Get Mystery Box with random crypto!

ዘንድሮ የሚሰጠው ልዩ የክረምት ስልጠና ለ50 ሺህ መምህራን የተዘጋጀ ነው - ትምህርት ሚኒስቴር | Ethiopian Digital Library

ዘንድሮ የሚሰጠው ልዩ የክረምት ስልጠና ለ50 ሺህ መምህራን የተዘጋጀ ነው - ትምህርት ሚኒስቴር

በዘንድሮው ዓመት ለ50 ሺህ መምህራን “ልዩ የክረምት ስልጠና” ለመስጠት፤ “አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን” የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ። በመጪዎቹ ሐምሌ እና ነሐሴ ወራት የሚሰጠው ይህ ስልጠና የቅድመ አንደኛ፣ የአንደኛ ደረጃ እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን አቅም ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 ዓ.ም. የሁለተኛው ሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት ነው። ፕሮፌሰር ብርሃኑ በዚሁ ሪፖርታቸው፤ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ለትምህርት ቤት አመራሮች እና መምህራን ስለሚሰጡ ስልጠናዎች አብራርተዋል።

“በትምህርት ቤት አመራሮች ዙሪያ የአንድ ዓመት ልዩ ስልጠና ስንሰጥ ነበር” ያሉት የትምህርት ሚኒስትሩ፤ በዚህ መርሃ ግብር አማካኝነትም ለ4,580 የትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል። ለመምህራን የሚሰጥ “መደበኛ ስልጠናን” በተመለከተ ደግሞ “ባሉበት ሁኔታ ጥሩ አስተማሪዎች እንዲሆኑ ለማድረግ” ያለመ ስልጠና በመጪዎቹ ሐምሌ እና ነሐሴ ወራት እንደሚካሄድ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ለመምህራን በዩኒቨርስቲዎች ይሰጥ የነበረው ስልጠና ባለፈው ዓመት “ተዘግቶ” እንደነበር ያስታወሱት የትምህርት ሚኒስትሩ፤ ይህ የሆነበት ምክንያት በትምህርት ጥራት ረገድ ችግር በመፈጠሩ እንደሆነ አስረድተዋል። “ሁለት ሳምንት እያስተማሩ፤ ‘ተምረዋል፣ ሰልጥነዋል’ እያሉ እየለቀቁ፤ ከጥራት አኳያ በጣም ብዙ ችግር ገጥሞን ነበር” ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፤ ዘንድሮ የትምህርት ካሌንደሩን በማስተካከል ሁለት ወር ለስልጠና ክፍት መደረጉን አትተዋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library