Get Mystery Box with random crypto!

Addis መረጃ™

Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™ A
Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™
Alamat saluran: @addis_mereja
Kategori: Berita
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 56.59K
Deskripsi dari saluran

@Addis_Mereja ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹
.
⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬
⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬

መረጃዎችን ለመላክ @Adis_Merejaa_bot

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


Pesan-pesan terbaru 21

2023-06-18 18:19:22 በአማራ ክልል የሰላም ድርድር እንዲጀመር ተጠየቀ

የሰሜኑ ጦርነት በሰላም ስምምነት እንደተቋጨው ኹሉ በአማራ ክልል የሚስተዋለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታትም የሰላም ድርድር እንዲጀመር የኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጠይቋል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ ዶክተር መብራቱ አለሙ ከአዲስ ማለዳ ጋር በነበራቸው ቃለመጠይቅ፤ "የሰሜኑ ጦርነት በድርድር እንዳለቀው እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ያለውን የሰላም ችግር ለመፍታት ድርድር እንደተጀመረው ኹሉ፤ በአማራ ክልል ያለውን የሰላም ችግር ለመፍታትም የጋራ ምክር ቤቱ ተመሳሳይ ድርድር መጀመር አለበት የሚል አቋም አለው።" ብለዋል።

የሰላም አማራጮች ገፍተው እንዲሄዱ ጥሪ እናቀርባለን ያሉት ሰብሳቢው፤ "በሰላም ድርድሮች ጉዳይ ኤምባሲዎች ጠርተን መግለጫ መስጠትም እንችላልን።" ሲሉ ተደምጠዋል።

አክለውም፤ "የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በተለይ በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ጋምቤላ ክልሎች አሳሳቢ የሆኑ የጸጥታ ችግሮች መኖራቸውን ገምግሟል።" ካሉ በኋላ፣ በእነዚህ ክልሎች ያለው አሳሳቢ የጸጥታ ሁኔታ በሰላማዊ መንገድ መፈታት እንዳለበት አሳስበዋል።

ዋና ሰብሳቢው "በኢትዮጵያ የሰላም ችግሮች እንዲፈቱ የውጭ ተቋማት እና ኤምባሲዎችን ጨምሮ ከማንኛውም ኃይል ጋር እንሰራለን።" ሲሉም ገልጸዋል።

@Addis_Mereja
29.9K viewsedited  15:19
Buka / Bagaimana
2023-06-11 09:27:09 ማንቸስተር ሲቲ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ አነሳ

ማንቸስተር ሲቲ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ አንስቷል፡፡ የእንግሊዙ ማንቸስተር ሲቲ እና የጣሊያኑ ኢንተርሚላን ምሽት 4 ሰዓት ላይ በቱርኩ አታቱርክ ኦሎምፒክ ስታዲየም የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡

የፔፕ ጋርዲዮላው ማንቸስተር ሲቲ ኢንተርሚላንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ ያነሳው፡፡

በዚህም ማንቸስተር ሲቲ ሶስት ዋንጫዎችን በማንሳት የውድድር ዓመቱን በስኬት አጠናቅቋል፡፡ የፍጻሜ ጨዋታውን የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻንን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን እግር ኳስ ተመልካቾች በቀጥታ ተከታትለውታል፡፡

@Addis_Mereja
3.4K views06:27
Buka / Bagaimana
2023-06-04 13:14:11 ሰበር መረጃ!!

መንግስት "በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ የሚገኘውን የሥላሴ ገዳም ከለላ በማድረግ መንግሥትን በትጥቅ ትግል ለመጣል ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ጽንፈኛ ባላቸው ኃይሎች ላይ በተወሰደው እርምጃ በእስክንድር ነጋና በግብረዓበሮቹ  ለውጊያ ሲውል የነበረው ምሽግ መሰበሩንና
#በ200 ታጣቂዎችም ላይ እርምጃ መወሰዱን(መገደላቸውን) የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ!!


የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ግንቦት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ባወጣው መግለጫ <በደብረ ኤሊያስ ገዳም ሳካሂድ ቆይቻለሁ > ያለው < ወታደራዊ ዘመቻ ዓላማው እስክንድር ነጋ ላይ እርምጃ ለመወሰድ መሆኑን > አረጋግጧል። የጋራ ግብረሀይሉ በመግለጫው < በጎጃም ደብረ ኤልያስ ሥላሴ ገዳም መሽገው መንግሥትን በትጥቅ ትግል ለመጣል ሲንቀሳቀሱ > ነበሩ ባላቸው <እስክንድር ነጋና ግብረዓበሮቹ ላይ በተወሰደው እርምጃ ክልሉን የማተራመስ ሴራቸው ከሽፏል > ብሏል።

መግለጫው አክሎም < በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወረዳ የሚገኘውን የሥላሴ  ገዳም ከለላ በማድረግ መንግሥትን በትጥቅ ትግል ለመጣል ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ጥቂት ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ እርምጃ ተወደስዷል> ሲል ይፋ አድርጓል።በዚህም <በእስክንድር ነጋና በግብረዓበሮቹ  ለውጊያ ሲውል የነበረው ምሽግ መሰበሩንና በ200 ታጣቂዎችም ላይ እርምጃ መወሰዱን > አስታውቋል፡፡ 

<የታጣቂ ቡድኑ መሪና አስተባባሪ  የነበረው > ያላቸው <እስክንድር ነጋና ጥቂት ግብረዓበሮቹ  ከአካባቢው ለመሰወር ቢሞክሩም በዋናነት የመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ለማዋል እግር በእግር በመከታተል የተቀናጀ ኦፕሬሽን እያካሄዱ መሆኑንም > አመልክቷል

<ግለሰቡ[እስክንድር] ይህ እንዳልተሳካለት ሲያውቅ፤ መንግሥትን በኃይል ለመጣል በማቀድ የአማራ ሕዝባዊ ግንባር የተባለ አደረጃጀት በመፍጠር ሽመልስ ስማቸው፣ ሰውመሆን ወረታውና መንበሩ ካሴ ከተባሉ ግብረዓበሮቹ እንዲሁም ከሌሎች ጥቂት የክልሉ ጽንፈኛ ኃይሎች ጋር በመቀናጀትና በህቡዕ በመንቀሳቀስ  ታጣቂዎችን ሲመለምል፣ ሲያደራጅና ስምሪት ሲሰጥ ነበር > ሲል ወንጅሏል።

< ግንባሩን በሀገር ውስጥ ራሱ ሲመራ በውጭ ደግሞ ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ የተባለ ግለሰብ ያስተባብራል > ሲል የገለፀው መግለጫው፤ < ሁለቱ  በፈጠሩት ትስስር በክልሉ የትጥቅ ትግል በማድረግ ሕዝቡን ወደማያባራ ጦርነት ለማስገባት ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል > ሲል ከስሷል።

<በተለይ የገዳሙ አስተዳዳሪ የሆኑትን አባ ኤልሳን ለዚህ ሕገወጥ ተግባር ሲጠቀሙ ነበር > ብሏል። አስተዳዳሪውም ከሃይማኖቱ አስተምህሮ ውጭ በገዳሙ ውስጥ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴ እንዲደረግ ከመፍቀድ ባሻገር ከሌሎች መነኮሳት ጋር በማበርና የጦር መሣሪያ ጭምር በማንገብ ከጽንፈኛ ቡድኑ አባላት ጋር  ተሰማርተው ነበር > ሲል ወንጅሏቸዋል።

<የጥፋት ቡድኑ አባላት ሕገ ወጥ እንቅስቃሴውን እንዲያቆሙና በውይይት ወደ ሰላም እንዲመጡ ከክልል እስከ ወረዳ በሚገኙ አካላት ተደጋጋሚ ጥረት > እንዳደረገ የሚገልፀው መግለጫው ይህ ግን ፍሬያማ ሊሆን እንዳልቻለ አስታውቋል።

