Get Mystery Box with random crypto!

Addis መረጃ™

Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™ A
Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™
Alamat saluran: @addis_mereja
Kategori: Berita
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 56.80K
Deskripsi dari saluran

@Addis_Mereja ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹
.
⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬
⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬

መረጃዎችን ለመላክ @Adis_Merejaa_bot

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


Pesan-pesan terbaru 9

2023-12-08 17:22:08
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

ልዩ መልዕክተኛው በኢትዮጵያ ቆይታቸው በፕሪቶሪያ የተደረሰው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ዙሪያ ምክክር ያደርጋሉ ብሏል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ።

በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሚታዩ ግጭቶችም በንግግር እንዲቆሙ፤ በግጭቶች ንጹሃን ዜጎች ለከፋ ችግር እንዳይጋለጡ እና የሰብአዊ መብቶች እንዳይጣሱም ጥሪ እንደሚያቀርቡ ጠቁሟል። ማይክ ሃመር የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) በሱዳን ጦርነት ዙሪያ ከነገ ጀምሮ በጂቡቲ በሚያካሂደው የመሪዎች ጉባኤ ላይም ይሳተፋሉ።

ዘጠነኛ ወሩን በቅርቡ የሚይዘው የሱዳን ጦርና የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ጦርነት ያደረሰው ጉዳት ላይ የሚመክሩት የኢጋድ አባል ሀገራት መሪዎች ተፋላሚዎቹን ለማቀራረብ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም ይወያያሉ ተብሏል። ኢጋድ የኢትዮጵያ፣ ጂቡቲ፣ ኬንያ እና ደቡብ ሱዳን መሪዎችን ያካተተ የአራትዮስ የመሪዎች መፍትሄ አፈላላጊ ቡድን አዋቅሮ በሰኔ ወር በአዲስ አበባ የሱዳን ተፋላሚዎችን መጋበዙ ይታወሳል።

የሱዳን ጦር ተወካይም አዲስ አበባ ቢገኙም ለአርኤስኤፍ ወገንተኛ አስተያየት ሰጥተዋል ያሏቸውን የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በመቃወም በስብሰባው ሳይሳተፉ መቅረታቸውም አይዘነጋም። በቅርቡ በናይሮቢ ጉብኝት ያደረጉት አልቡርሃን ይህን ወቀሳ የሚያላላ ምክክር ማድረጋቸውንም ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግቧል።

@Addis_Mereja
13.3K viewsedited  14:22
Buka / Bagaimana
2023-12-05 20:25:31 የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ቤቲንግ ቤቶች አይዘጉም ሲል አስታወቀ።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳስታወቀው አንዳንድ ግለሰቦች በማህበራዊ ሚዲያ ቤቲንግ ሊዘጋ ነው በማለት የሚያሰራጩት መልእክት ፍጹም ስህተት ነው ብሏል።

አክሎም የስፖርት ውርርድ ጨዋታዎችም ሆነ ሎተሪን በተመለከተ ማንኛውም መረጃ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ማግኘት እንደሚቻል አስተዳደሩ ገልጻል።

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ቤቲንግ " ሊታገድ መሆኑን የሚገልፁ በትክክል ምንጫቸው ያልተገለፁ ፅሁፎች ሲሰራጩ ተስተውሏል።

አንዳንድ ግለሰቦች በማህበራዊ ሚዲያ ቤቲንግ ሊዘጋ ነው በማለት የሚያሰራጩት መልእክት ፍጹም ስህተት መሆኑን እንገልፃለን " ያለው አስተዳደሩ " የስፖርት ውርርድ ጨዋታዎችም ሆነ ሎተሪን በተመለከተ ማንኛውም መረጃ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ብቻ ማግኘት እንደሚገባ አመልክቷል።

ከዚህ ቀደም ከ ' ቤቲንግ / ስፖርታዊ ውርርድ / ' ጋር በተያያዘ ፤ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲታገድ እየሰራ መሆኑን አሳውቆ እንደነበር ይታወሳል።

ሚኒስቴር መ/ቤቱ ፤ ከታዲጊዎች እና ወጣቶች ስብዕና ግንባታ እንዲሁም በተለያየ መንገድ ከሚያስከትላቸው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውሶች አንጻር ነው ዘርፉ ሊታገድ ይገባል በሚል እየሰራ እንደሆነ አሳውቆ የነበረው።

Via Ethio FM
@Addis_Mereja
14.8K viewsedited  17:25
Buka / Bagaimana
2023-12-04 09:54:14
የብርሃን ባንክ ባለአክሲዮኖች የትርፍ ድርሻ ዝቅተኛ በመሆኑ ቅሬታቸዉን ገለፁ!

