Get Mystery Box with random crypto!

Addis መረጃ™

Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™ A
Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™
Alamat saluran: @addis_mereja
Kategori: Berita
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 56.80K
Deskripsi dari saluran

@Addis_Mereja ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹
.
⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬
⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬

መረጃዎችን ለመላክ @Adis_Merejaa_bot

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


Pesan-pesan terbaru 10

2023-11-26 21:01:51
ዘመን ባንክ ከዋናዉ መስሪያቤቱ ህንፃ በመቀጠል 2ኛዉን ህንፃ ሊገነባ መሆኑን ገለፀ!

ዘመን ባንክ በቅርቡ ላስገነባዉ የዋና መስሪያቤቱ ህንፃ የማስፋፊያ ፕሮጀክት በሚል የንድፍ ዲዛይን ዉድድር ማካሄዱን በመግለፅ አሸናፊዉን ይፋ አድርጓል።

ባንኩ 1.5 ቢሊዮን ብር ገደማ ወጪ ላደረገበት እና በቅርቡ ላስመረቀዉ ባለ 36 ወለል ህንፃ ለማስፋፋት በሚል በያዘዉ ፕሮጀክት ሁለተኛዉን ህንፃዉን ሊገነባ መሆኑን አሳዉቋል።

በ 2 ሺህ ካሬሜትር ላይ ለሚያርፈው የህንፃው ንድፍ ስራ በተደረገዉ የዲዛይን ዉድድር አለበል ደስታ አማካሪ ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ካፒታል ሰምቷል።

@Addis_Mereja
14.4K viewsedited  18:01
Buka / Bagaimana
2023-11-23 23:05:51
#አህያ

በአዲስ አበባ ከተማ ከተለመደው " የከብት ስጋ ውጪ ህገወጥ እርድ እየተፈፀመ ነው " የሚል ጥርጣሬን ተከትሎ ጉዳዩን በአንክሮ እየተከታተለ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ማሳወቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ዘግቧል።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፤ ጨለማን ተገን በማድረግ የሚደረግን ህገወጥ እርድ የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ጋር በመሆን ህገወጥ እርድን የመቆጣጠርና የማስወገድ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጾ ፤ ከእንስሳት ዝውውር፣ ግብይትና ዕርድ ጋር በተያያዘ የወጡ ደንቦች ተሻሽለዋል ፤ ደንቦቹን ተላልፈው የተገኙ አካላትም እስከ 15 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ሲል ገልጿል።

ነገር ግን ባለስልጣኑ ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለው እንደሆነ አስታውቋል፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ በ119 ወረዳዎች እንዲሁም በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከዚህ ድርጊት ጋር በተያያዘ ለባለስልጣኑ የደረሰው  ጥቆማ አለመኖሩን ገልጿል።

በሌላ በኩል ፥ የስጋ ነጋዴዎች " የአህያ ስጋ በአዲስ አበባ እየተሸጠ ነዉ " በሚል ምክንያት የቀድሞ ገበያችን በከፍተኛ ደረጃ ተቀዛቅዟል ሲሉ ለ ' ካፒታል ጋዜጣ ' ተናግረዋል።

ሁኔታዉ አሳስቦናል ያሉት የስጋ ነጋዴዎቹ  ከገቢ አንፃር ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚሆነዉን ማጣታቸዉን ለ 'ካፒታል ጋዜጣ' ገልጸዋል።

በመንግስት እውቅና የተሰጠው የአሰላ የአህያ ቄራ በቀን ከ100 - 300 አህዮች ለእርድ ያቀርባል፤ በዚህ ተነሳ ከዚህ ቀደም ከ2 ሺህ እስከ 3 ሺህ ብር ይሸጥ የነበረው አህያ አሁን ከ9,000 እስከ 11,000 ብር እየተሸጠ ነው ተብላል።

@Addis_Mereja
15.8K viewsedited  20:05
Buka / Bagaimana
2023-11-21 20:45:40
" ያለ ውጤት ተበትኗል "

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሸኔ (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ ከሚጠራው ታጣቂ ቡድን) ጋር በሁለት ዙር ሲካሄድ የነበረው ንግግር ያለ ውጤት መቋጨቱን አሳውቋል።

(የመግለጫው ሙሉ ይዘት ከላይ ተያይዟል)
@Addis_Mereja
12.7K viewsedited  17:45
Buka / Bagaimana
2023-11-20 21:48:45
በኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ከሕዳር 11 እስከ 15 ቀን ሰብል እንዲሰበስቡ ተወሰነ!

