Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

Alamat saluran: @ethiopian_digital_library
Kategori: Pekerjaan
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 65.82K
Deskripsi dari saluran

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru 23

2024-01-08 10:29:19 የሪሚዲያል ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ጊዜ

ቦረና ዩኒቨርሲቲ በ2016 የሪሚዲያል ፕሮግራም የተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከጥር 1 እና 2/2016 ዓ.ም

አክሱም ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ሪሚዲያል ፕሮግራም የተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከጥር 6 እና 7/2016 ዓ.ም

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ሪሚዲያል ፕሮግራም የተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከጥር 7 እስከ 9/2016 ዓ.ም

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ሪሚዲያል ፕሮግራም የተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከጥር 13 እስከ 15/2016 ዓ.ም

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ሪሚዲያል ፕሮግራም የተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከጥር 15 እና 16/2016 ዓ.ም

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከጥር 15 - 17/2016 ዓ.ም

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከጥር 21-23/2016 ዓ.ም

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከየካቲት7- 8/2016 ዓ.ም

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ የካቲት 07 እና 08/2016 ዓ.ም

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 16 እና 17/2016 ዓ.ም

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከጥር 15 እስከ 17/2016 ዓ.ም

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 16 እና 17/2016 ዓ.ም

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ጥር 16 እና 17/2016 ዓ.ም

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ እሁድ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ጥር 16/2016 ዓ.ም

ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ጥር 16 እና 17/2016 ዓ.ም

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሰርትፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ከ9ኛ አስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ የቅርብ ጊዜ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ብርድ ልብስ፣ አንሶላና ትራስ ጨርቅ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
18.5K viewsedited  07:29
Buka / Bagaimana
2024-01-08 09:54:09 ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና (#Exit_Exam)

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና (#Exit_Exam) የሚሰጥበት ቀን ከጥር 27 - 30/2016 ዓ.ም እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ለውጥ ካለ የምናሳውቅ ይሆናል።

የመጀመሪያው ዙር መዉጫ ፈተና(#Exit_Exam) አጠቃላይ መረጃ!
በአጠቃላይ 150 ሺህ 184 ተማሪዎች ፈተና ወስደዋል።
በአጠቃላይ ከመንግስትም ከግልም ተቋማት 61 ሺህ 54 ተማሪዎች አልፈዋል።
ከመንግሥት ተቋማት 48 ሺህ 632 ተማሪዎች ያለፉ ሲሆን
ከግል ኮሌጅ ተፈታኞች ደግሞ 12 ሺህ 422 ያለፉ ተማሪዎች
የማለፍ ምጣኔ በመቶኛ እንደ አጠቃላይ 40.65% ነዉ።
የማለፍ ምጣኔ በመቶኛ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች 62.7% ሲሆን
የማለፍ ምጣኔ በመቶኛ የግል ኮሌጅ ተማሪዎች ደግሞ 17.2% ነው።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.5K viewsedited  06:54
Buka / Bagaimana
2024-01-06 17:20:49 ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

መልካም በዓል!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
15.4K viewsedited  14:20
Buka / Bagaimana
2024-01-05 18:18:43 Natural Science Contents for Remedial Program

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
18.1K views15:18
Buka / Bagaimana
2024-01-05 18:18:38 Social Science Contents for Remedial Program


@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.2K views15:18
Buka / Bagaimana
2024-01-04 17:16:40
የማካካሻ ትምህርት (Remedial) ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሰጥ

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ማለፊያ ነጥብ ማምጣት ላልቻሉ ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት (Remedial) ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ወስኗል።

በሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ታህሳስ 24/2016 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የማካካሻ ትምህርት ለሚሰጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከው ደብዳቤ ፤ የማካካሻ ትምህርቱ ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲሰጥ ያዛል።

በዚህም ተቋማቱ ከጥር 1 ጀምሮ በቀሩት ወራት ትምህርቱን ውጤታማ በሆነ መንገድ መስጠት እንዳለባቸው ተገልጿል። #MoE

ትምህርት ሚኒስቴር

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.8K viewsedited  14:16
Buka / Bagaimana
2024-01-03 13:22:51 ከቀጣይ አመት ጀምሮ የ8ኛና የ12ኛ ክፍል የፈተና ምዝገባ የሚደረገው በዲጅታል መሆኑ ተገለፀ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከቀጣይ አመት ጀምሮ የፈተና ምዝገባ የማደርገው በዲጅታል ነው ብሏል።አገልግሎቱ በዛሬው እለት ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ጋር በጋራ በሰጠው መግለጫ ነው ይሄን ያስታወቀው።በየአመቱ በሃገር አቀፍ እና የክልል አቀፍ የፈተና ምዝገባዎች ሲደረጉ አገልግሎቱ በርካታ ሚሊየን ብር እንደሚያወጣ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ ተናግረዋል።

