Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

Alamat saluran: @ethiopian_digital_library
Kategori: Pekerjaan
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 65.82K
Deskripsi dari saluran

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru 12

2024-04-23 10:36:16 የሪሚዲያል ፈተና

የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ፕሮግራም ፈተና ከሰኔ 3 -14 በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል!

#Remedial

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.8K viewsedited  07:36
Buka / Bagaimana
2024-04-23 10:18:29
ሚያዝያ 15 (April 23) ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቀን

የዓለም መጽሐፍ ቀን በየዓመቱ ሚያዝያ 15 ይከበራል።

ሚያዝያ 15 ለዓለምአቀፍ የመጽሐፍ ቀንነት የተመረጠበት ምክንያት የዊልያም ሼክስፒር እና ስፔናዊው የታሪክ ጸሐፊ ኢንካ ጋርሲላሶ ዴ ላ ቬጋ የሞቱበት ቀን በመሆኑ እንደመታሰቢያ እንዲሆን ነው።

በእዚህ ቀን በዓለምአቀፍ ደረጃ በተለይ ወላጆች ለልጆቻቸው መጻሕፍትን በስጦታ መልክ በመስጠት ያከብሩታል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.0K viewsedited  07:18
Buka / Bagaimana
2024-04-22 16:05:43
በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተሰሩ ሞዴሎች የቁንጅና ዉድድር ሊካሄድ ነዉ

እስካሁን በተለመዱት የቁንጅና ዉድድሮች ሴቶች ባላቸዉ ቁንጅና ተወዳድረዉ የቁንጅና አክሊል ይሸለሙ ነበር፡፡ አሁን ግን ውድድሩ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤት በሆኑ ሞዴሎች መካከል ነው ይለናል የዴይሊ ሜይል ዘገባ፡፡

"ሚስ ኤ.አይ" የተሰኘዉ የቁንጅና ውድድር በዓለም አቀፉ የኤ.አይ ፈጣሪዎች ሽልማት አዘጋጆች (The World AI Creator Awards) ተሰናድቷል፡፡ ዓላማውም በዓለም አቀፍ ደረጃ የኤ.አይ ፈጠራ ስራ ዉስጥ ለሚሳተፉ አካላት እውቅና ለመስጠት ብሎም ለማበረታታት ነው። ሰዉ መሳይ ሮቦት ሞዴሎችን በመስራት ላይ ያሉ አካላት ምርቶቻችዉን በማስመዝገብ በውድድሩ ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

ተወዳዳሪ ሞዴሎቹ የተለያዩ የውበት እና መሰል መለኪያዎችን ያካተተ አጠቃላይ ግምገማን እንዲያልፉ ይደረጋል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያላቸዉ ተፅዕኖ ፈጣሪነትና እዉቅናም ከግምት ውስጥ የሚገባ ይሆናል።

ውድድሩ ኤሚሊ ፔሌግሪኒ እና አይታና ሎፔዝ በተባሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተሰሩ ሁለት ታዋቂ ሞዴሎችን ጨምሮ በአራት ባለሙያዎች ይዳኛል። የዉድድሩ አሸናፊዎች የሚጋሩት 20 ሺ ዶላር የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን ከቁንጅና መለኪያ ዘዉድ ጋር አሸናፊዋ ትቀዳጃለች፡፡

ምንጭ:- የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.4K viewsedited  13:05
Buka / Bagaimana
2024-04-22 15:56:04 በ2016 ዓ.ም 8.8 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል - ትምህርት ሚኒስቴር

በፀጥታ ችግር ምክንያት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች 8.8 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት 8,977 ትምህርት ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 6,483 ሙሉ በሙሉ ዝግ መሆናቸውን በሚኒስቴሩ 'ትምህርትን በአደጋ ማስቀጠል' ባለሙያ ንጋቱ አበበ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

ሚኒስቴሩ እና የክልል ትምህርት ቢሮዎች በጋራ በመሆን የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማስቀጠል ጥረት ቢያደርጉም፤ አሁንም በተለያዩ ቦታዎች በቀጠሉት ግጭቶች ምክንያት ችግሩን ለመፍታት አስቸጋሪ እንደሆነ ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡

የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ የመማር ማስተማር ሒደቱን ለማስቀጠል የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ባለሙያው ጥሪ አቅርበዋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.1K viewsedited  12:56
Buka / Bagaimana
2024-04-21 12:48:06
500 ብር የመክፈል እና ደረሰኝ የማቅረብ ግዴታ

የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የአገልግሎት 500 ብር የመክፈል እና ደረሰኝ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው - ትምህርት ሚኒስቴር


ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ #ExitExam #Exit_Exam

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
12.9K viewsedited  09:48
Buka / Bagaimana
2024-04-21 11:33:38 #Inbox

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ከመጣ ጀምሮ ለዩኒቨርሲቲ መምህራን በተለያዩ ስብሰባዎች የተናገራቸው ወይም ቃል የገባቸው ግን ፈፅሞ ያልተገበራቸው፦

1. ለዩኒቨርሲቲ መምህራን ክብራቸውና ደረጃቸውን የሚመጥን በቂ የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግ ጠንክረን እንሰራለን።

2. ለሶስተኛ ድግሪ (ፒኤችዲ) ተማሪዎች በቂ የምርምር ገንዘብና ጥቅማ ጥቅም ጭማሪ ይደረጋል አይደለም ጭማሪ ሊያደርግ ጭራሽ GAT ፈተና ለመፈተን 1000 ብር መመዝገቢያ ብሎ የሚከፈለኝ ወርሃዊ ደመወዝ ወር እስከ ወር አላደረሰኝም ከሚል መምህር ገንዘብ መሰብሰብ ጀመረ።