የብርሃን ባንክ ባለአክሲዮኖች በቅርቡ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት የተገኘው የትርፍ ክፍፍል ዝቅተኛ በመሆኑ ቅሬታቸውን ገለጹ።የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለ2022/23 የሒሳብ ዓመት ከ7 በመቶ በታች የትርፍ ክፍፍል ሐሳብ በማቅረቡ ከፍተኛ ትችት ገጥሞታል። ባለአክሲዮኖች አሁን ያለው ሁኔታ ተቀባይነት እንደሌለው ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ከ16,000 በላይ ባለአክሲዮኖች በተገኙበት የባንኩ 14ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ 15.6 በመቶ የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገልፆ ከዚህ ዉስጥ ለአንድ ባለአክሲዮን የትርፍ ድርሻ 156.2 ብር መሆኑን ተነግሯል ነገር ግን በማዕከላዊ ባንክ ውስጥ ያሉ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣኖች ወደ 6.03 በመቶ ዝቅ ያደረጉት ብድሮች እና ሌሎች ተቀናሾች ምክንያት ነው።

ለተከታታይ ዓመታት የገቢ መጠን እያሽቆለቆለ መምጣቱን እና ከ7 ወደ 6 በመቶ ዝቅ ማለቱ ለጉዳት የሚያጋልጥ መሆኑን በማንሳት አንዳንድ ባለአክሲዮኖች ብስጭታቸውን ገልፀዋል።አንድ ባለአክሲዮን የሙስና አዝማሚያዎች መኖራቸውን በመጥቀስ በባንኩ የሥራ አፈጻጸም ላይ ከዓመት ወደ ዓመት ለውጥ ባለመኖሩ ቅሬታ ማቅረባቸውን ካፒታል ሰምቷል።

ሌላው የባለ አክሲዮኖች ስጋት በአዲስ አበባ 5,400 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሰንጋ ተራ እየተባለ የሚጠራው የዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ እንዲሁም በወላይታ ሶዶ ከተማ ሊገነባ የታቀደው ሌላ ሕንፃ ነው። ባለአክሲዮኖች የእነዚህ ፕሮጀክቶች የረዥም ጊዜ የግንባታ ደረጃ ካፒታልን በማያያዝ እና የባንኩን የፋይናንስ አቋም ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ በመሆኑን ተከራክረዋል።

Via Capital
@Addis_Mereja
16.9K viewsedited  06:54
Buka / Bagaimana
2023-12-03 18:36:04
የኦሮሚያ ክልል “በርካታ” ንጹሃን ለተገደሉበት ጥቃት ሸኔን ተጠያቂ አደረገ!!

የኦሮሚያ ክልል “በርካታ ንጹሃን” ለተገደሉበት ጥቃት የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ሸኔ)ን ተጠያቂ አድርጓል።

በክልሉ አርሲ ዞን ሼካ ወረዳ በሶስት መንደሮች ላይ በተከፈተ ጥቃት በጥቂቱ 36 ሰዎች መገደላቸውን ሬውተርስ ነዋሪዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።

የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ ጥቃቱን የፈጸሙት የሸኔ ታጣቂዎች መሆናቸውን ባወጡት መግለጫ ጠቁመዋል። ሸኔ በወሰደው “ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ ብዙ ዜጎች ገድሏል፤፡ ቤት ንብረታቸውንም አቃጥሏል” ያሉት ሃላፊው፥ ቡድኑ የራሱን የመደራደር አቅም ከፍ ለማድረግ ሰላማዊ ዜጎቸ ላይ ያነጣጠረ እርምጃ መውሰዱን እንደገፋበትም አንስተዋል።

