Get Mystery Box with random crypto!

Addis መረጃ™

Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™ A
Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™
Alamat saluran: @addis_mereja
Kategori: Berita
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 56.59K
Deskripsi dari saluran

@Addis_Mereja ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹
.
⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬
⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬

መረጃዎችን ለመላክ @Adis_Merejaa_bot

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


Pesan-pesan terbaru 11

2023-11-13 12:01:18
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፤ ነገ ማክሰኞ ህዳር 4፤ 2016 በተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ሊሰጡ ነው።

ጥያቄዎቹ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የፌደራል መንግስትን ዓመታዊ ዕቅድ በተመለከተ፤ ከአንድ ወር በፊት ለተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ያቀረቡትን ዓመታዊ የመክፈቻ ንግግር ላይ የተንተተራሱ ናቸው ተብሏል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@Addis_Mereja
13.4K viewsedited  09:01
Buka / Bagaimana
2023-11-10 22:06:42
ጋዛ ውስጥ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ11 ሺህ በላይ መሆኑ ተነገረ!

በሐማስ የሚመራው የጋዛ የጤና ሚኒስቴር ዛሬ አርብ ከሰዓት በኋላ ባወጣው መግለጫ በጦርነቱ አስካሁን የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 11,078 ከፍ ማለቱን አመለከተ።

ሰላሳ አምስት ቀናት ባስቆጠረው እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እያካሄደችው ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ከተገደሉት ፍልስጤማውያን መካከል አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ሕጻናት እና ሴቶች ናቸው።የጤና ባለሥልጣናቱ ካወጡት 11,078 የሟቾች አሃዝ ውስጥ 4,506ቱ ሕጻናት እና ከ3,000 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ተጠቅሷል።

በሐማስ የበላይነት የሚመራው የጤና ሚኒስቴር በቴሌግራም ገጹ ላይ ባሰራጨው መረጃ ላይ ከተገደሉት ከ11 ሺህ በላይ ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች ከ27,000 የሚልቁት ጉዳት ደርሶባቸዋል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጦርነቱን ሰለባዎች ከዚህ በፊት ከተደረጉት ግጭቶች ጋር በማነጻጸር እንዳለው የአሁኑ የሟቾች ቁጥር ከፍተኛ ነው።

ሐማስ ጋዛን ከተቆጣጠረበት ከ2007 (እአአ) በኋላ በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዱ ግጭቶች በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 5,400 ያህል ነበር። የአሁኑ ግን ከዚህ በእጥፍ ከፍ ማለቱን ድርጅቱ አመልክቷል።አሜሪካ እና አስራኤል የሟቾችን አሃዝ በተመለከተ በሐማስ ከሚመራው የጤና ሚኒስቴር የሚወጣው መረጃ በጥንቃቄ ሊታይ ይገባል ሲሉ፣ የዓለም የጤና ድርጅት ግን ቁጥሩ የሚታመን ነው ብሏል።

[BBC]
@Addis_Mereja
14.9K viewsedited  19:06
Buka / Bagaimana
2023-11-10 21:14:07
ሼክ ሁሴን አሊ አላሙዲን ከበርካታ ጊዜያት በኋላ ታይተዋል!

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ልዑክ ቡድናቸው ዛሬ በሳዑዲ አረቢያ ከሼክ ሁሴን አሊ አላሙዲን ጋር ተገናኝቷል።

@Addis_Mereja
12.6K viewsedited  18:14
Buka / Bagaimana
2023-11-10 14:14:55
የዓለማችንን የመጀመሪያው እና የተሳካ የዓይን ንቅለ ተከላ ተደረገ

የኒው ዮርክ የቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች የዓለማችንን የመጀመሪያው እና የተሳካ የዓይን ንቅለ ተከላ ማድረጋቸውን ሮይተርስ አስነብቧል፡፡

ቀዶ ጥገናው ከተከናወነ በኋላ ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ የታካሚው ዓይን የጤናማነት ምልክቶች ታይቶበታል።

