Get Mystery Box with random crypto!

Addis መረጃ™

Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™ A
Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™
Alamat saluran: @addis_mereja
Kategori: Berita
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 56.80K
Deskripsi dari saluran

@Addis_Mereja ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹
.
⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬
⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬

መረጃዎችን ለመላክ @Adis_Merejaa_bot

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


Pesan-pesan terbaru 22

2023-05-02 21:01:14 የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

በአዲስ አበባ ከተማ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የዋጋ ማስተካከያው ከሚያዝያ 24 ቀን 2015 ሌሊት 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2015 ዓ.ም  የሚቆይ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በዚሁ መሠረት፡ -

- ቤንዚን በሊትር 69 ብር ከ43 ሳንቲም ብር

- ነጭ ናፍጣ በሊትር 71 ብር ከ08 ሳንቲም

- ኬሮሲን በሊትር 71 ብር ከ08 ሳንቲም

- የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 66 ብር ከ60 ሳንቲም 

- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 57 ብር ከ84 ሳንቲም

- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 56 ብር ከ50 ሳንቲም ተደርጓል።

ምንጭ፣ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

@Addis_Mereja
9.6K viewsedited  18:01
Buka / Bagaimana
2023-04-30 21:57:56 የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ዛሬ በሰጠው መግለጫ "ሰሞኑን በጭካኔ የተገደሉት የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባልና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ እና የጥቃት ሰለባ የሆኑ የሥራ ባልደረቦቻቸው  የተገደሉት በለጠ ሸጋውና ምሕረት ወዳጆ በተባሉት የጽንፈኛ ኃይሉ ታጣቂ መሪዎችና ግብረ-አባሮቻቸው መሆኑን ገልጿል።

በመግለጫው "እነዚህ ኃይሎች እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈጸም በአማራና በሌሎች አካባቢዎች በሚገኙ 130 ወረዳዎች የመለመሏቸውን 450 ግለሰቦች የአማራ ክልል ህዝብ የመረጣቸውንና በተለያዩ የአመራር እርከኖች ላይ ያስቀመጣቸውን በኃይል በማስወገድ በራሳቸው መዋቅር የመተካት ሥራ ሲሰሩ እንደነበር  በክትትልና በምርመራ የተደረሰባቸው መሆኑን አስታውቋል

በመግለጫው "የእነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎችን የሚዲያና ፕሮፓጋንዳ ክንፍ የሚመራው

መስከርም አበራ በተባለች ግለሰብ መሆኑን ጠቅሶ፤ በዚህ ህቡዕ አደረጃጀት ውስጥ

ከሀገር ውስጥ ዳዊት በጋሻው የተባለ ግለሰብ እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ ሀገራት ደግሞ

ከኢትዮ 360ና መረጃ ቲቪ ሀብታሙ አያሌው፣ ምንአላቸው ስማቸው፣ ብሩክ ይባስ እና እየሩሳሌም ተ/ፃዲቅ 

በተጨማሪም ዘመድኩን በቀለና ልደቱ አያሌው

ከአንከር ሚዲያ መሳይ መኮንን እንዲሁም ሌሎች ግለሰቦች የዚህ እኩይ ዓላማ አስፈፃሚ አባላት መሆናቸውን በምርመራ መረጋገጡን" ግብረሀይሉ ገልጿል።

ግብረ ሀይሉ "እነዚህ የሽብር ኃይሎች ከሚኖሩባቸው ሀገራት በአለም አቀፍ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) እንዲሁም  እነሱ ከሚኖሩባቸው ሀገራት መንግሥት የፀጥታና የደኅንነት ተቋማት ጋር በመሆን ወደ ሀገር ቤት ተላልፈው እንዲሰጡ በህግም እንዲጠየቁ እየሰራ መሆኑንና ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

@Addis_Mereja
6.0K views18:57
Buka / Bagaimana
2023-04-29 14:18:38 የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል መሪው ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሱዳን ጦር የሚፈጽመውን የአየር ላይ ጥቃት እስካላቆመ ድረስ ለድርድር አንቀመጥም ብለዋል።

ጦሩ “በግዴለሽነት” ሃይላችን በቦምብ እየደበደበ ነው ያሉት ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ፥ የተኩስ አቁም ስምምነቱ መጣሱን አብራርተዋል። “ሱዳን እንድትፈራርስ አንፈልግም” በማለትም የጀነራል አልቡርሃን ጦር ግጭት እያባባሰ ነው ስሉ ከሰዋል።