በኦሮሚያ ክልል ሰብል በደረሰባቸው አካባቢዎች ከ5ኛ ክፍል በላይ የሆኑ ተማሪዎች ከሕዳር 11 እስከ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ሰብል እንዲሰበስቡ መወሰኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው ማምሻውን ባወጣው መግለጫ÷አሁን ላይ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሰብል መሰብሰቢያ ወቅት መሆኑን አንስቷል፡፡

ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የደረሱ ሰብሎችን እንዳያበላሽም ከ5ኛ ክፍል በላይ የሆኑ ተማሪዎች ከሕዳር 11 እስከ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ሰብል እንዲሰበስቡ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ትምህርት ቤቶችም ተማሪዎች ከሰብል ስብሰባ ሲመለሱ የባከነውን ክፍለ ጊዜ እንዲያካክሱ ማሳሰቢያ መሰጠቱን የክልሉ ኮሙኒኬስሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

@Addis_Mereja
15.4K viewsedited  18:48
Buka / Bagaimana
2023-11-19 18:06:04 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የክፍያ ማስተካከያ ማድረጉ ይታወቃል።

የተሻሻለውን የአገልግሎት ክፍያ በተመለከት ከደንበኞቻችን ባገኘነው ግብረ መልስ መሠረት በአንዳንድ  አገልግሎቶች ላይ ድጋሚ የክፍያ ማሻሻያዎች አድርገናል፡፡

በድጋሚ ማሻሻያ የተደረገባቸው አገልግሎቶች እና የተሻሻለው ክፍያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡

1. በወዲአህ በተከፈቱ ሂሳቦች በቅርንጫፍም ሆነ በሞባይል ባንኪንግ የሚደረግ ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አግልግሎት ከክፍያ ነፃ ነው፤
2. በሙዳራባህ ውል የተከፈቱና እና ለረጅም ጊዜ ያልተንቀሳቀሱ ሂሳቦች (Inactive Accounts) ከክፍያ ነፃ ናቸው፤
3. በቅርንጫፍ የሚከናወን ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡

• ከብር 1 እስከ 10,000 - ብር 5
• ከብር 10,000 እስከ ብር 100,000 - ብር 10
• ከብር 100,001 በላይ - ብር 10 ሲደመር በእያንዳንዱ 100 ሺ 5 ብር (ከ100 ብር ያልበለጠ)

4. በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የሚከናወን ከሂሳብ ወደ ሌላ ደንበኛ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡

• ከብር 1 እስከ 50,000 - ነፃ
• ከብር 50,001 እስከ ብር 100,000 - ብር 5
• ከብር 100,001 እስከ ብር 200,000  - ብር 10
• ከብር 200,001 እስከ ብር 300,000  - ብር 15
• ከብር 300,001 በላይ - ብር 20

5. በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ሌላ ባንክ ወደሚገኝ ሂሳብ ገንዘብ ለማስተላለፍ (RTGS) ብር 50 የአገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል፤
6. ከ P2P የገንዘብ ዝውውር በ ኢትስዊች (ETSWITCH) 5 ብር እና የኢትስዊች ክፍያን በመደመር የአገልግሎት ክፍያ ይከፈልበታል፤
7. ወደ ሲቢኢ ብር ሂሳብ ከ50 ብር በታች ለማስገባት የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ የለም፤
8. በሲቢኢ ብር በቀን ከ3 ጊዜ በላይ የገንዘብ ልውውጥ ሲኖር ገንዘብ የማስገባት አገልግሎት እንደሚከተለው የአገልግሎት ክፍያ ይታሰብበታል መባሉን ዳጉ ሰምቷል።