<200 የጽንፈኛ ቡድኑ አባላት ታጣቂዎች  መደምሰሳቸውነና የቀሩትም ከመማረካቸውና ከመሸሻቸው ውጪ፤ ቡድኑ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በሚነዛባቸው የማኅበራዊ ትስስር ገፆች በመንግሥት ጸጥታ አካላት በገዳሙና በምዕመናን ጉዳት እንዳደረሰ ተደርጎ የሚሠራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው > ሲል አጣጥሏል።

መግለጫው በመቋጫው <በቀጣይም ክልሉ ከጥቂት ጽንፈኛ ኃይሎች ጸድቶ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲሰፍን ለሚደረገው ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴ ኅብረተሰቡ የጋራ ጥረቱንና አጋርነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል >  ጥሪ አስተላልፏል፡፡

@Addis_Mereja
12.4K views10:14
Buka / Bagaimana
2023-05-30 19:46:39 “ጠላፊው ከላካቸው ሽማግሌዎች ውስጥ የፖሊስ አዛዦች ይገኙበታል”- የጸጋ ቤተሰቦች

በሀዋሳ ከአንድ ሳምንት በፊት የተጠለፈችው ጸጋ በላቸው እስካሁን ያለችበት አልታወቀም።

ጠለፋው እንዴት እንደተፈጸመና ጠላፊው ምን ፍላጎት እንዳለው አል ዐይን ቤተሰቦቹን አነጋግሯል።

ወይዘሪት ጸጋ፥ ግንቦት 15፣ 2015 አመሻሽ ላይ ከስራ ወደ ቤቷ ለማምራት ታክሲ የምትይዝበት ቦታ ላይ ነው የመንግስት መኪና በያዘና አስቀድሞ ለፍቅር ጓደኝነት በሚፈልጋት ግለሰብ የተጠለፈችው። “ከቤቷ ውጭ አድራ ስለማታውቅ አከራዮቿ ወደ ጓደኞቿ እና ፍቅረኛዋ ደወሉ፤ ከዚያም እኔ ጋር ጠዋት ደውለው ጠየቁኝ” የሚለው ወንድሟ ታምሩ በላቸው ፥የስራ ባልደረባዋ እና ጓደኛዋ ግን የጠላፊውን ስም ጠርታ የት እንደሄዱ ጭምር እንደነገረቻቸው ይገልጻል።

ጠላፊው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የአቶ ጸጋዬ ቱኬ የግል ጠባቂ መሆኑን መግለጿንም ያስታውሳል።እነ ታምሩ ይህን መረጃ ይዘው ይገኙበታል ወደተባለው ይርጋለም ከተማ ከፖሊሶች ጋር  ይጓዛሉ፤ ይሁን እንጂ ይርጋለም እንዳሉ “ሀገረሰላም ቡርሳ ነን” የሚል የጽሁፍ መልዕክት ደረሳቸው።

ከይርጋለም ወደ ሀገረሰላም በመጓዝም ወደ ቡርሳ የገጠር መንደር ማቅናታቸውን ነው ወንድሟ ታምሩ የሚያስታውሰው።“በጨለማ 3 ኪሎሜትር አካባቢ በእግር ሄደን ቡርሳ ደረስን፤ የአክስቱ እና የአጎቱ ቤት ተጠቁመን አይተን ተመለስን፥ ከፖሊስ ጋር ሌሊት 10 ስአት ሄድን እስኪነጋ ጠብቀን እያንዳንዱን ቤት ፈተሽን ግን እህቴን ልናገኛት አልቻልንም። እህቴ ተግታበት የነበረው ቤት ባለቤት እና የጠላፊው የእህቱ ወንድም በቁጥጥር ስር ዋሉ” ይላል።