መንግስት በወሰደው እርምጃም በምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ቡኖ በደሌን ለማጥቃትና ለማውደም ሲንቀሳቀስ የነበረው የሸኔ ቡድን ሙትና ቁስለኛ ሆኗል ነው ያሉት።እየተወሰደ ባለው እርምጃ የተደናገጠው የሽብር ቡድኑ በሰላማዊ ዜጎች ላይ አሰቃቂ ጥቃቶችን ማድረሱንም የሽብርተኝነቱ ማሳያ አድርገው አቅርበውታል።

“የሽብር ቡድኑ ለድርድር ይዞ የቀረበው የጋላቢዎቹን አጀንዳ ነው፤ ይህ የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ስለሆነ ተቀባይነት የለውም” ያሉት የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊው፥ ሸኔ ተገዶ ወደ ሰላም እንዲመጣ መንግስት የተቀናጀ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

“የሽብር ቡድኑ ከሽብር ተግባሩ ተቆጥቦ ወደ ሰላማዊ ውይይትና ንግግር ከተመለሰ መንግሥት ለሰላም ሁልጊዜም በሩ ክፍት ነው” ሲሉም ነው አቶ ሃይሉ የተናገሩት። ሸኔ ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ለተነሳው ወቀሳ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።

@Addis_Mereja
14.0K viewsedited  15:36
Buka / Bagaimana
2023-12-02 18:43:46
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለክቡራን ደንበኞቻችን

ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ ከቅዳሜ ህዳር 22 ሌሊት 8፡00 ሰዓት እስከ እሁድ ህዳር 23 ቀን 2016 ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ኢንተርኔት ባንኪንግ እና ሞባይል ባንኪንግን ጨምሮ ሁሉም በኮር ባንኪንግ ሲስተም የሚሰጡ አገልግሎቶች እንደሚቋረጡ አውቃችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

@Addis_Mereja
13.3K viewsedited  15:43
Buka / Bagaimana
2023-11-30 10:09:10 ኤችአይቪን የሚከላከለው መድኃኒት ውጤታማ መሆኑ በጥናት ተረጋገጠ!

ዌልስ ውስጥ በሙከራ ላይ የነበረውና በሰውነት ውስጥ የኤችኤይቪ ቫይረስ ሥርጭትን የሚገታው መድኃኒት ውጤታማ መሆኑ በጥናት ተረጋገጠ።የመድኃኒቱ ውጤታማነት የተረጋገጠው በመላው እንግሊዝ ከተውጣጡ እና በጥናቱ በተካተቱ ከ24 ሺህ በላይ የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎች ላይ ምርመራ ከተካሄደ በኋላ ነው።

በእንግሊዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ፒአርኢፒ የተሰኘውን ይህን መድኃኒት ከሥነ ተዋልዶ ጤና ክሊኒኮች እየወሰዱ ይገኛሉ።ከቼልሲ እና ዌስትሚኒስትር ሆስፒታል ጋር በመሆን የመድኃኒቱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የተደረገውን ሙከራ የመራው የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የጤና ደኅንነት ኤጀንሲ፣ ጥናቱ በገሃዱ ዓለም በዓይነቱ ትልቅ ጥናት መሆኑን ገልጿል።

ጥናቱ ከአውሮፓውያኑ ጥቅምት 2017 እስከ ሐምሌ 2020 ባሉት ጊዜያት እንግሊዝ ውስጥ በሚገኙ 157 የሥነ ተዋልዶ ጤና ተቋማት ላይ ተካሂዷል።ይህ ጥናት ‘ፕሪ ኤክስፖዠር ፕሮፍላክሲስ (ፒአርኢፒ)’ የተባለው መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ማረጋገጫ የሰጠ ሲሆን መድኃኒቱ በኤችአይቪ የመያዝ ዕድልን በ86 በመቶ ይቀንሳል።

በክሊኒክ የተደረጉ ሙከራዎች እንዳመለከቱትም መድኃኒቱ 99 በመቶ ውጤታማ ነው።የዩኬ ጤና ደኅንነት ኤጀንሲ የመድኃኒቱ ውጤታማ መሆን የአገሪቷ መንግሥት በ2030 የኤችአይቪ ሥርጭትን ዜሮ ለማድረስ ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት ይረዳል ብሏል።በጥናቱ ላይ የተሳተፉት የሥነ ተዋልዶ ጤና እና ኤችአይቪ አማካሪ ጆን ሳንደርስ እንዳሉት ሙከራው መድኃኒቱ ኤችአይቪን ለመከላከል ውጤታማ መሆኑን ይበልጥ ያሳየ ነው።

