Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

Alamat saluran: @ethiopian_digital_library
Kategori: Pekerjaan
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 64.49K
Deskripsi dari saluran

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru 14

2024-01-17 18:16:23
#Ads

For general knowledge questions and answers please join our YouTube channel!

https://www.youtube.com/@hablen/videos
13.1K views15:16
Buka / Bagaimana
2024-01-17 09:50:49 ለፍቅረኛው ፈተና ለመፈተን ሲል ሊፒስቲክ እና ሜክአፕ ተሰርቶ ወደ መፈተኛ ክፍል የገባው አፍቃሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

አንድ ህንዳዊ በፑንጃብ ዩኒቨርሲቲ በሴት ጓደኛው ስም ሊፒስቲክ፣ ሜካፕ እና የሴት ልብስ ለብሶ ፈተና ለመውሰድ ሲሞክር ተይዟል።

በፑንጃብ ፋሪድኮት አውራጃ የሚገኘው የባባ ፋሪድ የጤና ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ባለስልጣናት በቅርቡ አንድ ህንዳዊ ወጣት የሴት ጓደኛዋ ወክሎ ሁለገብ የጤና ባለሙያዎችን ፈተናን ለመፈተን ፍቅረኛውን በመምሰል እና የውሸት ሰነዶችን ሲጠቀም ተይዟል። የፋዚልካ አንግሬዝ ሲንግ በመባል የሚታወቀው ይህው ወጣት ጥር 7 ቀን በኮትካፑራ በሚገኘው የፈተና ማእከል ውስጥ  ሙሉ የሴት አልባሳት ለብሶ፣ ሜክአፕ እና ሊፕስቲክ ተቀብቶ ይገኛል።

በተጨማሪም በፍቅረኛው የሴት ስም ሰነዶችን ይዞም ነበር። የማስመሰል ሂደቱ የመፈተኛ ጣቢያ ሰራተኞቹን ሊያታልል ቢችልም መረጃ ቋቱ ውስጥ ካለው ጋር የያዘው የገፅታ ግን የባዮሜትሪክ ስካነሮችን ማታለል ባለመቻሉ በቁጥጥር ስር ውሏል። ግለሰቡ ወደ ፈተና አዳራሽ ቢገባም በማመልከቻ ቅጹ ላይ ያለው የፍቅረኛውን የፓራምጄት ካኡር ምስል ከእርሱ ፊት ጋር በመሳሪያው ስላልተመሳሰለ የዩኒቨርሲው ባለስልጣናት ይጠራጠራሉ።

ህንድ ኤክስፕረስ እንደዘገበው በባዮሜትሪክሱ መሰረት በመዝገቦቹ ውስጥ ከተቀመጠው ምስል ጋር አይዛመዱም። በዚህም አንግሬዝ ሲንግ ፍቅረኛው የሆናችውን ካውርን እንዳስመሰለ ለማወቅ ተችሏል። በፓራምጄት ካውር ስም የተሰራ የውሸት ካርድ፣ የፈተና ካርድ በፍተሻ ወቅት ተገኝቶበታል። መጀመሪያ ላይ የዩንቨርስቲው ሰራተኞች አንግሬዝን ወደ ቤቱ እንዲሄድ ሸኝተውት የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ በበርካታ ክሶች በምርመራ ላይ ይገኛል።

ያለ ፍቅረኛውው ካውር ፍቃድ በእሷ ቦታ ፈተናውን መስሎ መፈተን ስለማይችል ከሲንግ ጋር በማሴር ወንጀል ተከሷል።የ34 ዓመቷ ፓራምጄት ካውር ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ፈተና ወስዳ ማለፍ ስላልቻለች የ26 ዓመቱ ፍቅረኛዋ አንግሬዝ ፈተናውን በመውሰድ ፍቅረኛውን ለማሳለፍ ተስፋ አድርገው ነበር። ወጣቱ መጀመሪያ ላይ ከካኡር ጋር ዘመድ እንደሆኑ ለፖሊስ ተናግሮ ነበር፣ ነገር ግን ይህ ውሸት መሆኑን ፖሊስ ባደረገው ምርመራ አረጋግጧል።