የታካሚው የዓይን ደም ሥሮችና ሬቲና ላይ ጤናማ የደም ዝውውሮች እንደታየበት ተገልጿል።

የቀዶ ጥገና ቡድኑን የመሩት ዶክተር ኤድዋርዶ ሮድሪጌዝ "የዓይን ንቅለ ተከላው ወደፊት የሚወስደን ትልቅ እርምጃ ነው፤ ይህ ነገር ለዘመናት ሲታሰብበት የነበረ ቢሆንም ከዚህ በፊት ግን አልተሳካም ነበረ" ብለዋል።

ንቅለ ተከላው የተከናወነላቸው የ46 ዓመቱ አሮን ጀምስ የአርካንሳስ ነዋሪ ሲሆኑ፣ በወታደራዊ ሥራ ላይ እያሉ በደረሰባቸው ከፍተኛ ኃይል ያለው የኤሌክትሪክ አደጋ በግራ ፊታቸው፣ በአፍንጫው፣ በአፋቸው እና በግራ ዓይናቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው እንደነበረ በዘገባው ተጠቅሷል።

ቀዶ ጥገና የተደረገለት ታካሚ እስካሁን ድረስ እየታውን እንዳለገኘ ዘገባው ያመለከተ ሲሆን በታካሚው አይን ላይ ጤናማ የደም ዝውውሮች እንደታዩ ተገልጿል፡፡

@Addis_Mereja
14.3K viewsedited  11:14
Buka / Bagaimana
2023-11-09 02:02:23
የፋኖ ታጣቂዎች በላሊበላ ከተማ ዉስጥ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ዉጊያ መግጠማቸዉ ተሰማ!!

አማራ ክልል ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል አሁንም ውጊያ መቀጠሉን ዶቼ ቬለ ዘግቧል።

በጎጃም- ቡሬ ፣ በሰሜን ሸዋ - ሸዋ ሮቢት ፣ በወሎ - ላሊበላ ፣ በጎንደር - ወረታ ከተሞች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በከተሞች አካባቢ የመከላከያ ሠራዊት አባላት እንደሚገኙ ፣ የፋኖ ታጣቂዎች ደግሞ ከከተሞች ወጣ ባሉ ስፍራዎች እንደሚገኙ ገልፀው ግጭቶችና ውጊያዎች አሁንም መቀጠላቸውን ተናግረዋል። 

የኢትዮጵያ መከላከያ ጦርና አማራ ክልል የሸመቀዉ የፋኖ ታጣቂዎች በታሪካዊቱ #ላሊበላ ከተማ ዉስጥ ዉጊያ መግጠማቸዉ ተነግሯል።የከተማይቱ ነዋሪዎች ዛሬ ጧት ጀምሮ ዉጊያ መኖሩን ቢናገሩም መንግስት ግን አካባቢዉ ሰላም ነዉ ይላል።

ዶቼ ቨሌ ካነጋገርናቸው ሰዎች መካከል የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪው፤ «ባሕር ዳር ላይ ያለው ነገር አሁን ፀጥ ያለ ነው። ሰሞኑን በጢስ ዐባይ አካባቢ ነበረ [ ውጊያ]።» በማለት የገለጹ ሲሆን

በጎጃም መከላከያ ሠራዊት እና ፋኖ ብርቱ ውጊያ ውስጥ ስለመሆናቸው የቡሬ ከተማ ነዋሪው ደግሞ ተናግረዋል። «ከባድ መሣሪያ ቀጥታ የሚተኮሰው ቤት ላይ ማረፍ ጀምሯል። ዜጎች ላይ ነው ማረፍ የጀመረው። ሕፃናትና አረጋዊያን ሳይቀሩ ነው እየተመቱ ያሉት።» ነው የሚሉት።

የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪው እንደሚሉት ደግሞ አንፃራዊ ሰላም የነበረ ቢሆንም ትናንት ምሽት «ያልታወቁ ተኩሶች ነበሩ ፣ ዛሬ ጠዋት መንገድ ተዘግቷል።» ይላሉ።

@Addis_Mereja
16.7K viewsedited  23:02
Buka / Bagaimana
2023-11-07 20:59:50
በሀገር ውስጥ ያሉ እና ጫት በሚጓጓዝበት መስመር ያሉ ሁሉም #ኬላዎች ሙሉ በሙሉ እንዲነሱ ተወስኗል።

በዚሁ መሠረት በጫት ላኪነት የንግድ ፍቃድ ዘንድሮ ጭምር ያወጡት ዳግም ምዝገባ እንዲያከናውኑ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

በጫት ንግድ የተሰማሩ አዲስም ሆኑ ነባር ነጋዴዎች የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያዘጋጀውን መስፈርት ማሟላታቸው እየተረጋገጠና ግዴታ እየገቡ ፍቃድ ይወስዳሉ ብለዋል።

ለዳግም ምዝገባው የሚኖራቸው ጊዜ እስከ ህዳር 15 /2016 ድረስ እንደሚሆን አሳውቀዋል።

በተጨማሪ ሚኒስትሩ ፤ በሀገር ውስጥ ያሉ እና ጫት በሚጓጓዝበት መስመር ያሉ ሁሉም ኬላዎች ሙሉ በሙሉ እንዲነሱ መወሰኑንም ይፋ አድርገዋል።

" ወደ ውጪ በሚላክ ጫት ላይ የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ተግባራት እየበዙ መጥተዋል " ያሉት ሚኒስትሩ  " በዚህም ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ከሚላክ ጫት የምታገኘው ገቢ ከዓመት ዓመት እየቀነሰ ነው " ብለዋል።

ለአብነትም በ2015 ወደ ውጪ ከላከችው ጫት የተገኘው ገቢ ከቀዳሚው ዓመት ከ144 ሚሊዮን ዶላር በላይ ቅናሽ ማሳየቱን ጠቅሰዋል።

ኮንትሮባንድን ጨምሮ የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራት ለዚህ ምክንያት መሆናቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ይህንኑ ለማስተካከል ሲባል ሁሉም ጫት ላኪ ነጋዴዎች በሚቀጥሉት 15 ቀናት ዳግም ምዝገባ እንዲያደርጉ ተወስኗል ብለዋል።

አንዳንዶቹ ነጋዴዎች ፍቃዳቸውን ለሌላ ወገን በማስተላለፍ ያልተገባ ጥቅም እያገኙ መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በ2013 ከጫት ወጪ ንግድ 402 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ፣ በ2014 ዓ/ም 392 ነጥብ 2ሚሊዮን ዶላር ፣ በ2015 ዓ/ም ደግሞ 248 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር ማግኘቷ ተነግሯል።

መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia
13.1K viewsedited  17:59
Buka / Bagaimana
2023-11-06 22:16:34
የኦሞ ወንዝ ነዋሪዎችን አፈናቀለ!

በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ድልኝሙር በተባለው መንደር ነዋሪ ሎኮሪስ ካባለፈው ሳምንት ጀምሮ በኦሞ ወንዝ ሙላት የተነሳ መንደራቸው በውኃ መከበቡን ይናገራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት እሳቸውና ሌሎች የመንደሩ ነዋሪዎች ቤተሰቦቻቸውንና የቤት እንስሳቶቻቸውን በመያዝ ወንዙን አቋርጠው ወደ ደረቃማ መሬቶች መሸሻቸውን ገልጸዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ አሁን ላይ ከወንዙ ሙላት ሕይወታቸውን ማትረፍ ቢችሉም እስከአሁን ግን ምንም አይነት ድጋፍ እንዳላገኙ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።የደቡብ ኦሞ ዞን የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ኖንጎዲዮ በዳሰነች ወረዳ የኦሞ ወንዝ እየሞላ በነዋሪዎችና በመሠረተ ልማቶች ላይ ተደጋጋሚ ጉዳቶችን እያደረሰ እንደሚገኝ ተናግረዋል ሲል ዶቼ ቬለ ዘግቧል።የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ድርጅት በበኩሉ በቀጣይ ቀናትም ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ ሥለሚኖር ኅብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡

@Addis_Mereja
13.6K viewsedited  19:16
Buka / Bagaimana
2023-11-03 17:30:52
የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

Website:  https://result.ethernet.edu.et/
Telegram bot: @moestudentbot

@Addis_Mereja
17.7K viewsedited  14:30
Buka / Bagaimana
2023-11-01 23:56:23
የሰሜን ኮሪያው መሪ ለፍልስጤም ድጋፍ እንዲደረግ ማዘዛቸው ተነገረ!!

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለፍልስጤማውያን ድጋፍ እንዲደረግ ማዘዛቸውን ደቡብ ኮሪያ ገለጸች!!

የሴኡል የስለላ ተቋም ዳይሬክተር ኪም ዩ ዩን ለሀገሪቱ ህግአውጪዎች ባቀረቡት ሪፖርት፥ ፒዮንግያንግ የእስራኤል እና ሃማስን ጦርነት ልትጠቀምበት መዘጋጀቷን ተናግረዋል።የስለላ ተቋሙ ዳይሬክተር ሰሜን ኮሪያ ለሃማስ እና ሌሎች የጋዛ ታጣቂ ቡድኖች የጦር መሳሪያ ለመሸጥ መዘጋጀቷን መናገራቸውንም ወል ስትሪት ጆርናል አስነብቧል።

የደቡብ ኮሪያ መገናኛ ብዙሃንም ይህንኑ የዳይሬክተሩን መረጃ ጠቅሰው ጉዳዩን ሰፊ ሽፋን ቢሰጡትም ፒዮንግያንግ ለሃማስ የጦር መሳሪያ ልትሸጥ መሆኑን ያመላክታሉ ያሏቸውን ማስረጃዎች አላቀረቡም።የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለፍልስጤማውያን “ሁሉን አቀፍ ድጋፍ” ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ከባለስልጣናቶች ጋር ስለመወያየታቸው ግን በስፋት እየተዘገበ ነው።

ሃማስ ከ25 ቀናት በፊት በእስራኤል ላይ ጥቃት ሲፈጽም ሰሜን ኮሪያ ሰራሽ መሳሪያዎችን ታጥቆ ታይቷል የሚሉ ዘገባዎች ባለፈው ሳምንት ሲወጡ እንደነበር ይታወሳል።ቡድኑ ቀደም ብሎም የኪም ጆንግ ኡን ሀገር የሰራቻቸውን የሮኬት ማስወንጨፊያዎች እና ጸረ ታንክ መሳሪያዎች ታጥቋል የሚሉ ሪፖርቶች ቢወጡም ፒዮንግያንግ ሀሰት ነው በሚል አስተባብላለች።

@Addis_Mereja
13.5K viewsedited  20:56
Buka / Bagaimana
2023-11-01 13:32:37 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባን አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር ማብራሪያ ሰጠ!

በ2015 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት የተማሪ ምደባ መስፈርቶች፡-

1. 1000 ለሚሆኑ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፡- የምደባ ስርዓቱ በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል።

2. ውጤት፡- የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

3. የዩኒቨርሲቲ ምርጫ፡- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ተማሪዎች 46 ዩኒቨርሲቲዎች ለምርጫ ቀርበውላቸዋል፡፡ መረጃው የተሰበሰበው https://portal.etherenet.edu.et ላይ ነው፡፡

4. በተማሪዎች የተመረጡ ተቋማት ያላቸው የትምህርት ፕሮግራሞች ፡- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ የትምህርት ፕሮግራሞች እና የተመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ያደረገ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

