Get Mystery Box with random crypto!

መምህራን ለኑሮአቸው ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱ የትምህርት ጥራት አደጋ ላይ የሚጥሉ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች | Ethiopian Digital Library

መምህራን ለኑሮአቸው ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱ የትምህርት ጥራት አደጋ ላይ የሚጥሉ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እያጋጠሟቸው ነው

ኢትዮጵያውያን ፕሮፌሰሮች በአካዳሚክ ትምህርት የወደፊቱን ጊዜ በመቅረጽ ረገድ ወሳኝ ሚና ቢኖራቸውም ከቀን ሠራተኞች ጋር የሚወዳደር ደመወዝ እያገኙ በከፋ የኑሮ ደረጃ እና ስቃይ ውስጥ እንደሚገኙ ያነጋገርናቸው መምራን ገልፀዋል።

ዶ/ር ታደለ የዶክትሬት ዲግሪ ማዕረግ ያላቸው እና በኢትዮጵያ ዩንቨርስቲ በተባባሪ ፕሮፌሰርነት ደረጃ በማስተማር ላይ ይገኛሉ፣ በመምህራን ህይዎት እየገጠማቸው ያለውን አስከፊ እውነታ አብራርተዋል። “በወር አንድ ረጅሙን የህይዎት ዘመኑን በትምህርት ያለፈ ዶክተር 250 ዶላር ያገኛል፡፡ በአገሬው ምንዛሬ 14000 (አስራ አራት ሽህ ብር) ይጠጋል፡፡ ይህም ቤት ኪራይ ከፍሎ፣ ልጅ አስተምሮ ፣ በልቶ ለማድረ እና ህይዎትን ለመምራት እጅግ አሰቃቂ ድህነት ውስጥ እና የርሃብ ጊዜ እያሳለፍን ነው” ሲል በቁጭት ይናገራሉ፡፡

“በሳምንት አምስት ቀን በመስራት የቀን ደመወዛችን ከ 8 ዶላር ያልበለጠ ሲሆን ይህን በኢትዮጲያ የጉልበት ስራ በመስራት ብቻ በአናጢነትም ሆነ ግንበኛ ከሚያገለግለው ባለሙያ በግማሽ ያነሰ ነው።” ለደህንነት ሲባል ስማቸው የተቀየረው ሌላው መምህር ዶ/ር አበባው የአቶ ታደለን ሀሳብ ይደግፋሉ። “ብዙውን ጊዜ በባዶ ሆዳችን እያስተማርን እንገኛለን፣ በቀን አንድ ጊዜ መመገብ አንችልም” ሲሉ ሀሳቡን ይጋራሉ።

‹‹የገንዘብ ችግሮቻቸውን የሚያባብሰው የኑሮ ውድነቱ፣ በተለይም የቤት ወጪ፣ የልጆች ትምህርት ክፍያ ነው።›› የሚሉት መምህርት ዓለምፀሐይ ደረሶ ‹‹ዘመድ መርዳት እና መጠየቅ ፣ የቅንጦት መሆኑን ጠቅስው ‹እየራበን አናስተምርም› ብለው አድማ መምህራን ለሳምንት በሀገር አቀፍ ደረጃ ቢመቱም የተደረገው ጭማሪ በቀን ሲሳላ ከአንድ ብር ያነሰ የሳንቲም ሂሳብ ነው፡፡›› ከዛ በተሻለ የመምህራንን አመፅ በመፍራት መንግስት ለፕሬዝዳንቶች የቤት አበል ከ300 ፐርሰንት በላይ በመጨመር አፈና ፈፅሞብናል›› ይላሉ፡፡

መምህራቷ አክለውም በአሁኑ ስዓት ኢትዮጵያውያን ፕሮፌሰሮች ባለው የቤት ውድነት በመላ ሀገሪቱ ከመሰረተ ልማት ርቀው ኑሯቸውን ለመግፋት ተገደዋል፡፡ ርካሸ ቤት ለማግኘት በሚልም ‹‹ከከተማ መሠረተ ልማት ውስጥ በሚገኙ እንደ መብራት እና ውሃ ያሉ መሰረታዊ መገልገያዎችን ያሉበት ቤት ለመከራየት ሙሉ ወጭ የሚጠይቅ በመሆኑ፣ መሰረተ ልማት በሌሉበት ደረጃቸውን ያልጠበቁ መኖሪያ ቤቶችን ለመፈለግ ተገደዋል።