አንግሬዝ እንደ ሴት መስሎ የሚታይበት ምስል በህንድ ማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።እኤአ በ2015 ዓመት በተመሳሳይ በካዛኪስታን አንድ ሰው ለፍቅረኛው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ለመፈተን በማሰብ ተመሳሳዩን ድርጊት ማድረጉ ይታወሳል። #ዳጉ_ጆርናል
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.3K viewsedited  06:50
Buka / Bagaimana
2024-01-17 09:49:42
13.0K views06:49
Buka / Bagaimana
2024-01-17 09:29:09 ዲላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች

በ2016 ዓ.ም ዲላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥር 23 እና 24/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ (ኦዳያኣ ካምፓስ) በሚገኘው ሬጂስትራር ጽ/ቤት

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ 3x4 የቅርብ ጊዜ ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ፣አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ፡፡#DillaUniversity

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.9K viewsedited  06:29
Buka / Bagaimana
2024-01-16 15:07:22
12.9K views12:07
Buka / Bagaimana
2024-01-16 09:49:20
#Update

የሪሚዲያል ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ጊዜ በቅደም ተከተል

#Today

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ: በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳቹህ ለሪሚዲያል ፕሮግራም በ2016 የትምህርት ዘመን ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 27 እና 28/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ: በ2016 ዓ.ም በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥር 15 እና 16/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ: በ2016 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥር 20 እና 21/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ጭሮ ከተማ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ካምፓስ

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ: በ2016 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥር 20 እና 21/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ትምህርት ጥር 22/2016 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

N.B:
ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሰርትፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ከ9ኛ አስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ የቅርብ ጊዜ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ብርድ ልብስ፣ አንሶላና ትራስ ጨርቅ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.2K viewsedited  06:49
Buka / Bagaimana
2024-01-15 17:22:25 23 Best Apps for Students to Study Efficiently

App Blocker Apps: Stay Focused, AppBlock
Best Planner Apps: myHomework Student Planner, Google Calendar
Best Task Managers: Todoist, Microsoft To Do, Any.do
Best Note-Taking Apps: OneNote, Google Keep, Evernote
Best Word Processor Apps: Google Docs, Microsoft Word
Best Dictionary Apps: Merriam-Webster Dictionary, Oxford Dictionary of English
Best Learning Apps: Khan Academy, Google Translate, Duolingo
Best Organizer Apps: Office Lens, Adobe Scan
Best Cloud Storage Apps: Google Drive, Dropbox
Best Calculator Apps: GeoGebra Graphing Calculator, RealCalc

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
12.8K viewsedited  14:22
Buka / Bagaimana
2024-01-15 15:11:38 አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) የአለማችንን 40 በመቶ ሰራተኞች ስራ ሊያሳጣ እንደሚችል ተነገረ

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የአለማችን 40 በመቶ ሰራተኞችን ስራ ሊነጥቅ እንደሚችል የአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ገለጸ።
ተቋሙ ይፋ ባደረገው አዲስ ጥናት ቴክኖሎጂው ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ተንብዩዋል። የአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክርስታሊና ጆርጂየቫ “አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) የሰው ልጆችን ስራ ከመንጠቅ ባሻገር ኢፍትሃዊነትን ያባብሳል” ብለዋል። 

ቴክኖሎጂው ከባድ ማህበራዊ ቀውስ ከማስከተሉ በፊትም ፖሊሲ አውጪዎች መፍትሄዎችን እንዲያዘጋጁ ነው ያሳሰቡት።
በዳቮስ እየተካሄደ በሚገኘው የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ይሄው የሰው ልጆችን ስራ ይነጥቃል የሚል ስጋት የቀረበበት አርቲፊሻል ኢንተርለጀንስ ዋነኛ የምክክር አጀንዳ ሆኗል። የአለም የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) በዚሁ ስብሰባ ይፋ ያደረገው ጥናትም ቴክኖሎጂውን በስፋት መጠቅም የሚያስችል መሰረተ ልማት በዘረጉት የበለጸጉት ሀገራት ሰው ሰራሽ አስተውሎት እስከ 60 በመቶ ሰራተኞች ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል ብሏል።