• ከብር 50 በታች - ነፃ
• ከብር 51 እስከ ብር 500  - ብር 6.45
• ከብር 501 እስከ ብር 2,000  - ብር 7.60
• ከብር 2,001 እስከ ብር 3,000 - ብር 8.18
• ከብር 3,001 እስከ ብር 4,000 - ብር 9.33
• ከብር 4,001 እስከ ብር 5,000 - ብር 10.48
• ከብር 5,001 እስከ ብር 6,000 - ብር 11.63
• ከብር 6,001 በላይ - የሚገባው ገንዘብ 0.2 በመቶ መሆኑን ባንኩ አሳዉቋል። ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ለማድረጉ የሰጠዉ ምክኒያት የለም።

@Addis_Mereja
15.8K viewsedited  15:06
Buka / Bagaimana
2023-11-18 12:38:17 ነገ ለሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጲያ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ!

በታላቁ ሩጫ በኢትዬጲያ አዘጋጅነት በከተማችን አዲስ አበባ የሚካሄደው የሩጫ ውድድር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው 10 ኪሎ ሜትር ውድድር ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ፤

ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ ሃያ ሁለት ዘሪሁን ህንፃ ላይ፣

ከቦሌ መድሀኒአለም ወደ ኡራኤል አትላስ መብራት ላይ፣

ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ፣

ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ መኪና አጎና ሲኒማ ለሌሎች ተሽከርካሪዎች  ጥላሁን አደባባይ ላይ፣

ከጎፋ ማዞሪያ አዲሱ መንገድ ወደ ለገሀር ጨርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛው ላይ፣

ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ ከባድ መኪና ቡልጋሪያ መዞሪያ ሌሎች ገነት ሆቴል ላንድማርክ ላይ፣

ከአፍሪካ ህብረት ወደ ንግድ ምክር ቤት ጠማማ ፎቅ ላይ፣

ከሳርቤት ወደ ሜክሲኮ አፍሪካ ህብረት ጥይት ቤት፣

ከጦር ኃይሎች ወደ ሜክሲኮ ክፍተኛ ፍርድ ቤት ላይ፣

ከኑር ህንፃ ባልቻ መስቀለኛ ኑር ህንፃ አካባቢ፣

ከተስፋ ኮከብ ት/ቤት ወደ ልደታ ኮንዶምኒየም ተስፋ ኮከብ ት/ቤት ላይ፣

ከፈረሰኛ ወደ ጌጃ ሰፈር ፈረሰኛ መብራት ላይ፣

ከሞላ ማሩ ወደ ጌጃ ሰፈር ሞላ ማሩ ላይ

ከበርበሬ በረንዳ ወደ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በርበሬ በረንዳ፣

ከጎማ ቁጠባ ወደ አረቄ ፋብሪካ ፣ወደ ሰንጋ ተራ እንዲሁም ወደ ብሄራዊ ቴአትር ጎማ ቁጠባ ላይ፣

ከሜትሮሎጂ ወደ ፖስታ ቤት ሜትሮሎጅ ላይ፣

ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ ሼል ላይ፣

ከጎላ ሚካኤል ወደ ኢሚግሬሽን ጎማ ቁጠባ መስቀለኛ ላይ፣

  ከቸርቸር ወደ ለገሀር ቴዎድሮስ አደባባይና ኢሚግሬሽን መብራት ላይ፣

ከንግድ ማተሚያ ፣ኦርማ ጋራዥና ፍል ውሃ ንግድ ማተሚያ (ኦርማ ጋራዥ)፣

ከአራት ኪሎ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፓርላማ መብራትና የድሮው አሮጌ ቄራ መስቀለኛ (ኮንሰን ላይ)፣