ይህም ቀደም ብለው ከተሠሩ ጥናቶች በበለጠ መድኃኒቱ በሽታውን የመከላከል አቅሙን ለመጀመሪያ ጊዜ አሳይቷል ብለዋል።ትሬንስ ሂጊንስ ኤችአይቪ የተባለው ግብረሰናይ ድርጅትም ጥናቱ መውጣቱን በበጎ ተቀብሎ፤ ነገር ግን ተደራሽነትን ለማስፋት፣ ስለመድኃኒቱ ግንዛቤ ለመስጠት ብዙ ሊሠራ እንደሚገባ ጠቁሟል።

የድርጅቱ የፖሊሲ ጉዳዮች ኃላፊ ደቢ ላይኮክ መድኃኒቱ በመድኃኒት ቤቶች እና በበይነ መረብ (ኦንላይን) ተደራሽ እንዲሆንም ጠይቀዋል።ዶ/ር ሳንደርሰን እንዳሉት ምንም እንኳ ምርምሩ የመድኃኒቱን ውጤታማነት ከማረጋገጡ ባሻገር ጥናቱ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል የሚያስረዱ ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል።

“መጀመሪያ ምን ያህል ሰዎች መድኃኒቱን እንደሚፈልጉ እንዲሁም ለምን ያህል ጊዜ መድኃኒቱን ሲወስዱ እንደቆዩ አናውቅም ነበር። አሁን ላይ ግን መድኃኒቱ ለማን መታዘዝ እንዳለበት ተረድተናል። በመሆኑም ብዙ ሰዎችን ለመድረስ ከክሊኒኮች ጋር መሥራት እንችላለን” ብለዋል ሳንደርሰን።

ፒአርኢፒ ቀደም ብሎ የነበሩትን ቴኖፎቪር ዲሶፕሮክሲል እና ኢምትሪሳይታቢን የተባሉ የኤችአይቪ መድኃኒቶችን የያዘ ሲሆን፣ የኤችአይቪ ቫይረስ ወደ ሰውነት እንዳይገባ እና በሰውነት ውስጥ ከገባም በኋላ ራሱን እንዳያባዛ ያደርጋል።መድኃኒቱ በክኒን መልክ በቀን አንዴ መወሰድ አሊያም ከወሲብ ግንኙነት ቀደም ብሎ መወሰድ ይችላል።

ይህንን መድኃኒት እንደ አውሮፓውያኑ በ2020 በእንግሊዝ በስፋት እንዲሰራጭ የተደረገው ቀደም ብሎ በተሠሩ ጥናቶች ውጤት ላይ በመመሥረት ነበር።አሁን ላይ የጥናቱ ውጤት በላንሴት ኤችአይቪ ላይ የታተመው ሰፋ ያለ ናሙና ስለተወሰደ እና ጥናቱን ሌሎች ተመራማሪዎች ሰፊ ጊዜ ሰጥተው ስለተመለከቱት ነው ተብሏል።

Via BBC
@Addis_Mereja
15.0K viewsedited  07:09
Buka / Bagaimana
2023-11-28 15:02:19
የፈረንሳይ ኦሬንጅ ኩባንያ የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ ከመግዛት ሂደት ራሱን አገለለ

የፈረንሳይ ኦሬንጅ ኩባንያ የኢትዮ ቴሌኮምን 45 በመቶ ድርሻ ከመግዛት ሂደት ራሱን ማግለሉን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ፋይናንስ ሚንስቴር የኢትዮ ቴሌኮምን የ45 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ ማውጣቱ ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎም የፈረንሳዩ ኦሬንጅ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬት ቴሌኮም ኩባንያ የሆነው ኢ ኤንድ የተሰኘው ተቋም የኢትዮ ቴሌኮምን የ45 በመቶ ድርሻ ለመግዛት የመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው አሳውቀው ነበር።

የፈረንሳይና የአረብ ኢምሬት ኩባንያዎች የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ የመግዛት ፍላጎት እንዳላቸው ተገለፀ

የፈረንሳይ ኦሬንጅ ኩባንያ በትናንትናው እለት ባወጣው መግለጫ የኢትዮ ቴሌኮምን 45 በመቶ ድርሻ ከመግዛት ሂደት ራሱን ለማግለል መወሰኑን ሬውተርስ ዘግቧል።

