Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

Alamat saluran: @ethiopian_digital_library
Kategori: Pekerjaan
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 65.82K
Deskripsi dari saluran

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru 19

2024-02-24 10:00:58
"ሰውን እኩል በማታይ ሀገር ውስጥ መኖር አልፈልግም" ያለው የሜድስን ተማሪ ከሞት ተርፏል

እምሩ ሙስጠፋ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የሜዲስን ተማሪ ሲሆን በማህበራዊ ትስስር ገፁ "ቤተሰቦቼን አደራ፣ እኔ ሰውን እኩል በማታይ ሀገር ውስጥ መኖር አልፈልግም፣ እኔ መኖር እፈልጋለው መኖር ግን አልተፈቀደልኝም፣ ባልፈጠር ይሻለኝ ነበር ባልፈጠር እኔንም ቤተሰቤንም አላስቸግርም" በማለት ራሱን እንደሚያጠፋ ከገለፀ በኋላ በጓደኞቹ፣ በፖሊስ እና በዩኒቨርሲቲው ጥረት ራሱ ላይ ጉዳት ሳያደርስ ተይዟል። ቤተሰብ እስኪመጣ በነቀምት ከተማ ፖሊስ እንደሚቆይ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሃሰን ዩሱፍ (PHD) የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.1K viewsedited  07:00
Buka / Bagaimana
2024-02-23 17:08:44 በአዲስ አበባ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በሰኔ መጀመሪያ ላይ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ

ይህንንም ተከትሎ በዘንድሮ ዓመት በአዲስ አበባ ለስድስተኛ ክፍል 86 ሺህ 691 ተማሪዎች እንዲሁም ለስምንተኛ ክፍል 88 ሺህ 28 ተማሪዎች በከተማ አቀፍ ፈተናው ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

ተማሪዎች ለፈተናው ብቁ እንዲሆኑ በሥነ-ልቦና የማዘጋጀት፣ ከኩረጃ ነጻ የሆነ አስተሳሰብ እንዲይዙ እና በራስ መተማመን እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል።

ተማሪዎች በስልክና በመሰል የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ እንዲቀነሱና ትምህርት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ወላጆች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መነገሩን ኢዜአ ዘግቧል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.7K viewsedited  14:08
Buka / Bagaimana
2024-02-23 16:49:12 በአዲስ አበባ ያሉ አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ፈተናዎችን እንዳይሰጡ ተጥሎባቸው የቆየው እገዳ እንደተነሳላቸው ተነግሯል፡፡

በአዲስ አበባ ያሉ አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የሀገሪቱን ስርዓተ ትምህርት እንዲከተሉ በተደጋጋሚ ቢነገሩም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው፤ ተማሪዎቹ የ6ተኛ፣ 8ተኛ እና 12ተኛ ክፍል ፈተናዎች እንዳይወስዱ አግጃለሁ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ተናግሮ ነበር፡፡

በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚማሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እያሉ፤ የሌላ ሀገር ስርዓተ ትምህርት ተምረው የሀገሪቱን ፈተና መስጠት አግባብነት እንደሌለውም ቢሮው መናገሩ ይታወሳል፡፡

ሸገርም ጉዳዩ መፍትሄ አገኘ ወይ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮን የጠየቀ ሲሆን፤ ትምህርት ቤቶቹ ለተማሪዎቻቸው ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት ማስተማር ጀምረዋል ተብሏል፡፡

በመሆኑም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ጨምሮ ክልላዊ ፈተናዎችን እንዳይሰጡ ተጥሎባቸው የቆየው እገዳ እንደተነሳላቸው ተነግሯል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስራ ዘጠኝ አለምአቀፍ ትምህርት ቤቶች አሉ ተብሏል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.0K viewsedited  13:49
Buka / Bagaimana
2024-02-23 13:33:24 ውጤታማ የአጠናን ዘዴ

በትምህርት ህይወታችን ስኬታማ መሆን ከፈለግን በመጀመሪያ ለምንማረው ትምህርት ፍቅርና ፍላጎት እንዲኖረን ማድረግ አለብን።

ለመምህራን ያለን አመለካከትም አዎንታዊ መሆን ይገባል።

ሌላው መሰረታዊ ነገር ክፍል ውስጥ የሚሰጠውን ትምህርት በሚገባበማስታወሻይዞ ከልብ መከታተል ነው።

ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ካልሆነ በስተቀር ከክፍል ፈጽሞ መቅረት የለብንም። በተደጋጋሚ ከክፍል የምንቀር ከሆነ የሚሰጠው ትምህርት ተከታታይነትና

ቀጣዩ ስራችን የተለያዩ ማጣቀሻ መጽሐፍት መፈለግና ማንበብ ይኖርብናል።

በመጨረሻም የመምህሩን የማስተማር ስልት፣ የትኩረት አቅጣጫውን፣ የፈተና አወጣጥ ዝንባሌውን የመገመት ብቃት ልናዳብር ይገባል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.6K viewsedited  10:33
Buka / Bagaimana
2024-02-22 18:27:27 For English Tips, Quizzes,Tutorials and Materials!
@ethiopian_english_academy
12.7K views15:27
Buka / Bagaimana
2024-02-21 17:57:01
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
15.9K viewsedited  14:57
Buka / Bagaimana
2024-02-21 11:09:05 በአራት ቢሊዮን ብር አዳሪ ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ ነው

