Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

Alamat saluran: @ethiopian_digital_library
Kategori: Pekerjaan
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 65.82K
Deskripsi dari saluran

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru 11

2024-05-03 12:33:38
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን እንመኛለን!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
16.3K viewsedited  09:33
Buka / Bagaimana
2024-05-02 18:14:29 ማስታወቂያ

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 - 21/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ለማኔጅመንት (Management)ና አካውንቲንግ (Accounting) ተፈታኞች የonline (zoom) ቱቶሪያል አዘጋጅተናል::

ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ፈጥነው ይመዝገቡ::

Link: https://t.me/+_atK7wICcpEwOThk
14.9K viewsedited  15:14
Buka / Bagaimana
2024-05-02 16:46:31 የመምህራን ደመወዝ በመከፈሉ በወላይታ ዞን የተቋረጠው ትምህርት ተጀምሯል

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን፣ ላለፉት ሁለት ወራት ያህል ታጉሎ የቆየው የመምህራን ደመወዝ በመከፈሉ የተቋረጠው የመማር ማስተማር ሒደት መቀጠሉን፣ የክልሉ የመምህራን ማኅበር አስታወቀ፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ዐማኑኤል ጳውሎስ፣ ችግሩ ተፈጥሮባቸው የነበሩት የአንድ ከተማ አስተዳደር እና የ20 ወረዳዎች ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ መመለሳቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

ለደኅንነታቸው ስለሚሰጉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ውስጥ የሚያስተምሩ የአካባቢ ሳይንስ መምህር፣ ለሁለት ወር ያህል የታጎለባቸው ደመወዝ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በመከፈሉ ከሚያዝያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. አንሥቶ ተቋርጦ የቆየው ትምህርት መቀጠሉን በስልክ ተናግረዋል፡፡

መምህራን ወደ ሥራቸው የተመለሱት፣ የሁለት ወር ደመወዛቸው በከፊል እና ሙሉ በሙሉ በመከፈሉ መኾኑን፣ ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁት ሌላው መምህር ገልጸዋል፡፡ #VOA

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
15.4K viewsedited  13:46
Buka / Bagaimana
2024-05-02 14:12:30 እሳት ፣ ውሃ ፣ እውነትና ሃሰት

እሳት፣ ውሃ፣ እውነትና ሃሰት ጓደኞች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ሃሰት በዚህ ጥምረት ደስተኛ ስላልነበረ አንድነታቸውን ማበላሸት ፈልጎ እንዲህ አለ “ለምን ወደ አንድ ስፍራ ተጉዘን እያንዳንዳችን የራሳችንን ግዛት አንመሰርትም? ስለዚህ ተነስተን አብረን እንጓዝ፡፡” ሁሉም በሃሳቡ ተስማምተው ሲሄዱ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሀሰት ወደ ውሃ ጠጋ ብሎ “እሳት ሣሩን፣ ደኑንና ቁጥቋጦውን የሚያቃጥል ቀንደኛ ጠላታችን ስለሆነ ለምንድነው ከእርሱ ጋር ግዛት ፍለጋ የምንሄደው?” አለው፡፡

ውሃም “ታዲያ ምን ብናደርግ ይሻላል?” አለ፡፡ ሃሰትም ቀበል አድርጎ “ልንገድለው እንደሚገባ ግልፅ ነው፡፡ እሳትን የማጥፋት ብቸኛ ኃይል ያለህ ደግሞ አንተ ነህ፡፡ እናም ቁጭ ሲል ጠብቀህ እላዩ ላይ ራስህን በመርጨት አጥፋው፡፡” አለው፡፡ ውሃም “ራሴን መሬቱ ላይ ከረጨሁ ተመልሼ ውሃ መሆን አልችልም፡፡” አለ፡፡