ኦሬንጅ ኩባንያ ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል ለማዞር በሚደረገው የጨረታ ሂደት ላይ ለመሳተፍ ፍለጎት እንዳለው ያሳወቀው በፈረንጆቹ 2021 ነበር።

ኦሬንጅ ከጨረታ ሂደቱ ራሱን ለማግለል የወሰነው ስትራቴጂውን በፍጥነት ለመተግበር አስቻይ ሁኔታ እንደሌል መረዳቱን ተከትሎ እንደሆነም አስታውቋል።

የጨረታ ሂደቱን በበላይነት የሚመሩት ኢትዮ ቴሌኮምና የኢትዮጵያ ፋይናንስ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ እስካን ማብራሪያ አልሰጡም።

ኢትዮ ቴሌኮም በፈረንጆቹ በ2018 የመንግስት ልማት ድርጅቶችን በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዞር በተያዘው እቅድ ውስጥ ከተካተቱ ድርጅቶች አንዱ ነው።

ኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ የመንግስት ድርሻ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮምን ለመሸጥ ከወሰነች የቆየች ቢሆንም በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተው ጦርነት እንዳዘገየውም ይታወቃል።

@Addis_Mereja
16.1K viewsedited  12:02
Buka / Bagaimana
2023-11-27 15:32:14
በታይላንድ ሙሽራው በሰርጉ ላይ ሙሽሪንትን ጨምሮ 4ሰዎችን ገደለ

በታይላንድ አንድ ሙሽራ በሰርጉ እለት ሙሽሪትን ጨምሮ አራት ሰዎችን ተኩሶ መግደሉን ፖሊስ አስታውቋል። የቀድሞ ወታደር እና የፓራ አትሌት የነበረው ሙሽራው፣ ባለቤቱን ጨምሮ አራት ሰዎችን ተኩሶ ከገደለ በኋላ ራሱን ማጥፋቱንም ፖሊስ ገልጿል።

የ29 ዓመቱ ቻቱሮንግ ሱክሱክ እና የ44 ዓመቷ ካንቻና ፓቹንቱክ በሰሜን ምሥራቅ ታይላንድ ባሳለፍነው ቅዳሜ ነበር የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን የፈጸሙት።በሰርግ ስነ ስርዓቱ ላይ የነበሩ የዐይን እማኞች እንደተናገሩት ሙሽራው የሰርግ ስነ ስርዓቱን አቋርጦ ከወጣ በኋላ የጦር መሰሪያ ይዞ ተመልሶ ነው ጥቃቱን የሰነዘረው።

በዚህም የ44 ዓመቷ ሙሽሪት ካንቻና ፓቹንቱክ ጨምሮ፣ የ62 ዓመት እድሜ ያላቸው የሙሽሪት እና የ38 ዓመት እድሜ ያላት የሙሽሪት እህትን ተኩሶ መግደሉን አስታውቀዋል። በዚሁ ወቅት በተባራሪ ጥይት ሁለት የሰርጉ ታዳሚዎች መመታታቸውን እና ወደ ሆስፒታል ከተወደሱ በኋላ የአንዱ ህይወት ማለፉንም ተዘግቧል።ሙሽራው ጥቃቱን ከፈጸመ በኋላ የራሱን ህይወት ማጥፋቱም ነው የተነገረው።

ፖሊስ ሙሽራው ቻቱሮንግ ሱክሱክ "በወቅቱ በጣም ሰክሮ ነበር" ያለ ሲሆን፤ ግድያውን የፈጸመበት ምክንያት ግን ግልጽ አይደለም ብሏል።በስርጉ ላይ የታደሙ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ የታይላድ መገናኛ ብዙሃን ባወጡት መረጃ፤ ሙሽሮቹ በሰርግ ስነ ስርዓቱ ላይ ሲጨቃጨቁ ነበር ብለዋል።ባል የሚገዛበት የህንዱ የሙሽራ ገበያ ሙሽራው ቻቱሮንግ በእሱ እና በሚስቱ ካንቻና መካከል ያለው የዕድሜ ልዩነት ምቾት ይነሳው እንደነበረም ተዘግቧል።

ሆኖም ግን ፖሊስ “እነዚህ ጥርጣሬዎች ናቸው” ያለ ሲሆን፤ መረጃዎችን እያሰባሰበ መሆኑን እና በቅርቡ ምክንያቱን ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

@Addis_Mereja
14.5K viewsedited  12:32
Buka / Bagaimana
2023-11-27 13:00:16
ኢትዮጵያ የተለያዩ ምርቶችን ወደ ዉጪ በመላክ ከያዘችዉ እቅድ 65 በመቶ ብቻ ማሳካቷ ተነገረ!

