Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

Alamat saluran: @ethiopian_digital_library
Kategori: Pekerjaan
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 65.20K
Deskripsi dari saluran

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru 17

2024-02-25 09:08:07
የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የከተማ አቀፍ ፈተና

ከላይ እንደተገለጸው ለ2016 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የከተማ አቀፍ ፈተና ጥያቄዎችን በተመለከተ ፈተናው የሚዘጋጀው በሁለቱም የክፍል ደረጃ ብቻ ሲሆን ይህም ማለት ከ6ኛ እና ከ8ኛ ክፍል ብቻ የሚወጣ መሆኑን ተገንዝባችሁ ትምህርት ቤቶች በዚህ ልክ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡

ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ዋናው ፈተናችሁ የሚወጣው ከ8ኛ ክፍል ብቻ ነው የ7ኛ ክፍልን አይጨምርም። የ6ተኛ ክፍልም በተመሳሳይ የ5ኛ ክፍልን አያካትትም::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.1K viewsedited  06:08
Buka / Bagaimana
2024-02-24 10:54:24 ይሄን እያየ መጪው ትውልድ ለትምህርት ዋጋ ይሰጣል ማለት የማይታሰብ ነው

ሰሞኑን ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ወሎ ደሴ ጎራ ብዬ ነበር ፤ ድሮ አስረኛ ክፍል የወደቀው ጓደኛዬን አገኘሁትና አንድ ሁለት እንበል ብሎ Golden Gate የሚባል ቅንጡ ሆቴል ውስጥ ይዞኝ ገባ ፤ ኑሮ እንደት ነው ስለው እኔ ጋር እጅግ በጣም አሪፍ ነው አለኝ አንተስ ጋር ሲለኝ ምንም አይልም ሶስተኛ ድግሪዬን (ፒኤችዲዬን) እየተማርኩ ነው ስለው ቤት ሰራህ? መኪና ገዛህ ወይ ሲለኝ ኸረ ቤትም አልሰራሁም፣መኪናም አልገዛሁም፣የሚከፈለኝ ወርሃዊ ደመወዝ እራሱ ወር እስከ ወር አድርሶኝ አያውቅም ስለው እጅግ በጣም አዝኖ እናንተ (ሌክቸረሮች ማለቱ ነው) አንደኛ ድግሪ፣ሁለተኛ ድግሪና ሶስተኛ ድግሪ እያላችሁ ትቆጥራላችሁ እኛ (ነጋዴዎች) ደግሞ አንድ ቤት፣ሁለት ቤት፣ሶስት ቤት፣አንድ ቦታ፣ሁለት ቦታ፣አንድ መኪና፣ሁለት መኪና፣ሶስት መኪና ወዘተ እያልን እንቆጥራለን አለኝ ፤ ለማንኛውም እኔ ሶስት መኪናና ሶስት መኖሪያ ቤት አለኝ ሲል አጫወተኝ ፤ የበላነውንና የጠጣነውን ወጭ ከፍሎ አይዞህ ነገ ሌላ ቀን ብሎ አፅናንቶኝ Golden Bus ትኬት በ 1030 ብር ቆርጦ፤ከደሴ ወደ አዲስ አበባ አሳፈረኝ።

ድሮ የተማረ (መንግሥት ሰራተኛ) ከሚከፈለው ወርሃዊ ደመወዝ አጠራቅሞ ቦታ ገዝቶ ቤት ሰርቶ ጥሩ ኑሮ ይኖር ነበር፤የአሁኑ መንግሥት ሰራተኛ ግን አይደለም ከደመወዙ አጠራቅሞ ቦታ ገዝቶ ቤት ሊሰራ ይቅርና የሚከፈለው ወርሃዊ ደመወዝ ወር እስከ ወር በአግባቡ አያደርሰውም።

ይሄን እያየ መጪው ትውልድ ለትምህርት ዋጋ ይሰጣል ማለት የማይታሰብ ነው።
ሙሳ ሙሃባ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.6K viewsedited  07:54
Buka / Bagaimana
2024-02-24 10:00:58
"ሰውን እኩል በማታይ ሀገር ውስጥ መኖር አልፈልግም" ያለው የሜድስን ተማሪ ከሞት ተርፏል

እምሩ ሙስጠፋ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የሜዲስን ተማሪ ሲሆን በማህበራዊ ትስስር ገፁ "ቤተሰቦቼን አደራ፣ እኔ ሰውን እኩል በማታይ ሀገር ውስጥ መኖር አልፈልግም፣ እኔ መኖር እፈልጋለው መኖር ግን አልተፈቀደልኝም፣ ባልፈጠር ይሻለኝ ነበር ባልፈጠር እኔንም ቤተሰቤንም አላስቸግርም" በማለት ራሱን እንደሚያጠፋ ከገለፀ በኋላ በጓደኞቹ፣ በፖሊስ እና በዩኒቨርሲቲው ጥረት ራሱ ላይ ጉዳት ሳያደርስ ተይዟል። ቤተሰብ እስኪመጣ በነቀምት ከተማ ፖሊስ እንደሚቆይ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሃሰን ዩሱፍ (PHD) የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.1K viewsedited  07:00
Buka / Bagaimana
2024-02-23 17:08:44 በአዲስ አበባ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በሰኔ መጀመሪያ ላይ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ

ይህንንም ተከትሎ በዘንድሮ ዓመት በአዲስ አበባ ለስድስተኛ ክፍል 86 ሺህ 691 ተማሪዎች እንዲሁም ለስምንተኛ ክፍል 88 ሺህ 28 ተማሪዎች በከተማ አቀፍ ፈተናው ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

