Get Mystery Box with random crypto!

Addis መረጃ™

Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™ A
Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™
Alamat saluran: @addis_mereja
Kategori: Berita
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 56.80K
Deskripsi dari saluran

@Addis_Mereja ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹
.
⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬
⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬

መረጃዎችን ለመላክ @Adis_Merejaa_bot

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


Pesan-pesan terbaru 23

2023-04-22 15:08:53 በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚገኙበት የሱዳን አል-ሁዳ ወህኒ ቤት ተሰበረ 

ከካርቱም በስተምስራቅ የሚገኙ አካባቢዎች በጀነራል አህመድ ሃምዳን ዳጋሎ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ትልቁ የአል-ሁዳ ወህኒ ቤት መሰበሩ ተሰምቷል።

እስር ቤቱ ብዙ ኢትየጵየዊያን በሱዳን የፀጥታ ኃይሎች የሚታሰሩበት ሲሆን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እስረኞቹ እንዲለቀቁ ማድረጉን የአዲስ ዘይቤ ምንጮች ተናግረዋል።

ከካርቱም 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኦምዱሩማን መንገድ የሚገኝና የወንጀለኛ ቡድን መሪዎች፣ አደንዛዥ እፅ አዘዋዋሪዎች እና ከመኖሪያ ፈቃድ ጋር በተገናኘ ብዙ ኢትዮጵያውያን የሚታሰሩበት እንደነበረ ምንጮቻችን ተናግረዋል።

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ እስረኞቹን ማስለቀቁን ተከትሎ ሃሳባቸውን የሰጡ ምንጮች ታስረው ለነበሩት ኢትዮጵያውያን መፈታት በጎ ቢሆንም በከባድ ወንጀል የታሰሩ ሰዎችም መፈታታቸው ስጋት ፈጥሯል።

ግጭቱ ከተጀመረ ጀምሮ 15 የሚደርሱ ኢትዮጵያዊያን በጦርነቱ መገደላቸው የተገለፀ ሲሆንሲሆን በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቂ መረጃ እየሰጠ ባለመሆኑና ስለተገደሉት ዜጎች ጉዳይ መንግስት ያለው ነገር አለመኖሩ በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ትችቶች እንዲሰነዘሩ አድርጓል።በግጭቱ መባባስ ምክንያት ሀገራት ዜጎቻቸውን ከሀገሪቱ አእያስወጡ ሲሆንአሁን የኢትዮጵያ መንግስትም ዜጎቹን ለመታደግ ሀገራዊ ግብረ ሀይል ማቋቋሙን ይፋ አድርጓል።

Addis_Mereja
19.5K views12:08
Buka / Bagaimana
2023-04-22 12:04:19 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የነዳጅ ማደያ ድርጅቶች በሙሉ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

ከሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ተጠቃሚ ለሆኑ አካላት በሙሉ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንደሚካሄድ ያሳወቀዉ ንግድ ቢሮዉ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መፈጸም የተከለከለ መሆኑን አሳዉቋል፡፡

ከኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ውጪ በተለይ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መፈፀም የተከለከለ በመሆኑ ቢሮው በዕለቱ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል ነዉ ያለዉ፡፡ይህ በመሆኑም ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ለማንኛውም የነዳጅ ተጠቃሚ አካላት የነዳጅ ሽያጭን በኤክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንዲያስተናግዱ አሳስቧል።

@Addis_Mereja
12.1K views09:04
Buka / Bagaimana
2023-04-22 12:04:13 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የነዳጅ ማደያ ድርጅቶች በሙሉ ጥብቅ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

ከሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ተጠቃሚ ለሆኑ አካላት በሙሉ የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንደሚካሄድ ያሳወቀዉ ንግድ ቢሮዉ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መፈጸም የተከለከለ መሆኑን አሳዉቋል፡፡

ከኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ውጪ በተለይ በጥሬ ገንዘብ ክፍያ መፈፀም የተከለከለ በመሆኑ ቢሮው በዕለቱ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል ነዉ ያለዉ፡፡ይህ በመሆኑም ከወዲሁ በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ለማንኛውም የነዳጅ ተጠቃሚ አካላት የነዳጅ ሽያጭን በኤክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ እንዲያስተናግዱ አሳስቧል።

@Addis_Mereja
18.9K views09:04
Buka / Bagaimana
2023-04-21 15:52:42 ዩክሬን በመጨረሻ ኔቶን እንደምትቀላቀል የኔቶ ዋና ጸኃፊ አረጋገጡ!!