ጠላፊው ሀገረ ሰላም ሲገባ “እንደ ጀግና ተኩሷል” የሚለው ታምሩ፥ “እህቴንም ከአዲስ አበባ እንዳመጣትና ሊያገባት መሆኑን ሲናገርና ከጓደኞቹ ጋር ሲጨፍሩ መታየታቸውን” ከሀገረሰላም ነዋሪዎች መስማታቸውን ሌላኛው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የጸጋ ቤተሰብ ነግረውናል።ጸጋ በቡርሳ ለማምለጥ ሞክራ መያዟንም የአካባቢው ነዋሪዎች እንደነገሯቸው በማከል።

የጸጋ እና የጠላፊው ጥያቄ ምንድን ነው?

ጸጋ በላቸው ከተጠለፈች ስምንተኛ ቀን ቢሆናትም ድምጿን የሰማሁት ሁለት ጊዜ ብቻ ነው ይላል ወንድሟ ታምሩ።“እኔን ነጻ ማውጣት አትፈልግም ወይ? እኔን ነጻ በሚያወጣ መልኩ ተደራደር” ብላኛለች፥ ይሁን እንጂ  ለድርድር ከተቀመጥን ደግሞ እሷ በሰላም የምትወጣበትን ዋስትና አላገኘንም ባይ ነው። ጠላፊው ግለሰብ ደግሞ ሽምግልና መቀመጥ ግዴታ መሆኑን ደጋግሞ መግለጹን ነው የሚናገረው። በሽምግልና የማይፈታ እና ጉዳዩን በህግ የሚይዙት ከሆነም እንደሚገላት እየዛተ ነው። “ሊልካቸው ያሰቡ ሽማግሌዎች ደውለው አውርተውኛል፤ እስካሁን የት እንዳሉ አያውቁም፤ ደህንነቷን አላረጋገጡልኝም" ይላል ታምሩ በላቸው።

የጸጋ በላቸው ጠለፋ ከቤተሰቦቿ አልፎ የመላው ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ሆኖ መነጋገሪያነቱ ቀጥሏል። እናትና አባቷ እስካሁን የልጃቸውን ጠለፋ እንዳልሰሙ ነግሮናል።“አባቴ ሆስፒታል በህክምና ላይ ነው፤ እናቴም እያስታመመችው ነው፤ በጣም የሚወዷትን ልጃቸውን ጠለፋ ከሰሙ ወላጆቼን በሞት አጣቸዋለሁ” ሲልም ስጋቱን ይገልጻል።

እጮኛዋን ለማግባት እየተሰናዳች የነበረችው ጸጋ፥ ጠላፊዋ ሽማግሌ ልኮ ሚስቴ ካላደረኩሽ እያላት ነው። በቴክስት የተለያዩ መልዕክቶችን ሲልክና ፍላጎቱን ሲገልጽ መቆየቱን የሚያወሱት ቤተሰቦቿ በዚህ ዘመን የጠለፋ ወንጀል ይፈጸማል ብለው በፍጹም እንዳልጠበቁ ይናገራሉ።

የሃዋሳ ከተማ ከንቲባን ጨምሮ የጸጥታ አካላ ጉዳዩን ያልሰማ የለም የሚሉት ቤተሰቦቿ፥ መረጃው እንዴት እንደሚሾልክ ባናውቅም ደብዛውን አጥፍቶ ስምንት ቀናት መቆጠራቸውን ያነሳሉ።ጠላፊው ሊልካቸው ካሰባቸው ሽማግሌዎች ውስጥ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ ከፍተኛ የስራ ድርሻ ያላቸው ግለሰብ እንደሚገኙበት በመጥቀስም፥ የህግ ያለህ እያሉ ነው ቤተሰቦቿ።

የጸጋ ቤተሰቦች ከጠላፊው ጋር ተመሳጥራ ያስጠለፈቻት ብለው የሚጠረጥሯትና በቁጥጥር ስር ውላ የነበረችው ባልደረባዋም በ30 ሺህ ብር ዋስ መውጣቷን ገልጸዋል።(ምንጭ፣ አልአይን)

@Addis_Mereja
24.3K views16:46
Buka / Bagaimana
2023-05-25 21:07:05 መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ የነበሩ ታራሚዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ !

ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት  መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉ የከባድ ውንብድና ወንጀል ፍርደኛ ታራሚዎች በቁጥጥር መዋላቸው ተገለጸ። 

ትናንት ሌሊት 10 ሰዓት ከ30 ላይ መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉ 10 የከባድ ውንብድና ፍርደኛ ታራሚዎች ላይ ማረሚያ ቤቱ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥበቃና የደኅንነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ድሪባ ሰንበታ ለፋናቢሲ አስታውቀዋል።

ለማምለጥ ሙከራ ካደረጉ ፍርደኞች መካከል ከዚህ በፊት አምልጦ ከጣልያን ሀገር በኢንተርፖል ተይዞ የመጣ ታራሚ ይገኝበታል ያሉ ሲሆን ፥ ሌሎችም በተደጋጋሚ ከጤና ጣቢያ ፣ከመኪና ላይ ጭምር ለማምለጥ ሞክረው የተያዙ ፍርደኞች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ማረሚያ ቤቱ  ዛሬ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ቀጠሮ የነበራቸው ታራሚዎችን አጅቦ በማቅረብ መደበኛ ስራውን ሲሰራ መዋሉን አስተባባሪው አክለዋል። ታራሚዎቹ  ከመሰል ድርጊት እንዲቆጠቁ ተገቢ የሆነ  የክትትልና የቁጥጥር ስራው ይቀጥላልም ነው ያሉት።

@Addis_Mereja
32.4K views18:07
Buka / Bagaimana
2023-05-15 18:35:37 “ዘ ዊኬንድ” መጠሪያውን ወደ ትውልድ ሥሙ አቤል ተስፋዬ መኮንን መለሰ 

“ዘ ዊኬንድ” መጠሪያውን ወደ እውነተኛ የትውልድ ሥሙ አቤል ተሥፋዬ መኮንን መመለሱን አስታወቀ፡፡

ካናዳዊው አርቲስት ከሰኞ ዕለት ጀምሮ የትዊተር እና የኢንስታግራም አካውንቱን ወደ መደበኛው የትውልድ ሥሙ በመቀየር መጠቀም ጀምሯል።“የአሁኑ ለውጥ “ዘ ዊኬንድ” የሚለውን ማንነት ቀስ በቀስ የመግደል ሰፊ ዕቅድ ጅማሮ እንደሆነ” መግለጹን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

በአዲስ ማንነት ለመወለድ እና አቤል በሚለው የትውልድ መጠሪያው ቀጣዩን የሙዚቃ አልበም ለአድማጭ እንደሚያደርስም ገልጿል። ከዚህ በኋላም በሙዚቃው ኢንዱስትሪ መለያው በሆነው “ዘ ዊኬንድ” ሳይሆን በትክክለኛው ስሜ አቤል ተስፋዬ ብላችሁ ጥሩኝ ሲልም ነው የገለጸው።

አያይዞም “ከቀድሞው ማንነቴ በመውጣት እንደገና የመወለድ ፍላጎት አለኝ” ብሏል። አርቲስት አቤል በእናቱ ስም “ሳምራ ቡናን” በመጠቀም የኢትዮጵያን ቡና እያስተዋወቀ እንደሚገኝ ይታወቃል።

@Addis_Mereja
10.4K viewsedited  15:35
Buka / Bagaimana
2023-05-15 16:50:47 ሰርጉ ወደ ሀዘን ተቀየረ!!

በሰርግ ላይ በተተኮሰ ጥይት ሙሽራው እና አባትየው ህይወታቸው አለፈ!!