ቴክኖሎጂው በታዳጊ ሀገራት ደግሞ 26 በመቶ ስራዎች ላይ ተጽዕኖው ሊያሳርፍ አልያም ስራን ሊነጥቅ እንደሚችል በአይኤምኤፍ ተገምቷል። ባደጉትና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት መካከል ያለው ቴክኖሎጂውን ጥቅም ላይ የማዋል ልዩነት የሀገራቱን የእድገት ልዩነት እያሰፋው እንደሚሄድ ነው የሚጠበቀው። ቴክኖሎጂው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው እና ረጅም አመት ያገለገሉ ሰራተኞችን ከስራ በማሰናበት ከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ እንዳያስከትል ከወዲሁ ዝግጅት ይደረግ ሲል ነው አይኤምኤፍ ያሳሰበው።

የበለጸጉት ሀገራት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ይዞት ከመጣው በረከት በብዙው ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ቢጠበቅም ሚሊየኖች ከስራ ገበታቸው ሊሰናበቱ ይችላሉ የሚሉ ጥናቶች በተደጋጋሚ ወጥተዋል። በዳቮሱ ምክክር የሰው ሰራሽ አስተውሎት ምን ያህል ስራን እያቀለለ እና ውጤታማነትን እያሳደገ እንደሚገኝ ቢነሳበትም ስጋቱ አይሏል።

የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ባለፈው ወር የመጀመሪያውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቁጥጥር ህግ ማጽደቃቸው ይታወሳል። በያዝነው የፈረንጆቹ አመት በህብረቱ ፓርላማ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ህግ በዘርፉ የሚደረገውን ፉክክር ጤናማ ከማድረግ ባለፈ ተጠያቂነትን ያሰፍናል ተብሏል። አሜሪካ፣ ብሪታንያ እና ቻይናም የራሳቸውን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቁጥጥር ህግ ለማጽደቅ በሂደት ላይ ናቸው። #አልአይን

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.9K viewsedited  12:11
Buka / Bagaimana
2024-01-14 15:35:54 ሪሚዲያል ተማሪዎች

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ: በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችው ለሪሜዲያል ፕሮግራም በ2016 የትምህርት ዘመን ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ጥር 20 እና 21/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ማሳሰቢያ፡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በስም Alphabet
በተፈጥሮ ሳይንስ ከ A-H Alphabet በዋና ግቢ
በተፈጥሮ ሳይንስ ከ I-Z Alphabet በዱራሜ ካምፓስ
በማኅበራዊ ሳይንስ ከ A-M Alphabet በዋና ግቢ
በማኅበራዊ ሳይንስ ከ N-Z Alphabet በዱራሜ ካምፓስ

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ መርሐግብር የ2014 ባች ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር ምዝገባ ጥር 07 እና 08/2016 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ገልጿል። ጥር 09/2016 ዓ.ም ብቻ በቅጣት ምዝገባ እንደሚደረግ ተገልጿል።
ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ጽ/ቤት መልዕክት ይመልከቱ።

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ: በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 16 እና 17/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

መቱ ዩኒቨርሲቲ: በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን በመቱ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 20 እና 21/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
የምዝገባ ቦታ: ስማችሁ ከ A-B የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ እና ማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ምዝገባችሁ በበደሌ ካምፓስ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.8K viewsedited  12:35
Buka / Bagaimana
2024-01-14 13:08:14 Top 10 Technologies to Learn in 2024

1. Blockchain
2. Augmented Reality or Virtual Reality
3. IoT
4. 5G Technology
5. Machine Learning
6. Cybersecurity
7. Edge Computing
8. Biotechnology
9. Quantum Computing
10. Artificial Intelligence
Source: Internet
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
12.9K viewsedited  10:08
Buka / Bagaimana