብር ብቻ የሚከናወን ይሆናል።

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
12.3K viewsedited  13:52
Buka / Bagaimana
2024-05-21 10:53:29ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ለመመገብ ተቸግረዋል

በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ዩንቨርስቲዎች መንግስት በመደበው በቀን 22 ብር በጀት ተማሪዎችን በቀን ሦስት ጊዜ ለመመገብ መመገብ እንደተቸገሩና ተማሪዎች ለረሀብ የሚጋለጡበት ዕድል እየተቃረበ መምጣቱን ዋዜማ ካሰባሰበችው መረጃ ተረድታለች።

የጎንደር ዩንቨርሲቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ይዳኙ ማንደፍሮ፣ ዩንቨርሲቲያቸው ባገጠመው ተማሪዎቹን በቅጡ የመመገብ ችግር የተነሳ፣ ለሌሎች ሥራዎች ከያዘው በጀት ወደ ተማሪዎች ምገባ በማዛወር፣ ምገባውን ለማስቀጠል ጥረት እያደረገ መሆኑን ለዋዜማ ተናግረዋል። ዩንቨርሲቲው፣ መንግሥት በመደበው 22 ብር ተማሪዎቹን በቀን ሦስት ጊዜ መመገብ እንደማይችል ጠቅሰው፣ ምንም ማድረግ ባይቻልም ልጆቹ ችግር ላይ መውደቅ ስለሌለባቸው፣ በተለያዩ ጥረቶች ከዚህ ቀደም የነበረው ምገባ እስከአሁን አልተቋረጠም ብለውናል።

የሕዝብ ግንኙነቱ እንደሚሉት፣ ዩንቨርሲቲው በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ዘግይቶ ተማሪዎቹን መቀበሉ፣ እንዲሁም ለተማሪዎች የሚቀርበው ምግብ ኹሉም ግቢ ውስጥ የሚዘጋጅ መሆኑ የምግብ ለውጥ ሳያደርግ እንዲቀጥል አስችሎታል። ዩንቨርሲቲው በቀጣይ ዓመት መስከረም ላይ የሚቀበላቸውን ተማሪዎች እስከ ቀጣዩ ሰኔ ወር ድረስ ለመመገብ፣ አሁን ላይ በተቀመጠው በጀት የማይታሰብ እንደሆነ ለዋዜማ ነግረዋታል። ከጊዜ ወደ ጊዜ የምግብ ዋጋ እየጨመረ ስለሆነ፣ መንግሥት ያስቀመጠው በጀት ከሦስት ወር የዘለለ ለመመገብ አያስችልም ያሉት ኃላፊው፣ መንግሥት ይህን አይቶ የበጀት ጭማሪ ካላደረገ መጪው የትምህርት ዓመት ከባድ ነው ሲሉም ስጋታቸውን ገልፀዋል።

የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፋሪስ ደሊል (ዶ/ር) መንግሥት ለአንድ ተማሪ የዕለት የምግብ ወጪ የመደበው 22 ብር የማይበቃ መሆኑን ገልጸው፣ ዩንቨርሲቲው ለሌላ ከያዘው በጀት በማዛወር ተማሪዎችን እየመገበ መሆኑን ለዋዜማ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ በጀቱ በቂ እንዳልሆነ እና እየተቸገርን መሆኑን መንግሥት ያውቃል ሲሉ ገልጸው፣ ትምህርት ሚንስቴርም ጉዳዩን በትኩረት ይዞ ጥናት በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል። ግንቦት 08/2016 ከትምህርት ሚንስቴር ጋር በነበረን የጋራ መድረክ ባለፉት ሦስት ዓመታት የተማሪዎች ቁጥር እና አማካኝ የተማሪ የዕለት የምግብ ወጪ ከዩንቨርሲቲዎች መረጃ ሰብስቧል፣ ስለዚህም በቀጣይ በአጭርና በረዥም ግዜ የሚፈታ ጉዳይ ይኖራል ሲሉ ተናግረዋል።