በምዕራብ ጎጃም አስተዳደር  ዞን በቋሪት ወረዳ ወይበኝ ቀበሌ ልዩ ቦታው በተለምዶ አነሳት እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ በባህሉ በወጉ መሰረት ልጃችንን ለልጃችሁ ተባብለው ሙሽሪትና ሙሽራው ሊጣመሩ የሙሽራው ቤተሰብና የሙሽሪት ቤተሰብ በስጋ ዝምድና ሊጣመሩ ቤት ባፈራው እንደአቅም ድግስ በመደገስ የሩቁና የቅርቡ ወዳጅ ዘመድ ልጃችንን ስለምንድር ልጃችንን መርቁልን ማለት የተለመደ ስርዓትና ወግ ነው፡፡

ታዲያ በዕለተ እሁድ ከሩቁ ከቅርብ የተጠራው ቤተዘመዱ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሙሽራው መምጫ ሰዓት ደረሰ ሙሽራው ከነሚዜወቹ ደረሱ የሙሽሪት ቤተሰቦች በጣም ደስ አላቸው እልልታውን አቀለጡት ሙሽራው ሙሽሪትን በቤተሰብ አስመርቆ ወደቤቱ ሊመለስ ሲል ሞቅ ያለ ጭፈራ ሆታ ተነሳ በጭፈራው መሃል ቅልጥ ያለ የጥይት ተኩስም ተተኮሰ በድንገት ጭፈራ ሲጨፈር የነበረው ሰው ፀጥ አለ በጭፈራው መሃል በተተኮስ ጥይት ሙሽራው እና የሙሽራው አባት ወዲያውኑ ህይታቸው ያልፋል፣ አንድ የሴት ሚዜ አና ሰርጉን ለማድመቅ የተገኙ 4 ሰወች በድምሩ አምስት ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን በተደረገላቸው ህክምና ህይወታቸው መትረፉን የወረዳው የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ረ/ኢ/ር ተመስገን ሙሉነህ ተናግረዋለወ።

የወንጀል ድርጊት የተሳተፉትን በቁጥጥር ስር አድርገው ምርመራ እያጣሩ መሆኑን ገልፀዋል።

መረጃው የምዕ/ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ነው።

@Addis_Mereja
11.3K viewsedited  13:50
Buka / Bagaimana
2023-05-13 09:23:54 ኢትዮጵያ የብርን የመግዛት አቅም ማዳከሟ አይቀሬ መሆኑን ኢኮኖሚስቶች ተናገሩ!!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደ ሀገር የገጠመውን የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመፍታት በሚል በየጊዜው የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል።

የወጪ ንግድን ለማበረታታት እና የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመፍታት እንደ መፍትሔ ሲወሰድ የቆየው የብርን የመግዛት አቅም ማዳከም አንዱ ነው። ለአብነትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ስልጣን በመጡበት ወቅት አንድ የአሜሪካ ዶላር 27 ብር ገደማ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በባንኮች 54 ነጥብ 2 ብር በመመንዘር ላይ ሲሆን በጥቁር ገበያ ደግሞ እስከ110 ብር ድረስ እየተመነዘረ ይገኛል።

መንግስት በጦርነት እና ኮሮና ቫይረስ የተጎዳውን ኢኮኖሚ እንዲያገግም ከዓለም አቀፍ የገንዘብ አበዳሪ ተቋማት ብድር እና እርዳታ ለማግኘት ጥረት ላይ እንደሆኑ ይገለጻል። በቅርቡም የአይኤምኤፍ ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ከመንግስት ከፍተኛ ባለሙያዎች እና አመራሮች ጋር በአዲስ አበባ እና በዋሸንግተን ውይይት ማድረጋቸው ና ጥሩ መግባባቶች ላይ ተደርሷል ማለታቸው ይታወሳል። ይህን ውይይት ተከትሎም ዓለም ባንክ እና አይኤምኤፍ የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ምንዛሬ ተመንን በጥቁር ገበያ ካለው ምንዛሬ ተመን ጋር እኩል እንዲያደርጉ ምክረ ሀሳብ እንዳቀረቡ ሮይተርስ ዘግቧል።