በጎረቤት ሀገራት፣ በአሜሪካ እና በመንግስታቱ ድርጅት አማካኝነት የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከሀሙስ ምሽት ጀምሮ ለ72 ስአት እንዲራዘመ መደረጉ ይታወሳል። ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎም በደቡብ ሱዳን ከጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ጋር ፊት ለፊት ለመደራደር ፍላጎት ማሳየታቸው አይገለጽም።

ይሁን እንጂ ሄሜቲ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ የሱዳን ጦር በቦምብ መደብደቡን እስከቀጠለ ድረስ ድርድር የሚታሰብ ጉዳይ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል። የተኩስ አቁሙ ተገባራዊ ሆኖ ግጭቱ ከበረደ በኋላ ግን ለመደራደር ዝግጁ ነኝ ማለታቸው ተዘግቧል።

“ከአልቡርሃን ጋር የግል ጸብ የለኝም” ያሉት ሄሜቲ፥ ይሁን እንጂ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ታማኝ ደጋፊዎች መሰብሰባቸውን በመጥቀስ በከሃዲነት ከሰዋቸዋል። በ2019 አልበሽርን ከአልቡርሃን ጋር በመሆን ያስወገዱት ሄሜቲ፥ “የሲቪል አስተዳደር ነገ ሳይሆን ዛሬ እንዲመሰረት እፈልጋለሁ” ብለዋል።ይሁን እንጂ በ2021 ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ላይ በተደረገው መፈንቅለ መንግስት ተሳትፎ እንዳላቸው የሚጠቅሱ ተንታኞች፥ የአሁኑ ጦርነት የሲቪል አስተዳደር ከመሻት የመነጨ እንዳልሆነ ያነሳሉ።
 
@Addis_Mereja
11.8K views11:18
Buka / Bagaimana
2023-04-29 01:10:52 ሰበር ዜና

ግብረ ኃይሉ “በአማራ ክልል ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ኃይሎች ላይ እርምጃ እየወሰደኩ ነው” አለ!!


የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል “በአማራ ክልል ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ እርምጃ እየወሰድኩ ነው” አለ።

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ባወጣው መግለጫ፤ ለአማራ ሕዝብ እንታገላለን በሚል በውስጥም በውጭም በመቀናጀት የራሳቸውን ህቡዕ አደረጃጀት የፈጠሩ አካላት ከመሰል ቡድኖች ጋር በመቀናጀት የሕዝቡን የቁርጥ ቀን ልጆች መልሰው እየበሉ ይገኛሉ። “እነዚህ ኃይሎች በትናንትናው ዕለትም የአማራ ክልል ብልፅግና ጽሕት ቤት ኃላፊ የሆነውን ግርማ የሺጥላን በመግደል አስነዋሪ ድርጊታቸውን አስመስክረዋል” ብሏል ግብረ ኃይሉ።

“በአማራ ክልል ሕገመንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስም ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠርም ሲጥሩ መቆየታቸውን” መግለጫው አመላክቷል።

የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይልም ይህን ተከትሎ አስፈላጊና ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ነው የገለጸው።

ይሄ ጽንፈኛ ኃይል በአማራ ክልል ሳይገደብ እንደ ሀገርም መንግስትን በኃይል ከስልጣን ለማስወገድ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም ያለው የጋራ ግብረ ኃይሉ መግለጫ÷ ከዚህ የጥፋት መንገዳቸው እንዲመለሱ በተደጋጋሚ የተሰጣቸውን ዕድል ከመጠቀም ይልቅ አሁንም በሕ ገወጥ ተግባራቸው መቀጠላቸውን አመልክቷል፡፡

በዚህ ህገ ወጥ ተግባራቸውም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በሕግ እየታየ የሚገኙ በርካታ የቡድኑ አባላት መኖራቸውንም ግብረ ኃይሉ አስታውቋል፡፡ መንግስት በሀገሪቱ ብሎም በክልሉ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ በሌሎቸም የሕገ ወጥ ቡድኑና ቡድኑን በገንዘብና በሐሳብ በህቡእ በሚደግፉ አካላትና ግለሰቦች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ ነው ያስታወቀው፡፡