3. ከክልልና ከዞን ከተማ መስተዳድር አካላት ጋር ተነጋግረን ለዩኒቨርሲቲ መምህራን ቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጥ እናደርጋለን።

4. ብዙ ዓመት በማስተርስ ያስተማረ መምህርና አዲስ ማስተርስ የያዘ መምህር በፍፁም ተመሳሳይ ደመወዝ መከፈል የለባቸውም፤Horizontal እና Vertical career structure ተግባራዊ እንዲሆን እናደርጋለን።

5. ከአሁን በኋላ የዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሹመት በብሄርና በ recommendation ሳይሆን በእውቀት (merit-based) እንዲሆን እናደርጋለን።

6. ከአሁን በኋላ ለመማር ማስተማር የሚያገለግሉ ግብአቶች  በበቂ ሁኔታ በዩኒቨርሲቲዎች እንዲሟሉ ይደረጋል።

የማይተገብሩትን ቃል መግባት እዳ ብቻ ሳይሆን ታማኝነትንና አመኔታን ያሳጣል።

To: የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር

CC: ለፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

From: ሙሳ ሙሃባ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.1K viewsedited  08:33
Buka / Bagaimana
2024-04-20 12:37:54 የ2016 ዓ.ም መውጫ ፈተና ከሰኔ 14 - 21/2016 ዓ.ም ይሰጣል

ትምህርት ሚኒስቴር ሚያዝያ 9/2016 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ፤ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 14 እስከ 21/2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ #MOE

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.5K viewsedited  09:37
Buka / Bagaimana
2024-04-18 14:19:56
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደውን አለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤ ሊያስተናግድ እንደሆነ ተገለፀ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጉባኤውን ለማስተናገድ የተመረጠው በአፍሪካ አካል ጉዳተኞችን ማዕከል ያደረጉ በርካታ ጥናት እና ምርምሮችን ጨምሮ እንደ አህጉርም ከፈተኛ ቁጥር ያላቸው አካል ጉዳተኞችን ማስተማር በመቻሉ መሆኑ ተገልጿል።

15ኛው አለማቀፍ የምልክት ቋንቋ ጉባኤ በመጪው አመት ወርሀ ጥር የሚካሄድ ሲሆን ከመላው ዓለም የተውጣጡ ከ600 በላይ ተሳታፊዎች የሚታደሙበት እንደሚሆን ይጠበቃል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.9K viewsedited  11:19
Buka / Bagaimana
2024-04-16 14:31:01 የሚኒስትሪ መልስ መስጫ ወረቀት አጠቃቀም መመሪያ ለተማሪዎች

1.የተማሪዎች መለያ ቁጥር እና የትምህርት ዓይነት መለያ ቁጥር ለእያንዳንዳቸው በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ውስጥ ከላይ ወደ ታች መፃፍ አለበት፡፡

2.በተፃፈው መለያ ቁጥር ፊት ለፊት የተፃፈውን ቁጥር የያዘውን ክብ ብቻ መጠቆር አለበት፡፡

3.ተማሪዎች የመረጡትን መልስ ትይዩ በተሰጠው ክብ ላይ በትክክል ማጥቆር አለባቸው፡፡

4.ተማሪዎች ያጠቆሩትን መልስ መቀየር ቢፈልጉ መጀመሪያ ያጠቆሩትን ክብ በደንብ ማጥፋት አለባቸው፡፡

5. በአንድ ረድፍ ከአንድ በላይ ክብ ማጥቆር የተከለከለ ነው፡፡

6) ለመፃፍ እና ለማጥቆር ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ምንም አይነት ፅሁፍም ሆነ ጭረት ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡

7.ለመፃፍ ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ተፅፎ ወይም ትንሽ ጭረት እና ነጥብ ከተገኘ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ሙሉ  በሙሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

8.መልስ መስጫ ኮርነር ላይ ያሉትን አራት ጠርዞች መንካትም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

9. ተፈታኞች የመልስ መስጫ ወረቀታቸውን በንፅህና መያዝ አለባቸው ማለትም እንዳይቆሽሽ፣ እርጥበት  እንዳይነካው፤ እንዳይቀደድ እና እንዳይታጠፍ መጠንቀቅና ሙሉ ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.3K viewsedited  11:31
Buka / Bagaimana
2024-04-14 09:57:27 ተማሪውና መምህሩ

አንድ ሂሣብ የማይገባው ተማሪ ነበር፡፡ አንድ ቀን ታዲያ መምህሩ ስለመቀነስ እያስተማሩ ሳለ ተማሪው ስላልገባው መምህሩ ምሳሌ ይሰጡት ጀመር፡፡

እንዲህም አሉት “አምስት በጎች በረት ውስጥ ቢኖርህና አንዱ ሾልኮ ቢያመልጥ ስንት ይቀርሃል?”

ተማሪውም “መምህር እረ ምንም አይቀረኝ” አላቸው፡፡

መምህሩም በመበሳጨት “ይህ እንዴት አይገባህም?” ብለው ጮሁበት፡፡

ተማሪውም “ኧረ መምህር የበጎችን አመል ጠንቅቄ ነው የማውቀው አንዲቷ ካመለጠች ሌሎቹም ተከትለዋት ነው የሚጠፉት” አላቸው፡፡

በዚህም ጊዜ መምህሩ ሲስቁ ክፍሉ በሙሉ ሳቀ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
15.8K viewsedited  06:57
Buka / Bagaimana