ሁሉም የኔቶ አጋሮች ዩክሬን የህብረቱ አባል እንድትሆን ተስማምተዋል፤ አሁን ግን ዋናው ትኩረት ሀገሪቱ በሩሲያ ላይ የበላይነትን ማረጋገጥ ነው ሲሉ የኔቶ ዋና ፀሃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ተናግረዋል።

በጀርመን ራምስቴይን የአየር ኃይል ጣቢያ ከሚካሄደው የዩክሬን መከላከያ ቡድን ስብሰባ በፊት ሲናገሩ፣ በዩክሬን ያለው ጦርነት አንዴ ካበቃ ኪየቭ “አዳዲስ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያስችል መከላከያ” ሊኖራት ይገባል ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ዩክሬን የምዕራባውያን ወታደራዊ ጥምረት የሆነውን ኔቶ ለመቀላቀል በተደጋጋሚ ጥያቄ ብታቀርብም፣ ህብረቱ አስቸኳይ መፍትሄ አልሰጣትም።ከሩሲያ ጋር ጦርነት የገጠመችው ዩክሬን ኔቶን ለመቀላቀል ጥረቷን ቀጥላለች። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ያወጀችው ኔቶ ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት መስፋፋቱን እና ይህም ለደህንነቷ እንደሚያሰጋት ከገለጸች በኋላ ነበር።

ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት ከጦር መሳሪያ ጀምሮ በርካታ ድጋፍ እያደረጉ ያሉት አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራት በዩክሬን ኔቶን መቀላቀል ላይ ቁርጥ ያለ ውሳኔ አላሳለፉም።በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ስጋት የገባቸው ስዊድን እና ፊንላንድ ኔቶን ለመቀላቀል ጥያቄ አቅርበው፣ ፊንላንድ ወታደራዊ ጥምረቱን ተቀላቅላለች።
ሁለቱ ሀገራት ጥያቄ ያቀረቡት ቀደም ብለው የነበረ ቢሆንም በቱርክ ተቃውሞ ጥያቄያቸው ተጓትቶ ነበር።

የቱርክ ፖርላማ መፍቀዱን ተከትሎ ፊንላድ አባል ሆናለች። ነገርግን ቱርክ በስዊድን አሉ ከምትላቸው የኩርድ አማጺያን ጋር በተያያዘ ያቀረበችው ጥያቄ ስላልተመለሰ የስዊድንን የአባልነት ጥያቄ አላጸደቀችውም።

@Addis_Mereja
17.8K views12:52
Buka / Bagaimana
2023-04-21 15:52:07 የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ለ72 ሰዓታት ተኩስ ለማቆም ተስማሙ

የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ከዛሬ ጀምሮ ለ72 ሰዓታት ወይም ለሦስት ቀን የሚቆይ የተኩስ አቁም ስምምነት አወጁ፡፡

የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ የተኩስ አቁም ስምምነት መደረጉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም ቤተሰቦች እንዲገናኙ፣ የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ እና ንፁሀን ዜጎች ከጦርነት ቀጣናው ለቀው እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑም ተመላክቷል፡፡

@Addis_Mereja 
15.3K views12:52
Buka / Bagaimana
2023-04-21 10:57:31 ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለ1444ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላም ፣የደስታ ፣ የጤና ይሁንልን።
         ዒድ ሙባረክ

@Addis_Mereja
16.2K viewsedited  07:57
Buka / Bagaimana
2023-04-20 21:07:58 የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ ይከበራል!