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ የፅንፈኛ ቡድኖቹ ደጋፊዎች በዚህ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅ ላይ የተፈፀመውን ግድያ ከመኮነን ይልቅ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ገዳይ ቡድኖቹን ሲደግፉ ተስተውለዋል ብሏል መግለጫው፡፡ሐሳብን በሐሳብ ከማሸነፍ ይልቅ ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት ባፈነገጠ መልኩ በአሰቃቂ ሁኔታ ግድያ የፈጸሙትን ፅንፈኛ ቡድኖች ሕዝቡ በአንድነት በማውገዝ ኢትዮጵያዊ ጨዋነቱን ሊያስመሰክር ይገባልም ብሏል፡፡

በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ የፅንፈኛ ኃይሎቹን ትክክለኛ መልክና ገፅታ ለሕዝቡ በይፋ ያጋለጠ ነው ብሏል የደኅንነትና የጸጥታ የጋራ ግብረ ኃይል፡፡ መንግስት ለሕዝቡ ሰላምና ደኅንነት መረጋገጥ ግዴታውን ለመወጣት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ የጀመረ በመሆኑ÷ ሕዝቡም ይሄንን ተገንዝቦ የፌደራል እና የክልል የፀጥታ አካላት ተጠያቂነትን ለማስፈን የጀመሩትን እንቅስቃሴ ጥቆማና መረጃ በመስጠት እንዲደግፍ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የፅንፈኛ ኃይሎቹን አስነዋሪ ተግባር በመሸፋፈን በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች መሰረተ ቢስ ወሬዎችን ከሚያሰራጩ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ሕብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅ ግብረ ኃይሉ አሳስቧል፡፡

@Addis_Mereja
13.7K views22:10
Buka / Bagaimana
2023-04-27 12:13:22 የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች መቀሌ ገቡ !!

አቶ አደም ፋራህ የተመራና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና ሌሎች ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን ወደ መቀሌ ተጓዘ።

በቡድኑ ውስጥ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ፣ የአፋር ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል፣ የደቡብ ክልል፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ የጋምቤላ ክልል፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የሶማሌ ክልል፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ይገኙበታል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሀርና ሚኒስትሮች እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች አብረው ተጉዘዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለሰሜኑ ጦርነት የሠላም ስምምነት አስተዋጽኦ  ላበረከቱ አካላት የዕውቅና መርሀ-ግብር ሲከናወን  የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ወደመቀሌ በማቅናት መቀራረቡን እንዲያጠናክሩ ተናግረው እንደነበር የሚታወስ ነው።

@Addis_Mereja
16.8K views09:13
Buka / Bagaimana
2023-04-27 03:43:39 የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝደንት አልበሽር ከእስር ቤት ማምለጣቸውን ተሰማ።

ፕረዚደንት ዑመር አል በሽር ግጭቱ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ሚያዝያ 15 ቀን በፊት ወደ ወታደራዊ ሆስፒታል እንዲዛወሩ ተደርጎ እንደነበር ታውቋል። ከሳቸው ጋራ ቢያንስ 5 የቀድሞ ባለስልጣኖቻቸው የነበሩ ሲሆን በዳርፉር ለተፈጸመው እልቂት በዓለም አቀፉ የጦር መዳኛ ፍርድ ቤት የሚፈለጉት አብደልራሂም ሞሐመድ ሐሰን ይገኙበታል ተብሏል።

@Addis_Mereja
16.9K views00:43
Buka / Bagaimana
2023-04-27 03:43:21 የሱዳን ስደተኞች በመተማ በኩል እየገቡ ነው!!

በሀገረ ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት የተለያዩ ሀገር ዜጎች በመሸሽ በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በኩል እየገቡ ነው።

በሀገረ ሱዳን የእርስ በእርስ ግጭት ምክንያት የተለያዩ ሀገር ዜጎች ከግጭቱ በመሸሽ  በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በኩል እየገቡ ነው። የተፈጠረውን አለመረጋጋት ሸሽተው የሚመጡ የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜጎችን የምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በሰላም እያስተናገደች  ነው።

ሱዳን ላይ በተፈጠረው የውስጥ አለመረጋጋት  ምክኒያት ጦርነቱን ሸሽተው  ከካርቱም ወደ ጎረቤት ሀገር ኢትዩጵያ የሱዳን ዜጎችን ጨምሮ የ23 ሀገራት የተለያዪ ሃገራት ዜጎች  እንደገቡና  ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እየሄዱ ይገኛሉ።