በአጭር ግዜ ውስጥ መንግሥት አሁን ያለውን የተማሪዎች የዕለት የምግብ ተመንን እንደሚያሻሽል እንጠብቃለን ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ በረዥም ጊዜ ደግሞ ሌሎች አገራት የሚከተሉትን ስርዓት ለመከተል እና ሌሎች አማራጮችን ለመውሰድ ጥናት እየተደረገ መሆኑ ተነግሮናል ብለዋል።
ዩንቨርሲታያችን አሁን ባለው የኑሮ ሁኔታ ለአንድ ተማሪ የዕለት የምግብ ወጪ 120 ብር ቢመደብ አብቃቅቶ መጠቀም ይችላል ሲሉ ገልጸው፣ አሁንም ዩንቨርሲቲው ለአንድ ተማሪ የተጠቀሰውን ያህል ገንዘብ ለዕለት የምግብ ወጪ እያወጣ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ፣ የበጀት ጉድለቱን ተከትሎ የምግብ ቅያሬ መደረጉን ገልጸው፣ ማስተካከያ ባናደርግ ኖሮ ተማሪዎችን መመገብ አንችልም ነበር ነው ያሉት።

መንግሥት ማሻሻያ ሲያደርግ የአገሪቷን አቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን ጠቁመው፣ ሆኖም በቀጣይ ማሻሻያ ሲደረግ ስንት ብር ሊሆን እንደሚችል መገመት አልችልም ብለዋል። በቅርቡ ገንዝበ ሚንስቴር ዩንቨርሲቲዎች የቀጣይ ዓመት የበጀት ዕቅዳቸውን እንዲያሳውቁ በጠየቀው መሰረት፣ በጀታችንን ስንሰራ የተማሪዎች የምግብ ወጪን ያሰላነው በነበረው 22 ብር ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ማሻሻያ ሲደረግ በጀቱ ላይ ጭማሪ ይደረግልናል ብለዋል።

የባህር ዳር ዩንቨርሲቲ ሰላም ካምፓስ የተማሪ ሕብረት ተወካይ በበኩሉ፣ በበጀት ችግር ምክንያት የታጠፉ የምግብ ዝርዝሮች ከመኖራቸው ባለፈ በዚህ ዓመት በሳምንት ኹለት ቀን ለቁርስ ይቀርብ የነበረው የቲማቲም ስልስ እንዲቀር መደረጉን ነግሮናል። ከዚሁ ከበጀት እጥረት ጋር በተያያዘም ዕሮብ እና አርብ ጠዋት ቁርስ ላይ እንጀራ ፍርፍር ይቀርብ የነበረ ሲሆን፣ የአንዱ ቀን ባለፈው ዓመት፣ ቀሪው ደግሞ ዘንድሮ እንዲታጠፍ ተደርጎ ሻይ እና ዳቦ ብቻ እንዲቀርብ መደረጉን ጠቁሟል። ከእነ ጉድለቱም ቢሆን ለተማሪዎች የሚቀርበው ፓስታ ጥሩ ነው ያለው ተወካዩ፣ በቀጣይ ይህም ይቀራል የሚል ስጋት በተማሪዎች ዘንድ መኖሩን ጠቁሟል። የሚለወጥ እና የሚሻሻል ነገር ስለሌለም ተማሪዎች ችግሩን አውቀው ተቀብለውታል ያለው የተማሪዎቹ ተወካይ፣ ችግሩ በኹሉም የዩንቨርሲቲው ካምፓሶች ተመሳሳይ መሆኑን መረዳቱንም ጠቅሶልናል።

ስሜ እንዲጠቀስ አልፈልግም ያሉን አንድ የጅማ ዩንቨርሲቲ የሥራ ኃላፊም፣ ዩንቨርሲቲው ያልተከፈል ብዙ የምግብ ዕዳ እንዳለበት ለዋዜማ ገልጸዋል። ምግብ ለማቅረብ ከዩንቨርሲቲው ጋር ኮንትራት የገቡ ነጋዴዎችም እናቀርብም እያሉ ያስፈራሩናል ያሉት ኃላፊው፣ መንግሥት ከመደበው በጀት አንጻር “በተዓምር” ነው ተማሪዎችን እየመገብን ያለው ሲሉም የሁኔታውን ከባድነት ተናግረዋል።

ለአራት ሰው መቅረብ ያለበትን ምግብ ለሦስት ሰው ወይም ለ20 ሰው የሚቀርበውን ምግብ ለ15 ሰው በማቅረብ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት እንዲመገቡ ለማድረግ እንደሚሞከርም አመልክተዋል።

