Get Mystery Box with random crypto!

ለፍቅረኛው ፈተና ለመፈተን ሲል ሊፒስቲክ እና ሜክአፕ ተሰርቶ ወደ መፈተኛ ክፍል የገባው አፍቃሪ በ | Ethiopian Digital Library

ለፍቅረኛው ፈተና ለመፈተን ሲል ሊፒስቲክ እና ሜክአፕ ተሰርቶ ወደ መፈተኛ ክፍል የገባው አፍቃሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

አንድ ህንዳዊ በፑንጃብ ዩኒቨርሲቲ በሴት ጓደኛው ስም ሊፒስቲክ፣ ሜካፕ እና የሴት ልብስ ለብሶ ፈተና ለመውሰድ ሲሞክር ተይዟል።

በፑንጃብ ፋሪድኮት አውራጃ የሚገኘው የባባ ፋሪድ የጤና ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ባለስልጣናት በቅርቡ አንድ ህንዳዊ ወጣት የሴት ጓደኛዋ ወክሎ ሁለገብ የጤና ባለሙያዎችን ፈተናን ለመፈተን ፍቅረኛውን በመምሰል እና የውሸት ሰነዶችን ሲጠቀም ተይዟል። የፋዚልካ አንግሬዝ ሲንግ በመባል የሚታወቀው ይህው ወጣት ጥር 7 ቀን በኮትካፑራ በሚገኘው የፈተና ማእከል ውስጥ  ሙሉ የሴት አልባሳት ለብሶ፣ ሜክአፕ እና ሊፕስቲክ ተቀብቶ ይገኛል።

በተጨማሪም በፍቅረኛው የሴት ስም ሰነዶችን ይዞም ነበር። የማስመሰል ሂደቱ የመፈተኛ ጣቢያ ሰራተኞቹን ሊያታልል ቢችልም መረጃ ቋቱ ውስጥ ካለው ጋር የያዘው የገፅታ ግን የባዮሜትሪክ ስካነሮችን ማታለል ባለመቻሉ በቁጥጥር ስር ውሏል። ግለሰቡ ወደ ፈተና አዳራሽ ቢገባም በማመልከቻ ቅጹ ላይ ያለው የፍቅረኛውን የፓራምጄት ካኡር ምስል ከእርሱ ፊት ጋር በመሳሪያው ስላልተመሳሰለ የዩኒቨርሲው ባለስልጣናት ይጠራጠራሉ።

ህንድ ኤክስፕረስ እንደዘገበው በባዮሜትሪክሱ መሰረት በመዝገቦቹ ውስጥ ከተቀመጠው ምስል ጋር አይዛመዱም። በዚህም አንግሬዝ ሲንግ ፍቅረኛው የሆናችውን ካውርን እንዳስመሰለ ለማወቅ ተችሏል። በፓራምጄት ካውር ስም የተሰራ የውሸት ካርድ፣ የፈተና ካርድ በፍተሻ ወቅት ተገኝቶበታል። መጀመሪያ ላይ የዩንቨርስቲው ሰራተኞች አንግሬዝን ወደ ቤቱ እንዲሄድ ሸኝተውት የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ በበርካታ ክሶች በምርመራ ላይ ይገኛል።

ያለ ፍቅረኛውው ካውር ፍቃድ በእሷ ቦታ ፈተናውን መስሎ መፈተን ስለማይችል ከሲንግ ጋር በማሴር ወንጀል ተከሷል።የ34 ዓመቷ ፓራምጄት ካውር ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ፈተና ወስዳ ማለፍ ስላልቻለች የ26 ዓመቱ ፍቅረኛዋ አንግሬዝ ፈተናውን በመውሰድ ፍቅረኛውን ለማሳለፍ ተስፋ አድርገው ነበር። ወጣቱ መጀመሪያ ላይ ከካኡር ጋር ዘመድ እንደሆኑ ለፖሊስ ተናግሮ ነበር፣ ነገር ግን ይህ ውሸት መሆኑን ፖሊስ ባደረገው ምርመራ አረጋግጧል።

አንግሬዝ እንደ ሴት መስሎ የሚታይበት ምስል በህንድ ማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።እኤአ በ2015 ዓመት በተመሳሳይ በካዛኪስታን አንድ ሰው ለፍቅረኛው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ለመፈተን በማሰብ ተመሳሳዩን ድርጊት ማድረጉ ይታወሳል። #ዳጉ_ጆርናል
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library