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር በተያዘዉ በጀት ዓመት ወደ ዉጪ ለመላክ ካቀደዉ የተለያዩ ምርቶች 1.06 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር መገኘቱን ገልጿል።

በአራት ወሩ ከተላኩ ምርቶች የጥራጥሬ ሰብሎችና የቅባት እህሎች ከፍተኛዉን ድርሻ ይዘዋል ያለዉ ሚኒስትሩ ወደ ዉጪ በመላክ ገቢ ለማግኘት የተያዘው እቅድ 1.6 ቢሊዮን መሆኑን እና የአፈፃፀም እቅዱ 65 በመቶ ሆኗል ብሏል።

Via Capital
@Addis_Mereja
13.4K viewsedited  10:00
Buka / Bagaimana
2023-11-26 22:22:05
በቻይና መዲና ቤጂንግ እና ላዮኒንግ በተሰኘችው ግዛት የተቀሰቀሰው አዲስ ወረርሽኝ አሳሳቢ ሆኗል።

ህጻናትን የሚያጠቃው “የሳንባ ምች መሰል ወረርሽኝ” ሆስፒታሎችን ማጨናነቅ ከጀመረ ዋል አደር ብሏል።ከቤጂንግ በ804 ኪሎሜትሮች ርቃ በምትገኘው ላዮኒንግ ትምህርት ቤቶች ለመዘጋት ተቃርበዋልም ነው የተባለው።ምንነቱ እስካሁን ባልተለየው በሽታ የተያዙ ህጻናት ከፍተኛ ትኩሳት ቢኖራቸውም የጉንፋን ምልክት አልታየባቸውም፤ ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ በሽታዎች ምልክቶችም የላቸውም ተብሏል።

የኮቪድ 19 ቫይረስ በውሃን እንደተከሰተ የቻይና ብሎም የአለም ስጋት ይሆናል የሚል ስጋቱን አስቀድሞ የገለጸው “ፕሮሜድ” የተሰኘው የበሽታ ቅኝት ስርአት አዲሱን የቻይና ወረርሽኝ በስጋትነት ጠቅሶታል።የአለም ጤና ድርጅትም በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት ይደረጉ የነበሩ ጥንቃቄዎች ተፈጻሚ እንዲሆኑ አሳስቧል።የፊት መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ፣ የህመሙ ምልክት ካለባቸው ሰዎች መራቅ እና የታመሙ ሰዎችም ከቤታቸው እንዳይወጡ የሚል ማሳሰቢያውንም በድረገጹ ላይ አስፍሯል።ሰዎች ከሚሰበሰቡባቸው ስፍራዎች እንዲርቁና ከቻሉ ከቤታቸው እንዳይወጡም ነው ያሳሰበው።

“ማይኮፕላዝማ ኒሞኒያ” በተሰኘው ባክቴሪያ ምክንያት ሊከሰት እንደሚችል የተገመተው አዲሱ በሽታ ሳንባን ክፉኛ እንደሚጎዳ ተገልጿል።“ፕሮሜድ” ህጻናትን እያጠቃ ያለው “የሳንባ ምች መሳይ በሽታ” መቼ መስፋፋት ጀምሮ ወደ ወረርሽኝነት እንደሚለወጥ ባይገልጽም ህጻናትን በፍጥነት ማዳረሱ አሳሳቢ ሆኗል።የአለም ጤና ድርጅትም ቻይና የበሽተኞቹን መረጃ፣ የስርጭት መጠኑን እንዲሁም በሆስፒታሎች ላይ የፈጠረውን ጫና በተመለከተ ዝርዝር መረጃ እንድታጋራው ጠይቋል።

@Addis_Mereja
14.1K viewsedited  19:22
Buka / Bagaimana