5. ጾታ ፡- በተቋማት የጾታ ተዋጽኦን ለመጠበቅ በሚኖረው የምደባ ስርዓት የጾታ ተዋጽኦና ሚዛን እንዲጠበቅ ተደርጓል፣

6. የትምህርት ቤት ተዋጽኦ ፡- የምደባ ስርዓቱ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚመደቡ ተማሪዎችን ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ እንዲሆን ያግዛል፡፡ይህም ከአንድ ት/ቤት የወጡ ተማሪዎች በአንድ ዩኒቨርሲቲ ወይም ፕሮግራም ውስጥ እንዳይታጨቁ ይደርጋል፡፡

7. የውጤት ተዋጽኦ ፡-የምደባ ስርዓቱ ተማሪዎች ያስመዘገቡትን ውጤት ታሳቢ ያረገ ሲሆን ይህም ተመሳሳይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች አንድ ላይ እንዳይመደቡ በማድረግ የተለያየ ችሎታና ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችን ቀላቅሎ ለማስተማር ያግዛል፡፡

8. ወሊድን በተመለከተ፡- የምደባ ስርዓቱ እንደ ወሊድ ያሉ ልዩ ሁኔታዎችን ያማከለ ነው፡፡ በመሆኑም በመሰል ሁኔታ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመቀጠል የሚቸገሩ ከሆነ ትክክለኛ ለውጥና ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡ መረጃዎቹ የተሰበሰቡት https//student.ethernet.edu.et ላይ ነው፡፡
•አስፈላጊ ማስረጃዎች: - ከትምህርት ቤታቸው የድጋፍ ደብዳቤ እና የህጻናት የክትባት ካርድ

9. ትክክለኛ የሕክምና ቦርድ ማስረጃዎች፡- በምደባ ወቅት የጤና ችግር ኖሮባቸው ትክክለኛ የሕክምና ማስረጃ ላላቸው ተማሪዎች ምደባው በተለየ መልኩ ሊታይ ይችላል፡፡
• አስፈላጊ ማስረጃዎች፡ ከትምህርት ቤታቸው የድጋፍ ደብዳቤ እና ከህዝብ ጤና ተቋማት የህክምና ምስክር ወረቀት በሶስት ዶክተሮች እና በህክምና ዳይሬክተሩ የጸደቀ።
• የዚህ አይነት መረጃ የተሰበሰበው https://student.ethernet.edu.et በመጠቀም ነው።

10. ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትዮች (identical twins) ፡- በተማሪዎቹ መካከል ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትዮች ካሉ የምደባ ስርዓቱ ከፍተኛ ነጥብ ያገኘው/ችው ተማሪ ከተመደበበት/ችበት የትምህርት ተቋም ቀሪው መንትያ ደግሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቀጥታ ይመድባል። የዚህ አይነት መረጃ የተሰበሰበው https://student.ethernet.edu.et ላይ ነው።
• አስፈላጊ ማስረጃዎች፡- ከትምህርት ቤታቸው የድጋፍ ደብዳቤ እና የልደት የምስክር ወረቀት፣

11. የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች:- የምደባ ሲስተሙ የአካል ችግር ላለባቸው ተማሪዎች እኩል እድሎችን የሚሰጥ ሲሆን ልዩ ፍላጎቶቻቸውን እና ለምደባ መስፈርቶቻቸውን ግምትውስጥ በማስገባት የሚሰራ ይሆናል። የዚህ አይነት መረጃ የተሰበሰበው https://student.ethernet.edu.et በመጠቀም ነው።

• አስፈላጊ ማስረጃዎች፡ ከትምህርት ቤታቸው የድጋፍ ደብዳቤ እና የአካል ችግር ያለበትን የሰውነት ክፍል የሚያሳይ ፎቶግራፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
ማሳሰቢያ፣ ሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ የሚያቀርብ ተማሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከምደባ ውጭ የሚሆን መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

@Addis_Mereja
12.9K viewsedited  10:32
Buka / Bagaimana