2024-02-06 12:41:57
በፀጥታ ጉዳይ ጠቅላይ ሚንስተሩ ለፓርላማው ከሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች
የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ አንኳር ጉዳዮች የፖለቲካ ፍላጎትን ለማሳካት የሚኬድባቸው መንገዶች ችግር ያለባቸው መሆኑ ነው፤
ማንኛውም ችግር ሲያጋጥም ያንን ችግር ለመፍታት በንግግር ለመፍታት ያለን ልምምድ እየቀነሰ መምጣትም ሌላው ችግር ነው፤
ለሰላም ለሚደረግን ጉዞ ወጥመድ የሚቀመጥበት ልምምዱም የሰፋ መሆኑ ሌላ ችግር ነው፤
እነዚህ ችግሮች አብዛኛው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማዕከል አድርጎ የሚነሳ አይደለም፤ ቢሆን ኖሮ ለቀይ ባህር እድል ለመፍጠር የምናደርገውን ጥረት ባልተቃወሙት ነበር፤
ታንዛኒያ ከሸኔ ጋር የነበረውን ድርድር ስንጀምር ለመላው ህዝብ ነግረን አሳውቀን ሳንደብቅ ነው፤ ውጤቱ ግን ምንም የሚጨበጥ ስላልሆነ ምንም ማለት አልቻልንም፤
ሸኔ በአስመራ በነበረው ድርድር ቃል የተገባው ሳይፈጸም ቀርቶ ከሆነ ጫካ የገባው፤ እታገላለሁ የሚልለትን ህዝብ ማገትና ማሰቃየት ላይ ነው፤ የራስን ህዝብ እያሰቃዩ እታገልልሃለሁ ማለት ዋጋ የለውም፤
ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ በጠበንጃ ስልጣን መያዝ አይቻልም፤ የሚቻለው በሰላም በንግግር ነው፤
በአማራ ክልል በሁሉም ዞኖች ከከሚሴ በስተቀር ከህዝብ ጋር ለመነጋገር እድል አግኝቻለሁ፤ ጥያቄያቸው የልማት፣ የወሰን ይገባኛል እና የህገ መንግስት ነው፤
በአማራ ክልል ባለፉት አምስት አመታት 3 ሺህ 200 ኪሎሜትር መንግድ ጀምረነ እየሰራን ነው፤
ይህ መንገድ በክልሉ ውስጥ ዞንን ከዞን ወረዳን ከወረዳ ጋር የሚያገናኝ ነው፤
ይህ መንገድ አንድ ሽሮ ፈሰስ የሚባል አይደለምዐ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ነው፤
ከአማራ ክልል የተነሳውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ መንግስት የሄደበትን ርቀት አመላካች ነው፤ በቂ አይደለም፤
ከመንገድ ባሻገር በቱሪዝም መስክም የጎርጎራ ፕሮጀክት በአይነትና በደረጃው የትም ያልተሰራ ፕሮጀክት ሆኖ እየተሰራ ነው፤
የላሊበላን ቅርስም ለማደስ የፈረንሳይን ፕሬዝዳንት ሳይቀር ይዘን ሄደነ አሳይተነ እያሰራን ነው፤ በሰላም ምክንያት ወጣ ገባ ቢልም፤
ፋሲልንም የፈረሰውን ማስጎብኘት ተገቢ አይደለም ብለን፤ ስራውን ለማስጀመር ሙከራ አድረገነ ነበር፤ ነገር ግን በተለያዩ አሉባልታዎች ስራውን አስቁመውታል" ብለዋል።
@
Addis_Mereja
13.7K viewsedited 09:41