Get Mystery Box with random crypto!

በጆሮ ማዳመጫ(Earphone) እያዳመጡ መንገድ ማቋረጥ 80 ብር ያስቀጣል የአዲስ አበባ ከተማ | Ethiopian Digital Library

በጆሮ ማዳመጫ(Earphone) እያዳመጡ መንገድ ማቋረጥ 80 ብር ያስቀጣል

የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 395/2009 መሠረት በእግረኞች የሚፈፀሙ ጥፋቶች ላይ ቁጥጥር በማድረግ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ አስታውቋል ።

ደንቡ ቀደም ባለው ጊዜ የወጣ ይሁን እንጂ በአፈፃፀሙ ዳተኝነት ሲታይበት ቆይቶ በአሁኑ ወቅት በእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ስህተት ሳቢያ የሚከሰት የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ተብሏል ። 

በዚህም መሠረት ደንቡን የሚተላለፉ እግረኞች ከ40 እስከ 80 ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚቀጡ በባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የዲጂታል ሚዲያ ከፍተኛ ባለሙያ አ/ቶ መኳንንት ምናሴ ተናግረዋል ።

ከእግረኖች ደንብ መተላፎች መካከል ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርጉ መንገድ ማቋረጥ ፣ ለተሽከርካሪ በተፈቀደ መንገድ ላይ ያለበቂ ምክንያት መቆም ፣ የእግረኛ መንገድ በሌለበት ቀኝ ጠርዝ ይዞ መጓዝ ፣ ለእግረኛ ተብሎ ከተከለለ መንገድ ውጭ መጓዝ እና በማንኛውም ሁኔታ ለእግረኞች እንቅስቃሴ እንቅፋት መሆን እያንዳንጃቸው በ40 ብር የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጡ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ተለይተው የታጠሩ መንገዶችን ዘሎ ማቋረጥ ፣ በጆሮ ማዳመጫ እያዳመጡ መንገድ ማቋረጥ እንዲሁም እግረኞች እንዳያቋርጡ ክልክል በሆነ የማሳለጫ ወይም የቀለበት መንገድን ማቋረጥ እያንዳንዳቸው የ80 ብር ቅጣት እንደሚያስቀጡ አክለዋል ።

ሆኖም እግረኞች ይህን ተረድተው ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው የተገለፀ ሲሆን ጥፋተኛ ሆኖ የገንዘብ ክፍያ መፈፀም ያልቻለ ሰው ፅዳትን ጨምሮ ተመጣጣኝ ማህበራዊ አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል ተብሏል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library