አል ዐይን አማርኛ በጉዳዩ ዙሪያ የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ ምንዛሬ ተመን እና እጠረቱ ጋር በተያያዘ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችን አነጋግሯል።

ዶክተር ሽመልስ አርአያ በማክሮ ኢኮኖሚክስ ጉዳዮች ዙሪያ አማካሪ እና የጥናት ባለሙያ ናቸው፤ እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ገጥሞታል።

እጥረቱን ተከትሎም መንግስት የብርን የመግዛት አቅም ማዳከሙ አይቀሬ ነው፣ እነ ዓለም ባንክም ብዙ ቅድመ ሁኔታዎችን ያስቀመጡት ኢትዮጵያ ያለባትን እጥረት መጠን ስለሚያውቁ ጭምር መሆኑንም ዶክተር ሽመልስ አክለዋል።

ዓለም ባንክ አሁን ያለው የዓለም ኢኮኖሚ ስርዓት እንዲቀጥል ይፈልጋል ያሉት ዶክተር ሽመልስ ስርዓቱ እንዲቀጥል ደግሞ ሀብታም ሀገራት ሀብታም ሆነው እንዲቀጥሉ የግድ ድሃ ሀገራት ከድህነታቸው እንዲወጡ አይፈለግም ብለዋል።በብዙ ጉዳዮች እየተፈተነ ያለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የገጠመውን የውጭ ምንዛሬ ተመን ለመፍታት ሲል መንግስት ብድር እና ሌሎች የገንዘብ ድጋፎችን ለማግኘት የብርን የመግዛት አቅም ያዳክማል፣ ለዚህ ደግሞ የውጪ ንግድን ለማበረታታት የሚል ስም ይሰጣልም ብለዋል።

ከዚህ በፊት የተደረጉ የብርን የመግዛት አቅም ማዳከም ውሳኔዎች የኑሮ ውድነትን ከማባባስ፣ የሐብት ሽሽትን ከመፍጠር እና የንግድ ሚዛንን ከማዛባት ውጪ ጥቅም አለማስገኘታቸውንም አክለዋል ዶከተር ሽመልስ። እንደ ዶክተር ሽመልስ ገለጻ የሀገር ውስጥ መገበያያ ገንዘብን ማዳከም የሚሰራው እንደ ጃፓን እና ቻይና ያሉ ሰፊ ወደ ውጪ ሊላኩ የሚችሉ ምርቶች ላሏቸው ሀገራት ብቻ እንጂ እንደ ኢትዮጵያ የግብርና ምርቶችን ወደ ውጪ ለሚልኩ ሀገራት አይደለም።

መንግስት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከሚያመነጨው ገቢ በላይ ብር ማተሙን ካላቆመ የኢኮኖሚ ቀውሱ ይጨምራል ያሉት ደግሞ ሌላኛው ኢኮኖሚስት አቶ መቆያ ከበደ ናቸው። አቶ መቆያ እንዳሉት “የመንግስት ገቢ እና ወጪ አለመመጣጠን፣ ቅንጡ ፕሮጀክቶች ላይ ከፍተኛ ገንዘብ ማፍሰስ እና መንግስት ራሱ የውጭ ምንዛሬ ከጥቁር ገበያ እየገዛ መሆኑ በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱን እያባባሱ ናቸው” ብለዋል።