አሁን የፈተና አገልግሎቱ የፈተና ምዝግባዎችን በዲጅታል እንዲደረጉ የሚያደርግ በመሆኑ ይሄን ወጪ እንደሚያስቀር አንስተዋል።ይህንንም ማሳካት እንዲቻል በተለያዩ የሃገሪቱ አከባቢዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ለዚህም ከ32 ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞች ተመልምለው ወደ ተለያዩ አከባቢዎች ተደልድለዋል ብለዋል።ተቋሙ የሚሰጠውን አገልግሎት በማዘመን በ2015 ዓ.ም የሙከራ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን አሁን ላይ በሙሉ ኃይል ወደ አገልግሎት መግባቱን ገልጿል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
12.8K viewsedited  10:22
Buka / Bagaimana
2024-01-01 17:06:29 ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በር ለማግኘት እና ለማልማት የሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሊ ላንድ ጋር ፈፅማለች ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ባሂ ሁሉን አካታች የሆነውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

በዚሁ መሠረት ለብዙ ዘመናት ወደብ አልባ ሆና የቆየችው ሀገራችን ከሶማሊ ላንድ ጋር ባደረገችው ስምምነት በሊዝ የወደብ ባለቤት መሆን ችላለች።

Source: EBC

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.2K viewsedited  14:06
Buka / Bagaimana
2023-12-30 18:24:30 ኢትዮጵያን በመወከል ቻይና በተካሄደው ዓለምአቀፍ የሮቦቲክስ ፌስቲቫል ላይ የተሳተፈዉ ኢትዮ-ሮቦቲክስ 3ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ባሳለፍነው ሳምንት በቻይና ዩዥን በተካሄደው ዊልስ ቦት ዓለማቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር ላይ ሃያ አንድ ኢትዮጵያዎያን ታዳጊዎች ሀገራችን ኢትዮጵያን ወክለው በመወዳደር በሦስት ዘርፍ ማለትም በቤስት ኦርጋናይዜሽን አዋርድ፣ በቤስት ቲም አዋርድ እና በሞስት ዲቨሎፕመንት አዋርድ አሸንፈዋል።

ሶስት ሮቦቶችን ይዞ ወደ ቻይና አቅንቶ የነበረው የኢትዮ-ሮቦቲክስ ቡድን በዉድድሩ ከተሳተፉ 27 ሀገራት 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

በአያ ሆቴል በተካሄደው መርሐግብር
ቡድኑ ኢትዮጵያን በመወከል በቻይና ላስመዘገበዉ ውጤት ለቡድኑ አባላት  በኢትዮ-ሮቦቲክስ የእዉቅና ሰርትፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

የኢትዮ-ሮቦቲክስ መስራች እና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰናይ መኮንን፤ የወደፊት ተረካቢ ታዳጊዎች ባስመዘገቡት ውጤት ኢትዮጵያን በዓለም ማስጠራት መቻሉን ተናግረዋል።

ታዳጊዎች መጪዉን ዓለም ተረድተዉ ኢንጂነሮች እና ፕሮግራመሮች እንዲሆኑ ላለፉት 14 ዓመታት ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ጠቁመዉ፤ ድርጁቱ አሁንም ከ200 በላይ ታዳጊዎችን እያሰለጠነ መሆኑን ገልጸዋል።

የአፍሪካ የሮቦቲክስ ሻምፒዮና የፊታችን የካቲት ወር በአዲስ አበባ እንደሚዘጋጅም ስራ አስኪያጁ አስታውቀዋል።

ይህ ድል ለኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካዊያን ታዳጊዎችም ጭምር በሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተተኪዎች እንዲፈጠሩ ትልቅ መነቃቃት የሚፈጥር ነው ተብሏል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.9K viewsedited  15:24
Buka / Bagaimana
2023-12-29 16:38:15
በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪ ጥሪና ትምህርት ማስጀመርን አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

በአማራ ክልል የሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከጥር 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ትምህርት ይጀምራሉ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ክልል በተፈጠረው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች በ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያዉ ወሰነ-ትምህርት ተማሪዎቻቸውን ለመጥራትና መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸዉን ሙሉ ለሙሉ ለመጀመር አልቻሉም ነበር።

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር ከክልሉ ኮማንድፖስት፣ የጸጥታ አደረጃጀቶችና የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ሲያካሂድ ቆይቷል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ፣ የአስሩ ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልሉ ጸጥታ አካላት ትናንት ታህሳስ 18/2016 ዓ.ም በጉዳዩ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን አሁን በክልሉ አንጻራዊ ሰላም የተፈጠረ በመሆኑ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን መጥራትና ማስተማር እንደሚችሉ ውሳኔ ላይ ተደርሷል።

በዚህም መሰረት ከጥር 1/2016 ጀምሮ ባሉ ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ዩኒቨርስቲዎቹ ተማሪዎችን ጠርተው የመማር ማስተማር ስራቸውን ይጀምራሉ።

በመሆኑም በአማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የተመደባችሁ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲዎቹ የሚያደርጉትን ጥሪ እንድትከታተሉ እንገልጻለን።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
15.2K viewsedited  13:38
Buka / Bagaimana