Get Mystery Box with random crypto!

ይሄን እያየ መጪው ትውልድ ለትምህርት ዋጋ ይሰጣል ማለት የማይታሰብ ነው ሰሞኑን ቤተሰብ ለመጠየቅ | Ethiopian Digital Library

ይሄን እያየ መጪው ትውልድ ለትምህርት ዋጋ ይሰጣል ማለት የማይታሰብ ነው

ሰሞኑን ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ወሎ ደሴ ጎራ ብዬ ነበር ፤ ድሮ አስረኛ ክፍል የወደቀው ጓደኛዬን አገኘሁትና አንድ ሁለት እንበል ብሎ Golden Gate የሚባል ቅንጡ ሆቴል ውስጥ ይዞኝ ገባ ፤ ኑሮ እንደት ነው ስለው እኔ ጋር እጅግ በጣም አሪፍ ነው አለኝ አንተስ ጋር ሲለኝ ምንም አይልም ሶስተኛ ድግሪዬን (ፒኤችዲዬን) እየተማርኩ ነው ስለው ቤት ሰራህ? መኪና ገዛህ ወይ ሲለኝ ኸረ ቤትም አልሰራሁም፣መኪናም አልገዛሁም፣የሚከፈለኝ ወርሃዊ ደመወዝ እራሱ ወር እስከ ወር አድርሶኝ አያውቅም ስለው እጅግ በጣም አዝኖ እናንተ (ሌክቸረሮች ማለቱ ነው) አንደኛ ድግሪ፣ሁለተኛ ድግሪና ሶስተኛ ድግሪ እያላችሁ ትቆጥራላችሁ እኛ (ነጋዴዎች) ደግሞ አንድ ቤት፣ሁለት ቤት፣ሶስት ቤት፣አንድ ቦታ፣ሁለት ቦታ፣አንድ መኪና፣ሁለት መኪና፣ሶስት መኪና ወዘተ እያልን እንቆጥራለን አለኝ ፤ ለማንኛውም እኔ ሶስት መኪናና ሶስት መኖሪያ ቤት አለኝ ሲል አጫወተኝ ፤ የበላነውንና የጠጣነውን ወጭ ከፍሎ አይዞህ ነገ ሌላ ቀን ብሎ አፅናንቶኝ Golden Bus ትኬት በ 1030 ብር ቆርጦ፤ከደሴ ወደ አዲስ አበባ አሳፈረኝ።

ድሮ የተማረ (መንግሥት ሰራተኛ) ከሚከፈለው ወርሃዊ ደመወዝ አጠራቅሞ ቦታ ገዝቶ ቤት ሰርቶ ጥሩ ኑሮ ይኖር ነበር፤የአሁኑ መንግሥት ሰራተኛ ግን አይደለም ከደመወዙ አጠራቅሞ ቦታ ገዝቶ ቤት ሊሰራ ይቅርና የሚከፈለው ወርሃዊ ደመወዝ ወር እስከ ወር በአግባቡ አያደርሰውም።

ይሄን እያየ መጪው ትውልድ ለትምህርት ዋጋ ይሰጣል ማለት የማይታሰብ ነው።
ሙሳ ሙሃባ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library