Get Mystery Box with random crypto!

ደግለራሱና ክፉለራሱ በአንድ ወቅት ደግለራሱና ክፉለራሱ አብረው ጉዞ ጀመሩ (የስማቸውም ትርጉም | Ethiopian Digital Library

ደግለራሱና ክፉለራሱ

በአንድ ወቅት ደግለራሱና ክፉለራሱ አብረው ጉዞ ጀመሩ (የስማቸውም ትርጉም ‘መልካም ሰው ይሸለማል’ እና ‘ክፉ ሰው ይቀልጣል’ ማለት ነው፡፡)

እኩለ ቀን ሲሆንም ከአንድ ዛፍ ስር ተቀምጠው የደግለራሱን ምግብ በሉ፡፡ በሚቀጥለውም ቀን ይህንኑ በማድረግ አሁንም የደግለራሱን ምግብ ሲበሉ በሶስተኛውም ቀን ይኸው ተደገመ፡፡ በመጨረሻም የደግለራሱ ምግብ ስላለቀ ደግለራሱ ክፉለራሱን ምግብ እንዲሰጠው ሲጠይቀው ከለከለው፡፡
ክፉለራሱም “አንድ አይንህን አውጣና ምግብ እሰጥሃለው፡፡” አለው፡፡

ከዚያም ደግለራሱ አንድ አይኑን አውጥቶ ምግብ አገኘ፡፡ ከዚያም ጉዟቸውን ቀጥለው በሚቀጥለውም ቀን ክፉለራሱ ምግም አልሰጥም ብሎ ከለከለ፡፡ ደግለራሱ የቀረውን አንድ ዓይኑን አውጥቶ ምግብ ቢያገኝም አሁን ዓይነ ስውር ሆነ፡፡
ክፉለራሱም ጉዞውን ሲቀጥል ደግለራሱ ሌሊቱን ዛፍ ላይ ሊያሳልፍ ወጣ፡፡ በዚህ ጊዜ ሰይጣኖቹ ከዛፉ ስር ይጫወቱ ስለነበረ ስለዛፉ ቅጠሎች የተለያዩ ክፍሎች ሲያወሩ ሰማ፡፡

ከሰይጣኖቹ አንዱ “ይህ የሞት መድኃኒት ነው፡፡” ሲል ሌላኛው ደግሞ “ያኛው የዛፍ ክፍል ደግሞ ለሆድ ጥሩ ነው፡፡” አለ፡፡ ሶስተኛውም ቀበል አድርጎ “ያኛው ደግሞ ለአይነ ስውርነት መድኃኒት ነው፡፡” አለ፡፡ በማግስቱ ጠዋት ሠይጣኖቹ ሲሄዱ አይነ ስውሩ ደግለራሱ ሰይጣኖቹ የጠቀሷቸውን ቅጠሎች ሁሉ መሞከር ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ አይኑ በራ፡፡ ከዚያም የንጉሱ ልጅ አይነ ስውር መሆኗን ሰምቶ ካዳናት በኋላ አገባት፡፡ ደግለራሱ የገበያ ዳኛም ሆነ፡፡

ታዲያ አንድ ቀን ክፉለራሱ ወደ ገበያ መጥቶ ተገናኙ፡፡ “እንዴት ልትድን ቻልክ?” ብሎ ሲጠይቀው ደግለራሱም ታሪኩን በሙሉ አጫወተው፡፡ የገበያውም ዳኛ እንዴት እንደሆነ ነገረው፡፡ በዚህ ጊዜ ክፉለራሱ ሃብታም ሊያደርገው የሚችል ቅጠል የሚያገኝ መስሎት ወደ ዛፉ ሄደ፡፡
በዚያን ጊዜ ሰይጣኖቹ እንደቀድሞው ጊዜ ስለ መድኃኒት እየተወያዩ ሳለ በድንገት ክፉለራሱ ሃብታም የሚያደርገው ቅጠል የትኛው እንደሆነ እንዲያሳዩት ሲጠይቃቸው ከዛፉ ላይ ጎትተው አውርደው ደብድበው ገደሉት፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library