Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ያሉ አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ፈተናዎችን እንዳይሰጡ ተጥሎባቸው የቆየው እገዳ እን | Ethiopian Digital Library

በአዲስ አበባ ያሉ አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ፈተናዎችን እንዳይሰጡ ተጥሎባቸው የቆየው እገዳ እንደተነሳላቸው ተነግሯል፡፡

በአዲስ አበባ ያሉ አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የሀገሪቱን ስርዓተ ትምህርት እንዲከተሉ በተደጋጋሚ ቢነገሩም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው፤ ተማሪዎቹ የ6ተኛ፣ 8ተኛ እና 12ተኛ ክፍል ፈተናዎች እንዳይወስዱ አግጃለሁ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ተናግሮ ነበር፡፡

በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚማሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እያሉ፤ የሌላ ሀገር ስርዓተ ትምህርት ተምረው የሀገሪቱን ፈተና መስጠት አግባብነት እንደሌለውም ቢሮው መናገሩ ይታወሳል፡፡

ሸገርም ጉዳዩ መፍትሄ አገኘ ወይ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮን የጠየቀ ሲሆን፤ ትምህርት ቤቶቹ ለተማሪዎቻቸው ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት ማስተማር ጀምረዋል ተብሏል፡፡

በመሆኑም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ጨምሮ ክልላዊ ፈተናዎችን እንዳይሰጡ ተጥሎባቸው የቆየው እገዳ እንደተነሳላቸው ተነግሯል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስራ ዘጠኝ አለምአቀፍ ትምህርት ቤቶች አሉ ተብሏል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library