ሀሰትም “ችግር የለውም፡፡ ተረጭተህ እንዳትበታተን የተወሰኑ ድንጋዮች በዙሪያህ አኖርና በኋላ እሰበስብሃለሁ፡፡” አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ያልጠረጠረው እሳት መጥቶ ቁጭ ሲል ውሃው አንድ ጊዜ በላዩ ላይ ሲረጭ ሃሰት ድንጋዮች ዙሪያውን አድርጎ ውሃውን ከሰበሰበውና እሳትን ካስወገዱ በኋላ አብረው መጓዝ ጀመሩ፡፡ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሃሰት ውሃውን “ለምን እዚህ ገደል አፋፍ ላይ ቁጭ ብለህ በተፈጥሮ ውበት አትዝናናም?” አለው፡፡

ውሃም አፋፉ ላይ ቁጭ ሲል ሃሰት ቀስ ብሎ ተነስቶ ውሃ የተቀመጠባቸውን ድንጋዮች ከስሩ ሲለቅማቸው ውሃው በመረጨት በዚያው ተበታትኖ ጠፋ፡፡

በመጨረሻም ሃሰት እውነትን ማጥፋት ነበረበትና ወደ አንድ ትልቅ ተራራ በተቃረቡ ጊዜ ሃሰት እውነትን ከተራራው ግርጌ ቁጭ በል ብሎት ከተራራው አናት ላይ ትልቅ አለት ቁልቁል በመልቀቅ እውነትን ሊጨፈልቀው ሲል እውነት ቀልጠፍ ብሎ ማምለጥ በመቻሉ አለቱ ተንከባሎ ሲፈረካከስ ከውስጡ አልማዝ፣ ወርቅና ልዩ ልዩ የከበሩ ማዕድናት ወጡ፡፡ ሃሰትም የእውነትን አስከሬን ሊመለከት በመጣ ጊዜ እነዚህን ሁሉ የከበሩ ድንጋዮች አየ፡፡

እናም “እነዚህ ሁሉ ከየት መጡ?” ብሎ ጠየቀ፡፡ እውነትም “አለቱ እላዬ ላይ ሲወድቅ እነዚህ ማዕድናት ወጡ፡፡” አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ሃሰት “አሁን ደግሞ እኔ ከተራራው ግርጌ ልቀመጥና አንተ አለቱን በላዬ ላይ ልቀቅብኝ፡፡” አለው፡፡ እናም እውነት ወደ ተራራው ጫፍ ወጥቶ ትልቅ አለት ወደታች በለቀቀ ጊዜ አለቱ የሃሰት አናት ላይ አርፎ ሃሰትን ጨፈላልቆ ገደለው፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
15.8K viewsedited  11:12
Buka / Bagaimana
2024-05-02 10:15:45
ዲቪ 2025 ቪዛ ሎተሪ ውጤት ከሁለት ቀን በሗላ ይለቀቃል

2025 Entrant Status Check

DV-2025 Entrants may enter their confirmation information through the link below starting at noon (EDT) on May 4, 2024.

DV-2025 Entrants should keep their confirmation number until at least September 30, 2025.

Link: https://dvprogram.state.gov/

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.1K viewsedited  07:15
Buka / Bagaimana
2024-04-29 15:54:54 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ይሰጣል

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3 እስከ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ 6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት #Entrance2016

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.0K viewsedited  12:54
Buka / Bagaimana
2024-04-28 13:33:30
ልዩ የመምህራንና የትምህርት አመራር የአቅም ማጎልበቻ የክረምት ስልጠና

ትምህርት ሚኒስቴር በቀን14/08/2016 ዓ.ም በቁጥር፡- 10/242/897/2016 በተፃፈ ደብዳቤ በትምህርት ስርዓቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ መኆኑን በመግለጥ ከዚህም መካከል የመምህራንንና ትምህርት አመራሮችን አቅም ለመገንባት በክረምት ልዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና መርሃ ግብርን በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ለመጀመሪያ ዙር የሚሰጥ ይሆናል::

በመሆኑ በዚህም ዙር በእንግሊዝኛ፣ ሂሳብ፣ በፊዚክስ፣ በኬሚስትሪ እና ባዮሎጂ የትምህርት መስኮች በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመምህርነትና በትምህርት አመራርነት በመስራ ላይ ያሉት ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡ #የአዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር_ትምህርት_ቢሮ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.4K viewsedited  10:33
Buka / Bagaimana
2024-04-26 14:06:43 የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር ይሰጣል