ከአዋሬ ሴቶች አደባባይ ወደ ካሳንቺስ ቶታል ሴቶች አደባባይ ላይ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል፡፡  

ውድድሩ በሚያሄድባቸው መንገዶች ላይ ከዋዜማ ጀምሮ ለረዥም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፅሞ የተከለከለ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ እያስታወቀ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

@Addis_Mereja
13.9K views09:38
Buka / Bagaimana
2023-11-16 07:21:25
አሜሪካ በኢትዮጵያ አቋርጣው የነበረውን የምግብ እርዳታ ከመጪው ወር ጀምሮ ዳግም ልትጀምር መሆኑን አስታውቃለች።

የአሜሪካ መንግስት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) በሰኔ ወር ነበር የምግብ እርዳታ ከተቸገሩ ወገኖች ላይ ተሰርቋል በሚል እርዳታውን ያቋረጠው።በለጋሾች የተገዛ የምግብ እርዳታ ለገበያ መቅረቡና ወደ ውጪ አገራት ጭምር መላኩን የጠቀሰው የተራድኦ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የእርዳታ ስርጭቱን በተመለከተ ተከታታይ ውይይት ማድረጉን ገልጿል።

በዚህም ባለፈው ወር በሀገሪቱ ለሚገኙ ስደተኞች የምግብ እርዳታ ማቅረብ የጀመረ ሲሆን፥ ከመጪው ወር ጀምሮ ደግሞ በመላው ኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች እርዳታ ማቅረብ እንደሚጀምር ማሳወቁን ሬውተርስ ዘግቧል።ኢትዮጵያ የምግብ ድጋፍ ስርጭት ስርአቷን በመሰረታዊነት የሚያስተካክል ስራ መከወኗንና ለጋሽ ድርጅቶች እርዳታው ለተገቢው አካል መድረሱን እንዲከታተሉ መስማማቷን ድርጅቱ አስታውቋል።

ለጋሽ ድርጅቶች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ጫና ሳይደረግባቸው እርዳታ ለሚገባው ወገን መድረሱን ማረጋገጥ እንዲችሉ መፍቀዷንም ነው የዩኤስኤይድ መግለጫ ያመላከተው።በ30 ዓመታት ታይቶ አይታወቅም በተባለ ድርቅና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በኢትዮጵያ 20 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የምግብ እርዳታ ይሻሉ።ሀገሪቱ ከ850 ሺህ በላይ ስደተኞችን በማስተናገድ ላይ ስትሆን ፥ ከ35 ሺህ በላይ ሱዳናውያን ጦርነትን ሽሽት ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። የአለም ምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት በእርዳታ ስርቆት ምክንያት ድጋፍ አቋርጠው መቆየታቸውም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ሲነገር ቆይቷል።

@Addis_Mereja
13.4K viewsedited  04:21
Buka / Bagaimana
2023-11-15 12:33:58
የእስራኤል ጦር ኃይል ወደ አል-ሺፋ ሆስፒታል ዘልቆ መግባቱ ተሰማ!

የእስራኤል ጦር በጋዛ ከተማ ትልቅ ወደ ሆነው አል-ሺፋ ሆስፒታል መግባቱ ተሰምቷል።ወታደራዊ ኃይሉ ወደ ሆስፒታሉ መግባቱ የተሰማው አሜሪካ ለመጀመርያ ጊዜ ሐማስ በአል-ሺፋ ሆስፒታል ስር ማዘዣ ጣብያ እንዳለው የሚያሳይ መረጃ አለኝ ካለች በኋላ ነው።ምንም እንኳ እስራኤል በተደጋጋሚ ይህንን ብትልም ሐማስ ግን በተደጋጋሚ ውድቅ ሲያደረግ ቆይቷል።