ተማሪዎች ለፈተናው ብቁ እንዲሆኑ በሥነ-ልቦና የማዘጋጀት፣ ከኩረጃ ነጻ የሆነ አስተሳሰብ እንዲይዙ እና በራስ መተማመን እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል።

ተማሪዎች በስልክና በመሰል የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ እንዲቀነሱና ትምህርት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ወላጆች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መነገሩን ኢዜአ ዘግቧል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.7K viewsedited  14:08
Buka / Bagaimana
2024-02-23 16:49:12 በአዲስ አበባ ያሉ አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ፈተናዎችን እንዳይሰጡ ተጥሎባቸው የቆየው እገዳ እንደተነሳላቸው ተነግሯል፡፡

በአዲስ አበባ ያሉ አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የሀገሪቱን ስርዓተ ትምህርት እንዲከተሉ በተደጋጋሚ ቢነገሩም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው፤ ተማሪዎቹ የ6ተኛ፣ 8ተኛ እና 12ተኛ ክፍል ፈተናዎች እንዳይወስዱ አግጃለሁ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ተናግሮ ነበር፡፡

በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚማሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እያሉ፤ የሌላ ሀገር ስርዓተ ትምህርት ተምረው የሀገሪቱን ፈተና መስጠት አግባብነት እንደሌለውም ቢሮው መናገሩ ይታወሳል፡፡

ሸገርም ጉዳዩ መፍትሄ አገኘ ወይ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮን የጠየቀ ሲሆን፤ ትምህርት ቤቶቹ ለተማሪዎቻቸው ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት ማስተማር ጀምረዋል ተብሏል፡፡

በመሆኑም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ጨምሮ ክልላዊ ፈተናዎችን እንዳይሰጡ ተጥሎባቸው የቆየው እገዳ እንደተነሳላቸው ተነግሯል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስራ ዘጠኝ አለምአቀፍ ትምህርት ቤቶች አሉ ተብሏል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.0K viewsedited  13:49
Buka / Bagaimana
2024-02-23 13:33:24 ውጤታማ የአጠናን ዘዴ

በትምህርት ህይወታችን ስኬታማ መሆን ከፈለግን በመጀመሪያ ለምንማረው ትምህርት ፍቅርና ፍላጎት እንዲኖረን ማድረግ አለብን።

ለመምህራን ያለን አመለካከትም አዎንታዊ መሆን ይገባል።

ሌላው መሰረታዊ ነገር ክፍል ውስጥ የሚሰጠውን ትምህርት በሚገባበማስታወሻይዞ ከልብ መከታተል ነው።

ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ካልሆነ በስተቀር ከክፍል ፈጽሞ መቅረት የለብንም። በተደጋጋሚ ከክፍል የምንቀር ከሆነ የሚሰጠው ትምህርት ተከታታይነትና

ቀጣዩ ስራችን የተለያዩ ማጣቀሻ መጽሐፍት መፈለግና ማንበብ ይኖርብናል።

በመጨረሻም የመምህሩን የማስተማር ስልት፣ የትኩረት አቅጣጫውን፣ የፈተና አወጣጥ ዝንባሌውን የመገመት ብቃት ልናዳብር ይገባል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.6K viewsedited  10:33
Buka / Bagaimana
2024-02-22 18:27:27 For English Tips, Quizzes,Tutorials and Materials!
@ethiopian_english_academy
12.7K views15:27
Buka / Bagaimana
2024-02-21 17:57:01
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
15.9K viewsedited  14:57
Buka / Bagaimana
2024-02-21 11:09:05 በአራት ቢሊዮን ብር አዳሪ ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ ነው

በአራት ቢሊዮን ብር አዳሪ ትምህርት ቤቶች ሊገነባ መኾናቸውን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ በምዕራብ አማራ ዞኖች ከሚገኙ የትምህርት መሪዎች ጋር በወቅታዊ የትምህርት ሥራዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኀላፊ ኢየሩስ መንግሥቱ ክልሉ በዚህ ዓመት አራት ቢሊዮን ብር በመመደብ በደብረ ታቦር፣ በፍኖተ ሰላም እና በሰቆጣ ከተሞች አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ማጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡ በክልሉ 12ኛ ክፍልን ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች መካከል ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በአዳሪ ትምህርት ቤቶች ነው ያሉት ኀላፊዋ ይህን በጎ ተሞክሮ ለማስፋፋት በቢሮው በኩል እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።

በአዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ለትምህርታቸው ሰፊ ጊዜ እንዲሰጡ እና እርስ በእርስ እንዲተጋገዙ ስለሚረዳ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ በዚህ በኩልም የትምህርት ጥራትን ማምጣት ስለሚቻል መንግሥት ይህን ዘርፍ አጠናክሮ እየሠራበት ይገኛል ነው ያሉት፡፡

ወይዘሮ ኢየሩስ አክለውም ትምህርት ሚኒስቴር በራሱ ወጭ ደግሞ አንድ አዳሪ ትምህርት ቤት የሚገነባበት ቦታ እንዲሰጠው መጠየቁን ጠቁመዋል። በመኾኑም የባሕር ዳር ከተማ  አሥተዳድር የቦታ መረጣ እና ዝግጅት ሥራውን ወደ ማጠናቀቁ ደረጃ መድረሱን ተናግረዋል።
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
16.0K viewsedited  08:09
Buka / Bagaimana
2024-02-21 11:07:08 Do you enjoy reading this channel?

Perhaps you have thought about placing ads on it?

To do this, follow three simple steps:

1) Sign up: https://telega.io/c/Ethiopian_Digital_Library
2) Top up the balance in a convenient way
3) Create an advertising post

If the topic of your post fits our channel, we will publish it with pleasure.
13.8K views08:07
Buka / Bagaimana