1444ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ነገ እንደሚከበር ተገልጿል።


የሸዋል ወር ጨረቃ  በሳኡዲ አረቢያ በቱሚናር እና ሱዳይር ዛሬ ሀሙስ በመታየቷ የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ ጁምዓ / አርብ ይውላል።

እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

@Addis_Mereja 
20.2K viewsedited  18:07
Buka / Bagaimana
2023-04-18 16:24:09 #SUDAN

በሱዳን የEU አምባሳደር ጥቃት ተፈፀመባቸው።

በሱዳን ካርቱም ሚገኙት የአውሮፓ ህብረት (EU) አምባሳደር በመኖሪያ ቤታቸው ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተሰማ።

አምባሳደሩ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ያሳወቁት የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማት ጆሴፕ ቦሬል ናቸው (በትዊተር ገፃቸው)።

ቦሬል ስለ ጥቃቱ ምንም አይነት ዝርዝር ነገር ባይገልጹም አምባሳደሩ ግን " ደህና ናቸው " ብለዋል።

የዲፕሎማቲክ ቦታዎችን እና ሰራተኞችን ደህንነት ማስጠበቅ የሱዳን ባለስልጣናት ቀዳሚ ኃላፊነት ነውም ሲሉ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ቦሬል ፤ በሱዳን የአውሮፓ ህብረት አምባሳደርን ስም ባይፅፉም ስማቸው አይዳን ኦሃራ የሚባሉ ሲሆን የ
#አየርላንድ ዲፕሎማት ናቸው።

ቦሬል ካርቱም ውስጥ የተፈፀመው ጥቃት ፤ በሌሎች ሀገራት የሚሰሩ ዲፕሎማቶች ጥበቃን የሚደነግገውን የተመድ ስምምነት የ " ቪይና ኮንቬንሽን " በእጅጉ የጣሰ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ ናቢላ ማስራሊ ለAFP በሰጡት ቃል " የሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው " ብለዋል፤ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ቡድን ከካርቱም እንዲወጣ እንዳልተደረገ ተናግረዋል።

ቃል አቀባይዋ ፤ በሱዳን ያለው የፀጥታ እና ደህንነት ሁኔታ እየተገመገመ ነው ብለዋል።

@Addis_Mereja
28.1K views13:24
Buka / Bagaimana
2023-04-17 16:44:11 ማስታወቂያ!!

የተባበሩት ኤምሬትስ የሰጠውን ስኮላርሽፕ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች ሁሉ
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ለመስጠት በፈቀደው መሰረት ቀደም ሲል በተማሪዎች ቃል የተገባላችሁ ተማሪዎችና በዕድሉ ለመጠቀም ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች Application Form link:
http://survey.ethernet.edu.et/index.php/518562?lang=en --
በመግባት ከዛሬ 09/08/15 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 ቀናት ከላይ በተቀመጠው ሊንክ በመግባት፡-
1.  የ12ኛ ክፍል የማትሪክ ውጤት ኮፒ (Grade 12 Result) copy
2.  ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኮፒ (Grade 9-12 transcript) copy
3.  CV/ Curriculum Vitae copy
4.  የልደት የምስክር ወረቀት ኮፒ (Birth Certificate) copy እና ሌሎች በሊንኩ የተጠቀሱ መረጃዎችን  እንድትሞሉ እናሳስባለን ።
መረጃዎች ተጣርተው ለፈተና የሚቀረቡ ተማሪዎችን ስም ዝርዝር በቀጣይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የምናሳውቅ መሆናችንን እንገልጻለን።

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር
@Addis_Mereja
14.9K views13:44
Buka / Bagaimana
2023-04-17 16:44:06 ማስታወቂያ!!

የተባበሩት ኤምሬትስ የሰጠውን ስኮላርሽፕ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች ሁሉ
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ለመስጠት በፈቀደው መሰረት ቀደም ሲል በተማሪዎች ቃል የተገባላችሁ ተማሪዎችና በዕድሉ ለመጠቀም ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች Application Form link:
http://survey.ethernet.edu.et/index.php/518562?lang=en --
በመግባት ከዛሬ 09/08/15 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 ቀናት ከላይ በተቀመጠው ሊንክ በመግባት፡-
1.  የ12ኛ ክፍል የማትሪክ ውጤት ኮፒ (Grade 12 Result) copy
2.  ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኮፒ (Grade 9-12 transcript) copy
3.  CV/ Curriculum Vitae copy
4.  የልደት የምስክር ወረቀት ኮፒ (Birth Certificate) copy እና ሌሎች በሊንኩ የተጠቀሱ መረጃዎችን  እንድትሞሉ እናሳስባለን ።
መረጃዎች ተጣርተው ለፈተና የሚቀረቡ ተማሪዎችን ስም ዝርዝር በቀጣይ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የምናሳውቅ መሆናችንን እንገልጻለን።

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር
@Addis_Mereja
26.0K views13:44
Buka / Bagaimana