ዩንቨርሲቲው በስሩ የሚያስተዳድረውን ሆስፒታል ጨምሮ ትልቅ የገንዘብ እጥረት እንዳለበትም የጠቆሙት ኅላፊው፣ “በ22 ብር አንድን ሰው ቁርስ፣ ምሳ እና እራት መመገብ አሁን ባለው ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው፤ በዚህ ገንዘብ ተማሪዎችን እየቀለቡ ያሉ ዩንቨርሲቲዎች ሊመሰገኑ ይገባል” ሲሉም የሁኔታውን አስቸጋሪነት አጋርተውናል።

መንግሥት 15 ብር የነበረውን የአንድ ተማሪ የዕለት የምግብ ወጪ ወደ 22 ብር ለማሳደግ ረዥም ጊዜ እንደፈጀበት ጠቅሰው፣ አሁን ያለው የኑሮ እውነታ ስለሚታወቅ በጀቱን በድጋሜ ማስተካከል ግዴታ ነው ብለዋል። ኃላፊው ዩንቨርሲቲው በጉዳዩ ላይ ለመንግሥት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል።

በዋቻሞ ዩንቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪ የሆነው በረከት በበኩሉ፣ ባለፉት ዓመታት ሲቀርብ የነበረው የምግብ ዝርዝር ላይ ለውጥ ባይደረግም፣ አልፎ አልፎ እንጀራ አለቀ እንደሚባል፤ እንዲሁም የሚቀርበው ምግብ ጥራት እንደሚጎድለውና መጠኑም እያነሰ መምጣቱን ተናግሯል።

ወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ በበኩሉ፣ በምግብ ግብዓቶች ዋጋ መጨመር ምክንያት በምግብ አቅርቦት ላይ ማሻሻያ ለማድረግ መገደዱን ከሳምንት በፊት አሳውቆ ነበር። #ዋዜማ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
10.4K viewsedited  07:53
Buka / Bagaimana
2024-05-21 10:46:44
በ አሪፍ ዋጋ አሪፍ ገፅታ አሁን ይግዙ
የዋጋ ግሽበት ከመቼውም በላይ እየጨመረ ይገኛል :: #Ethiopia ከዓለም በዋጋ ግሽበት 10 ኛ ደረጀ ላይ ተቀምጣለች :: በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ብሮት ዋጋ ሲያጣ አትዩት!!

ብልህ ሰዉ ነገዉን ዛሬ ይወስናል !!ይፋጠኑ !!
DMC Real Estate Plc
በለቡ መብራት 65,395ካሬ ላይ ያረፈ ሰፊ እጅግ ዉብ መንደር
ቻድ ኢንባሲ CDC በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል !
በምቹ አከፋፈል 10%  560.ሺ ቅድመ ክፋያ ጀምሮ
የንግድ ሱቆች G.floor -3rd floor
ከstudio 56.6ካሬባለ1,2,3--4መኝታ 186ካሬ .በተለያየ የካሬ አማራጭ

በሚገርም ወብ Design የቀረበ
በዘመነ ፈጣን በተቀላጠፈ ቴክኖሎጂ አልሙንየም ፎርም ወርክ የሚሰራ

የግንባታ አይነት
ከፊል ግንባታ SF
ሙሉ ግንባታ  FF
ሰበር ዜና
ዛሬ አዳዲስ 2ኛ floor ጀምሮ ዝቅተኛቤት floor ጥቂት ቤቶች  አዉተናል ይፋጠኑ,ይምረጡ  !!
ብሮትን አሰሩት፤ በኢትዮጵያ ትልቁ አዋጭ የሆነው የሪል እስቴት ቢዝነስ ነው፡፡

"ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ...."
ቤት በመግዛት ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ሐብት ያፍሩ፣ገንዘብዎትን ከግሽበት ይጠብቁ፤እጥፍ ድርብ ትርፍ ያግኙ!
ዲኤም ሲ ሪል እስቴት/Dmc Real Estate

ለበለጠ መረጃ /ለሳይት ጉብኝት
ይጀዉሉልን!
0988684477/0910649363

https://wa.me/c/251988684477
9.8K views07:46
Buka / Bagaimana
2024-05-20 11:18:50 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በኦንላይን ለሚወስዱ የተዘጋጀ መለማመጃ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
9.0K viewsedited  08:18
Buka / Bagaimana