በተለይ በአስተማሪዎች ደመወዝ እና በቅርብ ተመራቂዎች መካከል ያለው ልዩነት ጎልቶ ይታያል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር “የቀድሞ ተማሪዎቻችን ከኛ አምስት እና ስድስት እጥፍ የሚበልጥ ገቢ ሲያገኙ ማየት ልጆቻችን የተማሩት ከኛ በላይ እንዲሆኑ የምንወደው እውነት ቢሆንም ፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመምህርነት ዘርፍ ላይ ግን ተስፋ አስቆራጭ እውነት ውስጥ ገብተናል” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“የልጆቼን ትምህርት ቤት ወጪ ለመሸፈን ብቻ መኪናዬን መሸጥ ነበረብኝ፣ ራሴን በሕዝብ ማመላለሻ ለዕለት ተዕለት መጓጓዣ መጠቀም ከጀመርኩ አመታት አልፈዋል” ሲሉ ሌላው ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ መምህር ይናገራሉ፡፡

አነስተኛ ገቢያቸውን ለማሟላት ሲሉ የዩኒቨርሲቲ መምህራን አካዳሚዎችን ትተው በግሉ ሴክተር ውስጥ አትራፊ ወደሚሉት የስራ መደቦችን እየፈለሱ ነው። ነገር ግን ይህ መሰደድ ዋጋ ያስከፍላል፤ የሚሉት የትምህርት ልማት ባለሙያው ዶ/ር ቢምረው በየነ ምክንያቱም አብዛኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መምህራን በትምህርታቸው ከፍተኛ ልህቀት አላቸው ትብለው የተመረጡ እና በምርምር ችግር ፈች ስራዎችን ይሰራሉ ተብለው የሚጠብቁ ናቸው፡፡

ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ምሁራን ለገበያ ፍላጎት አለመታጠቅ ምርታማነት እንዲቀንስ እና በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን ችሎታ እንዲያሳጣ አድርጓል። የትምህርት ተንታኝ የሆኑት አቶ ኃይሉ ጉተማ እንደሚሉት፣ በኢትዮጵያውያን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ላይ እየደረሰ ላለው ያልተፈታ ችግር፣ እጅግ በጣም ብዙ ተግዳሮቶች አስተዋፅዖ ያደርጋሉ።

“ያልዘመኑ የትምህርት አስተዳደራዊ ተግባራት፣ የመምህራን ነፃ ከቦታ ቦታ ዝውውር አለመኖር፣ የአካዳሚክ ነፃነት መገደብ፣ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት እና የመምህራን ማኅበራት በአግባቡ ኃላፊነታቸውን መጣታቸው ችግሩን ያባብሰዋል” ሲሉ ያስረዳል።

አሁን ባለው የመምህራኑ አስቸጋሪ ሁኔታ እና መምህራን ለለውጥ መነሳሳት ያላቸው ታሪካዊ ሚና መካከል ያለው ተመሳሳይነት በተመልካቾች ዘንድ አይጠፋም። የ1966ቱ የኢትዮጵያ አብዮት በከፊል በመምህራን ማኅበራት የተገፋው እንደ ማስጠንቀቂያ መሰረት ሆኖ ያገለግላል። የግጭት ተንታኞች እንደሚሉት ‹‹የኢትዮጵያውያን ፕሮፌሰሮች ቅሬታ ምላሽ አለማግኘቱ፣ ፖለቲካዊ አለመረጋጋትን እና በሀገሪቱ የስርዓት ለውጥ እንዲደረግ ጠሪ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። የኢትዮጵያ ዩንቨርስቲ መምህራን ከኢኮኖሚ ችግር እና ከስርአቱ ጋር በተያያዙ ፈተናዎች እየታገለ ባለበት በአሁኑ ወቅት ችግራቸውን የመቅረፍ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አልተቻልም። ይህን ባለማደረጉ የአካዳሚክ ጥራት ደረጃዎች መሸርሸር ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን መረጋጋት አደጋ ላይ እየጣለ ነው።

Source: https://africanewschannel.org/

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library