“በኢትዮጵያ ማንኛውም ሰው የየትኛውንም ሀገራት መገበያያ ብር እስካለው ድረስ ከጥቁር ገበያ እየገዛ ነው” የሚሉት አቶ መቆያ ይህ የሚያሳየው የውጭ ምንዛሬ ከገበያው ላይ መኖሩን ነው፣ ኢኮኖሚው የውጭ ምንዛሬ እያመነጨ ነው፣ ችግሩ የአያያዝ እንጂ የአቅርቦት አይደለም ሲሉም አክለዋል። መንግስት የገጠመውን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመፍታት ኢኮኖሚውን በውድድር ለይ የተመሰረተ ማድረግ እና የውጭ ምንዛሬ ተመኑን በባንኮች እና በጥቁር ገበያ ያለውን እኩል ማድረግ ይኖርበታልም ብለዋል። በኢኮኖሚው አስገዳጅነትም ሆነ በእነ ዓለም ባንክ ቅድመ ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት የብርን የመግዛት አቅም ማዳከሙ እንደማይቀርም አቶ መቆያ ግምታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ ከሰሞኑ የብርን የመግዛት አቅም ሊዳከም ነው በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰት ነው ሲል ማስተባበሉ ይታወሳል።

@Addis_Mereja
5.7K views06:23
Buka / Bagaimana
2023-05-04 18:54:25 በአማራ ክልል የሀገር መከላከያ እና በአካባቢው ታጣቂዎች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ግጭት ውስጥ ሙግባታቸውን ኢሰመኮ ገለጸ!!

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው “የሕግ ማስከበር ዘመቻ”ን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል። ኮሚሽኑ ይህ ድርጊት በሰብአዊ መብቶች ላይ ያለውን አንድምታና ተጽእኖ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑ አስታውቋል።

ኮሚሽኑ አደረኩት ባለው ክትትል በሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎና ሰሜን ሸዋ ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት አለ ብሏል።

በተለይም ሸዋሮቢት፣ አርማኒያ፣ አንጾኪያ፣ ገምዛ እና ማጀቴ በመከላከያ ሰራዊት እና በአካባቢው ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥና በከባድ መሣሪያ ጭምር የታገዘ ጥቃት መኖሩን ደርሼበታለሁም ብሏል።በዚህ የተኩስ ልውውጥ ምክንያትም በሲቪል ሰዎች ላይ የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት ከመድረሱ ባለፈ ከደሴ ወደ አዲስአበባ የሚወስደው መንገድ በተለያዩ ጊዜያት መዘጋቱን እንዳረጋገጠ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በተጨማሪም በክልሉ ያሉ የተወሰኑ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ የክልል ልዩ ኃይሎችን እንደገና የማዋቀር ውሳኔን በመቃወም የተካሄዱ ሰልፎችን መርተዋል የተባሉ የተወሰኑ ወጣቶችና ከፋኖ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች እንደታሰሩ ኢሰመኮ መረዳቱንም አስታውቋል።

ግጭቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶችና ንግግሮች እንዲቆጠቡ፣ ስለደረሰው ጉዳት ሁሉ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥም ኢሰመኮ ጠይቋል። እንዲሁም በማናቸውም ሁኔታ የሚፈጸሙ እስራቶች ሕግን መሠረት ያደረጉ በተለይም “የጥብቅ አስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነት እና ከመድልዎ ነጻ መሆን” የሚሉትን የሰብአዊ መብቶች መርሆችን ያከበሩ መሆናቸውን መንግሥት እንዲያረጋግጥ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Mereja
17.0K views15:54
Buka / Bagaimana
2023-05-04 17:00:01 የ2024 ድቪ ሎተሪ ቅዳሜ ይፋ ይደረጋል!

የ2024 ድቪ ሎተሪ እድለኞች ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ይፋ እንደምታደርግ እንደሚደረግ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በትዊተር ገጹ ጽፏል። ኤምባሲው ዜጎች ከድቪ ሎተሪ ጋር በተያያዘ ከሀሰተኛ መረጃ እንዲጠነቀቁ አሳስቧል።

አሜሪካ በዓለም ላይ በየዓመቱ 50 ሺህ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ ወይም ድቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ ሀገሯ ታስገባለች።

@Addis_Mereja
17.2K viewsedited  14:00
Buka / Bagaimana