Get Mystery Box with random crypto!

በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተከስቷል በተባለ የኮሌራ በሽታ ከ400 የማያንሱ ተማሪዎች መያዛቸውን በተቋሙ | Ethiopian Digital Library

በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተከስቷል በተባለ የኮሌራ በሽታ ከ400 የማያንሱ ተማሪዎች መያዛቸውን በተቋሙ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ከተከሰተ አንድ ሳምንት ሆኖታል ስለተባለው በሽታም ሆነ ስለደረሰ ጉዳት ከዩኒቨርሲቲው እንዲሁም ከክልሉ ጤና ቢሮ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱን ሬዲዮ ጣቢያው ገልጿል። 

ይሁን እንጂ አስተያየት የሰጡ ተማሪዎች በበሽታው ተይዘው ህክምና ሲደረግላቸው ከነበሩት መካከል አንዳንዶቹ እያገገሙ ይገኛሉ ብለዋል።

በዩኒቨርሲቲው ተከሰተ ስለተባለው ወረርሽኝ ለተማሪዎች በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። በሽታው "በውኃ ብክለት" ወይም "የግል ንፅህና ባለመጠበቅ" የመጣ ነው የሚሉ አስተያየቶች ተሰምተዋል።

በዚህም ምክንያት ተማሪዎች ወደ መመገቢያ አዳራሾች ሲገቡ ለጥንቃቄ እንዲታጠቡ ሲደረግ ነበር ተብሏል።

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች የፊታችን እሑድ እንደሚያስመርቅ ይጠበቃል። #ዶይቼ_ቬለ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library