Get Mystery Box with random crypto!

ሪሚዲያል ተማሪዎች ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ: በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችው ለ | Ethiopian Digital Library

ሪሚዲያል ተማሪዎች

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ: በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችው ለሪሜዲያል ፕሮግራም በ2016 የትምህርት ዘመን ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ጥር 20 እና 21/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ማሳሰቢያ፡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በስም Alphabet
በተፈጥሮ ሳይንስ ከ A-H Alphabet በዋና ግቢ
በተፈጥሮ ሳይንስ ከ I-Z Alphabet በዱራሜ ካምፓስ
በማኅበራዊ ሳይንስ ከ A-M Alphabet በዋና ግቢ
በማኅበራዊ ሳይንስ ከ N-Z Alphabet በዱራሜ ካምፓስ

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ መርሐግብር የ2014 ባች ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር ምዝገባ ጥር 07 እና 08/2016 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ገልጿል። ጥር 09/2016 ዓ.ም ብቻ በቅጣት ምዝገባ እንደሚደረግ ተገልጿል።
ተጨማሪ መረጃ ከላይ ከተያያዘው የዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ጽ/ቤት መልዕክት ይመልከቱ።

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ: በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 16 እና 17/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

መቱ ዩኒቨርሲቲ: በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን በመቱ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 20 እና 21/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
የምዝገባ ቦታ: ስማችሁ ከ A-B የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስ እና ማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ምዝገባችሁ በበደሌ ካምፓስ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library