ቢቢሲ በሆስፒታሉ የሚገኝ የዓይን እማኝ አናግሮ መረዳት አንደቻለው ታንኮች እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ወደ አል-ሺ ሆስፒታል ገብተዋል።“ስድስት ታንኮችን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኮማንዶ ወታደሮችን በሆስፒታሉ ውስጥ ተመልክቻለሁ። በዋናው ድንገተኛ ክፍል በኩል ነው የገቡት። የተወሰኑት ፊታቸውን የሸፈኑ ሲሆን በአረብኛ ’እንዳነትንቀሳቀሱ እንዳትንቀሳቀሱ’ እያሉ ይጮሃሉ” ሲል ተናግሯል።

ይህ የአይን እማኝ የእስራኤል ወታደሮች አስለቃሽ ጋዛ መተኮሳቸውን እና ሰዎች መተንፈስ ተቸግረው አንደነበር’ ገልጿል።አክሎም ወታደሮቹ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል ሲገቡ መመልከቱን ተናግሯል።ቢቢሲ የአይን እማኙን ምስክርነት ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አልቻለም።የአሜሪካው ፕሬዝዳነት ጆ ባይደን ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔተንያሁ ጋር የስልክ ልውውጥ አድርገዋል።

ኋይት ሐውስ ባወጣው መግለጫ ሁለቱ መሪዎች “በሐማስ እገታ ስር የሚገኙ ሕጻናትን እና አሜሪያውያንን ጨምሮ ስለሚለቀቁበት ሁኔታ ረዥም ጊዜ ወስደው ተነጋግረዋል”።ሐማስ እስራኤል በሆስፒታሉ ላይ ለፈጸመችው ወረራ አሜሪካ ሙሉ ኃላፊነት ትወስዳለች ሲል ተናግሯል።ሐማስ የአሜሪካ መግለጫ ለእስራኤል ወረራ “ይሁንታን” የሰጠ ነው ሲል ይከስሳል።

Via BBC
@Addis_Mereja
13.0K viewsedited  09:33
Buka / Bagaimana
2023-11-14 19:05:46
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 67 ቦይንግ ጀት አውሮፕላኖች የግዢ ስምምነት ተፈራረመ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የአቪዬሽን ታሪክ ትልቁ የተባለለትን 67 ቦይንግ ጀት አውሮፕላኖች የግዢ ስምምነት መፈራረሙን ቦይንግ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ከአየር መንገዶች ሪከርድ የተባለለትን

-11፣ የ 787 ድሪምላይነር፣
-20፣ 737 ማክስ እና ተጨማሪ 36 ጄቶችን መግዛት የሚችልበትን ስምምነት አድርጓል።

@Addis_Mereja
13.5K viewsedited  16:05
Buka / Bagaimana
2023-11-13 19:39:13
እነ ጃል መሮ ለፖለቲካዊ መፍትሔ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ

መንግሥት "ሸኔ" ብሎ በአሸባሪነት የፈረጀውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ኃይል ለሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሔ ለመፈለግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

በእነ ጃል መሮ ድሪባ የሚመራው ታጣቂ ኃይሉ፣ ከመንግሥት ጋር እያደረገ ስላለው ድርድር አጭር መረጃ አውጥቷል።

በታንዛኒያ ደሬ ሰላም በመካሄድ ላይ የሚገኘው ሁለተኛው ዙር፣ የሁለቱ ወገኖች ድርድር እንደቀጠለ ነው።

በዚህኛው ድርድር የታጣቂ ኃይሉ መሪ ጃል መሮና ምክትሉ ጃል ገመቹ አቦዬ እየታሰተፉ መሆኑ ተጠቁሟል።

የድርድሩ ሂደት እንደተጠናቀቀ ታጣቂ ኃይሉ መረጃ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

በቀጠለው ድርድር መንግሥትን ወክለው በድርድሩ ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙት ወታደራዊ አመራሮች፣ በተጨማሪ የፖለቲካ አመራሮች መጨመራቸው ተሰምቷል።

ድርድሩን ዘግይተው በትላንትናው ዕለት የተቀላቀሉት፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንና የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ናቸው።

@Addis_Mereja
13.2K viewsedited  16:39
Buka / Bagaimana