Get Mystery Box with random crypto!

ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ማርች 8 የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ታሪካዊ መነሻውን ያደረገው የሠራተኞ | Ethiopian Digital Library

ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ማርች 8

የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ታሪካዊ መነሻውን ያደረገው የሠራተኞች አንቅስቃሴን ሲሆን በአሁኑ ወቅት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዕውቅና የተሰው ዓመታዊ በዓል ለመሆን በቅቷል። የክብረ በዓሏ ጅማሮ በአውሮፓውያኑ 1908 ነው በወቅቱ 15 ሺህ የሚሆኑ ሴቶች በኒውዮርክ ከተማ ላይ የሥራ ሰዓት መሻሻል (ማጠር)፣ የተሻለ ክፍያና ሴቶች በምርጫ መሳተፍ አለባቸው በሚል የተቃውሞ ሰልፍ አካሄዱ።

ከአንድ ዓመት በኋላም የአሜሪካ ሶሻሊስት ፓርቲ የመጀመሪያዋን ብሔራዊ የሴቶች ቀን አወጀ። ቀኗን ዓለም አቀፍ የማድረግ ሃሳቡ የመጣው ክላራ ዜትኪን በምትባል ግለሰብ አማካኝነት ነው።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ይፋዊ ሆና መከበር የጀመረችው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ክብረ በዓሏን ማክበር በጀመረባት በአውሮፓውያኑ 1975 ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ "የኋላውን ማክበር፤ የወደፊቱን ማቀድ" በሚል በተባበሩት መንግሥታት ባወጣው መሪ ቃል በ1996 ነበረ በዓለም አቀፍ ደረጃ በደመቀ ሁኔታ የተከበረችው።

ዓለም አቀፏ የሴቶች ቀን የምትዘክረው ሴቶች በማኅረበሰቡ የደረሰባቸውን ጭቆናን ተቋቁመው በፖለቲካውና በምጣኔ ሀብቱ ያገኙትን ትሩፋት ትዘክራለች። ክብረ በዓሏ መሰረቷ ፓለቲካዊ ዓመፅ ሲሆን በአሁንም ወቅት በዓለም ላይ የሰፈነውን የተዛባ የሥርዓተ-ፆታ ኃይል ሚዛንን ለማስተካከል በተለያዩ ሰልፎችና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ትዘከራለች።

ዓለም አቀፍ የወንዶች ቀን የሚባል አለ?

አዎ አለ! ቀኑም የሚከበረው ኖቬምበር (ኅዳር) 19 ነው።
ዕለቱ መከበር የጀመረው ከአውሮፓውያኑ 1990ዎቹ በኋላ ቢሆንም ግን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዕውቅና የለውም። በዓለም ላይ ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በ80 አገራት ይከበራል።

ዕለቱም ወንዶች በዓለም ላይ ያመጧቸውን አዎንታዊ እሴቶች፣ ለቤተሰባቸውና ለማኅበረሰቡ እያደረጉት ያለውን አስተዋፅኦ ይዘክራል። ከዚህም በተጨማሪ አርዓያ የሚሆኑ ወንዶችን ማሳየትና በወንዶች ጤንነት ላይም ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library