በአራት ቢሊዮን ብር አዳሪ ትምህርት ቤቶች ሊገነባ መኾናቸውን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ በምዕራብ አማራ ዞኖች ከሚገኙ የትምህርት መሪዎች ጋር በወቅታዊ የትምህርት ሥራዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኀላፊ ኢየሩስ መንግሥቱ ክልሉ በዚህ ዓመት አራት ቢሊዮን ብር በመመደብ በደብረ ታቦር፣ በፍኖተ ሰላም እና በሰቆጣ ከተሞች አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ማጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡ በክልሉ 12ኛ ክፍልን ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች መካከል ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በአዳሪ ትምህርት ቤቶች ነው ያሉት ኀላፊዋ ይህን በጎ ተሞክሮ ለማስፋፋት በቢሮው በኩል እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።

በአዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ለትምህርታቸው ሰፊ ጊዜ እንዲሰጡ እና እርስ በእርስ እንዲተጋገዙ ስለሚረዳ ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ በዚህ በኩልም የትምህርት ጥራትን ማምጣት ስለሚቻል መንግሥት ይህን ዘርፍ አጠናክሮ እየሠራበት ይገኛል ነው ያሉት፡፡

ወይዘሮ ኢየሩስ አክለውም ትምህርት ሚኒስቴር በራሱ ወጭ ደግሞ አንድ አዳሪ ትምህርት ቤት የሚገነባበት ቦታ እንዲሰጠው መጠየቁን ጠቁመዋል። በመኾኑም የባሕር ዳር ከተማ  አሥተዳድር የቦታ መረጣ እና ዝግጅት ሥራውን ወደ ማጠናቀቁ ደረጃ መድረሱን ተናግረዋል።
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
16.0K viewsedited  08:09
Buka / Bagaimana
2024-02-21 11:07:08 Do you enjoy reading this channel?

Perhaps you have thought about placing ads on it?

To do this, follow three simple steps:

1) Sign up: https://telega.io/c/Ethiopian_Digital_Library
2) Top up the balance in a convenient way
3) Create an advertising post

If the topic of your post fits our channel, we will publish it with pleasure.
13.8K views08:07
Buka / Bagaimana
2024-02-20 13:06:11
የልጅነት አስተማሪዬ ....የዛሬ ታካሚዬ !!

4ኛ 'ሀ' ክፍል የማልረሳው ትዝታዬ እጅግ የምንወዳት እና የምናከብራት አስተማሪዬ እትዬ ስንታየሁ Sintayehu Mekit!
ከተለያየን 22 አመታት አልፈዋል ፤ 1994፣ የ4ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ።

እስከ 4ኛ ክፍል በሚገባ አስተምራናለች። በወቅቱ እትዬ ስንታየሁ የምታስተምርበት ክፍል መመደብ በጣም እድለኝነት ነበር። ትልቁ የትምህርት መሰረት የሚጣለው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ላይ ባለን ነገር እንደሆነ መቼም የታወቀ ነው። ጥሩ አድርገው አስተምረውን አሁን ላልንበት ደረጃ አድርሰዉናል።

በጣም የገረመኝ ያኔ 4ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ የምቀመጥበትን ቦታ እና ወንበር ሳይቀር አስታዉሳ ስትነግረኝ ፤ ተማሪዎች የሚወዷቸውን መምህራንን በጥልቀት እንደሚያስታዉሷቸዉ ሁሉ መምህራንም ተማሪዎቻቸውን በዚህ ልክ እንደሚያስታዉሱን ሳይ በጣም ተገርሜያለሁ!!

አስተማሪዎቻችን ፈጣሪ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይስጣችሁ !!"
ዶክተር አብርሃም አማረ
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
16.2K viewsedited  10:06
Buka / Bagaimana
2024-02-19 16:37:11 የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመቆጣጠር አስገዳጅ መመሪያ በት/ቤቶች ተግባራዊ ሊደረግ ነው

የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመቆጣጠር አስገዳጅ መመሪያ በትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ጽህፈት ቤት መሪ ስራ አስፈጻሚ ፈቃዱ ያደታ ኤችአይቪ/ኤድስ በሀገር አቀፍ ደረጃ የስርጭት መጠኑ ከ1 በመቶ በታች ቢሆንም በጋምቤላ 4 ነጥብ 5፣ በአዲስ አበባ 3 ነጥብ 4፣ በሐረሪ እና በድሬዳዋ ደግሞ 3 በመቶ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎችና የህብረተሰብ ክፍሎች ስርጭቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በወጣቶች ላይ የመያዝ ምጣኔው እንደታሰበው እየቀነሰ እንዳልሆነም አመልክተዋል፡፡

በተለይም በወጣት ሴቶች፣ ሴተኛ አዳሪዎች፣ የአደንዛዥ እጽ ተጠቃሚዎች፣ ረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፣ የህግ ታራሚዎችና በጎዳና ላይ ንግድ የሚተዳደሩ ሴቶች በይበልጥ ለቫይረሱ ተጋላጭ እንደሆኑም ነው የጠቆሙት፡፡

ቫይረሱን ለመቆጣጠር በትምህርት ቤቶች ላይ በትኩረት ለመስራት አስገዳጅ መመሪያ ለመተግበር ጤና ሚኒስቴር ጥረት እያደረገ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡ ይህም ስለኤችአይቪ ግንዛቤ ለመፍጠር እንዲሁም ሌሎች የመከላከል እና የመቆጣጠር ዘዴዎችን ትኩረት ሰጥቶ ለመተግበር ወሳኝ እንደሚሆንም አንስተዋል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
16.8K views13:37
Buka / Bagaimana