በአዲስ አበባ የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በሰኔ መጀመሪያ ላይ እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታወቀ ይህንንም ተከትሎ በዘንድሮ ዓመት በአዲስ አበባ ለስድስተኛ ክፍል 86 ሺህ 691 ተማሪዎች እንዲሁም ለስምንተኛ ክፍል 88 ሺህ 28 ተማሪዎች በከተማ አቀፍ ፈተናው ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል። ተማሪዎች ለፈተናው ብቁ እንዲሆኑ በሥነ-ልቦና የማዘጋጀት፣ ከኩረጃ ነጻ የሆነ አስተሳሰብ እንዲይዙ እና በራስ መተማመን እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል። ተማሪዎች በስልክና በመሰል የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ እንዲቀነሱና ትምህርት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ወላጆች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መነገሩን ኢዜአ ዘግቧል። @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library 14.7K viewsedited 14:08