Get Mystery Box with random crypto!

ብቻ ምን መሰለህ ትንሽ ስራ ስትጀምር የሚተችህ መብዛቱ አንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር እንደነገረኝ ከ | Ethiopian Digital Library

ብቻ ምን መሰለህ ትንሽ ስራ ስትጀምር የሚተችህ መብዛቱ

አንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር እንደነገረኝ ከሆነ ከ7 አመት በፊት ተጨማሪ ተጓዳኝ ስራ ልጀምር ብዬ ዲሽ መግጠም ጀመርኩ አለ።

ታዲያ በሰዓቱ የገጠመኝ ነገር ይገርማል አለኝ። ምን መሰለህ የስራ ባህላችን እጅግ መቀየር አለበት! የስራ ባልደረቦቼ ሳይቀሩ አንተ እኮ ይህን ስራ መስራት የለብህም ምን ሆነህ ነው ይሉኝ ነበር። ለአንተ ይሄ አይመጥንህም ተው አታሰድበን እስከ ማለት ደርሰውም ነበር።

አንድ ቀን ደግሞ እንዲሁ ተደውሎልኝ ስሄድ የተማሪዎቼ ቤት ኖሯል ከዚያማ ከላይ ወጥቼ እየሰራሁ ቲቹ ነው እኮ እየሰራ ያለው ደሞዙ አንሶት ነው አሁን ይህን የሚሰራ ሲሉ ሰማዋቸው።

ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰፈር የሚያውቀኝ ሰው አንተ መምህርም አይደለህ ለምንድን ነው ከአቧራ ጋር የምትታገለው አሁን የመምህር ደሞዝ አልበቃህ ብሎህ ነው ሲል የዲሽ ጥገናውን እንዳቆም አሳስቦኝ ነበር።

ብቻ ምን መሰለህ ትንሽ ስራ ስትጀምር የሚተችህ መብዛቱ አለኝ!

እና አሁን የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ከፍቼ ጥሩ የሚባል ስራ እየሰራሁ እገኛለሁ በመምህርነቱም እየሰራሁ ነው ። 

ያው እንደምታውቀው ቅርብ ጊዜ ኑሮው እጅግ በመናሩ ብዙ መምህራን ጓደኞቼ ሲቸገሩ አያለሁ እኔ ግን ብዙ ጫና ቻል አድርጌ በመስራቴ ኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም ችያለሁ ።

ሳጠቃልልህ የስራ ባህላችን በጣም መስተካከል አለበት የሚሰራን ሰው ለማደናቀፍ  የሚደረጉ ብዙ ጥረቶች አሉ ቢቻል ብናበረታታው ካልተቻለ ደግሞ ዝም ብን ሲል GA ሃሳቡን አጠቃሏል ።

እናንተስ ምን ትላላችሁ?

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library