12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰኔ ወር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።

የዩንቨርሲቲ መውጫ ፈተና ሰኔ መጀመሪያ ከተሰጠ በኋላ የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ይሰጣል።

በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ከ670 ሺህ በላይ ተማሪዎች ምዝገባ እንዳደረጉ መገለፁም ይታወሳል፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተናው፤ ዘንድሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ለማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ለእያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ አይዘነጋም፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.3K viewsedited  11:06
Buka / Bagaimana
2024-04-25 17:04:15
የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የኦሮሚያ ትምህርት ትራንስፎርሜሽን ታክስ ፎርስ ተቋቁሞ እየተሰራ ነው - ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ

በክልሉ በርካታ ጎበዝ ተማሪዎችን ለማፍራት የተለያዩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተገንብተው እየተሰራ እንደሚገኝ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ገልፀዋል፡፡

ቢሮው የኦሮሚያ ልማት ማህበር ካስገነባው ልዩ አዳሪ ትምህርት ፣ በክልሉ መንግስት ከተገነቡ ቦረና ሆስቴል እና ዶዶላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ልምድ በመቅሰም ተማሪዎችን ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ በመመልመል በልዩ ትምህርት ቤቶች አንዲማሩ እያደረገ እንደሚገኝም ነው ኃላፊው ያነሰቱ፡፡

ከዚህ በፊት የዩንቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ከ600 በላይ ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ቁጥር ውስን እንደነበር የገለፁት ዶ/ር ቶላ በክልሉ ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ቁጥርን ለማሳደግ ልዩ አዳሪ እና ልዩ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት የመማር ማስተማር ስርዓቱ እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

በዚህም አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ገልጸው ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት እና ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በማስፋፋት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ የሚችሉ ተማሪዎችን በብዛት ለማፋራት ትኩረት ተሰጥቶችት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.5K viewsedited  14:04
Buka / Bagaimana
2024-04-25 15:48:44
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሥር የሚገኙት ዘንዘልማ እና ሰባታሚት ካምፓሶች በፀጥታ ችግር ምክንያት መዘጋታቸውን ሪፖርተር ዩኒቨርሲቲውን በመጥቀስ ዘግቧል

በሁለቱ ካምፓሶች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ የግብርና፣ የጤና፣ የጂኦሎጂ እና የዲዛስተር ማኔጅመንት ተማሪዎች የፀጥታው ችግር እስኪቀረፍ ከተማ ውስጥ ባሉ ካምፓሶች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማድረጉን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ብርሃኑ ገድፍ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዘንዘልማ እና በሰባታሚት ካምፓሶች ውስጥ ይማሩ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች ከተማ ውስጥ ያሉ ካምፓሶች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው፡፡

ዘንዘልማ እና ሰባታሚት ካምፓሶች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የተኩስ ድምፅ በየጊዜው እንደሚሰማ የገለፁት ም/ፕሬዝዳንቱ፤ በተማሪዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከአንድ ወር በፊት ወደተለያዩ የተቋሙ ካምፓሶች እንዲዘዋወሩ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በከተማዋ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች ውስጥ በቂ ቦታ በመኖሩ ተማሪዎቹ ምንም ዓይነት መጉላላት ሳይደርስባቸው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ከሁለቱ ካምፓሶች ውጪ በሌሎች ካምፓሶች ላይ ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር እንደሌለ ም/ፕሬዝዳንቱ ገልጸው፤ በባህር ዳር ከተማ ካለው አንፃራዊ ሰላም አኳያ በርካታ ተማሪዎች ምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

ከሁለቱ ካምፓሶች ውጪ አለመረጋጋቱ የተሻሻለ ቢሆንም፤ አልፎ አልፎ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰሙ ተማሪዎቹ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ የዘንድሮ ተመራቂዎች የምረቃ ቀን መቼ እንደሆነ እስካሁን እንዳልተነገራቸውም አክለዋል፡፡ #ሪፖርተር

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.7K views12:48
Buka / Bagaimana