በዚህም የምዕራብ ጎንደሯ የፍቅር ከተማ መተማ ዮሃንስ  ከተማ እንግዶቿን እያስተናገደች ሲሆን በቀን ከ15-20  የሚሆኑ መኪናዎች ወደ ጎንደር እየሄዱ ይገኛሉ ። በዚህ የጦርነት ስጋት ሺሽትም  ህፃናት፣ ሴቶች  እና አቅመ ደካሞች ይገኙበታል። የመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላትም ዜጎች ያለምንም እንግልት ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እንዲደርሱ ሰብአዊ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሆነ በቦታው ተገኝተን አረጋግጠናል ሲል የምዕራብ ጎንደር ዞን ኮምኒኬሽን ዘግቧል።

@Addis_Mereja
16.1K views00:43
Buka / Bagaimana
2023-04-26 09:31:38 ሰበር ዜና

በታንዛኒያ ዛንዚባር ደሴት በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሰላም ውይይት ዛሬ ተጀመረ።

በታንዛኒያ የሰላም ድርድር ዛሬ ማለዳ መጀመሩን በስፍራው የነበሩ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በውይይቱ ላይ የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች ስድስት ሰዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በመንግስት በኩል ወደ ታንዛኒያ የተጓዘው የልዑካን ቡድን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እንደሚገኙበት ቢቢሲ ዘግበዋል።

በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኩል አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር መሃመድ ሃሰን እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ዋና አዛዥ አማካሪ ሚስተር ጂሬኛ ጉዳታ እና አቶ አብዲ ጠሃ እና ሌሎችም መገኘታቸውን ፋስት መረጃ ከቢቢሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ሁለቱም ተደራዳሪ አካላት ንግግር ስለመጀመሩ ማረጋገጫ ቢሰጡም ዝርዝር መረጃ ይፋ አላደረጉም ፤ የታንዛኒያ ባለስልጣናትም ስለድርድሩ የተለየ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

@Addis_Mereja
18.0K viewsedited  06:31
Buka / Bagaimana
2023-04-25 09:43:08 “የሱዳንን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ”- ጄነራል ዳጋሎ

ራፒድ ሰፖርት ፎርስ (አር.ኤስ.ኤፍ) ተብሎ በሚጠራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ዋና አዛዥ ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ “የሱዳንን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ” አሉ።

ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዙሪያ ከስካይ ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ “አሁን ላይ እየተዋጋን ያለነው ከሱዳን ጦር ጋር ሳይሆን ከቅጥረኛ ኃይሎች ጋር ነው፤ ምክንያቱም 90 በመቶ የሱዳን ጦር ከጥቅም ውጪ ሆኗል” ብለዋል። ዳጋሎ አክለውም፤ “ከዚህ በኋላ ከሱዳን ጦር ዋና አዛዣ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ተቀምጦ መነጋገር ምንም ዋጋ እንደሌለውና አልቡርሃን ከዚህ በኋላ ያለው አማራጭ እጅ መስጠት ብቻ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

“ጦርነት አልፈልግም ነበር፣ ከጦርነት ይልቅ ሰላም እና መረጋጋትን ነው የምመርጠው” ያሉት ዳጋሎ፤ “ወደ ጦርነት እንድንገባ የገፋፋን አልቡርሃን ነው፤ አሁን ግን እጁ ላይ ምንም አልቀረለትም” ሲሉም ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉ የተጠየቁት ሃሜቲ፤ “እኔ የሱዳን ህዝብ አንድ አካል ነኝ፤ ካርቱምን ለቀቄ ወደየትም መሄድ አልችልም፤ እዛው ጦር ግንባር ላይ ነኝ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የሱዳን መከላከያ ሰራዊት በበኩሉ በዛሬው እለት በቃል አቀባይ ጽህፈት ቤቱ በኩል ጦርነቱን አስመልክቶ መግለጫ የሰጠ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በሱዳን ያለው ሁኔታ እየተረጋጋ መሆኑን እና የሱዳን ጦር የካርቱም የመኖሪያ አካባቢዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን ከሱዳን ከማስወጣት ጋር በተያያዘ ከሀገራት መሪዎች ጋር ግንኙነት እየተደረገ መሆኑን እና የማስወጣት ሂደቱ አሁን ባለበት ሂደት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

@Addis_Mereja
17.9K views06:43
Buka / Bagaimana
2023-04-24 10:13:12 የኢትዮጵያ መንግስት ከ“ኦነግ ሸኔ” ጋር በመጪው ማክሰኞ ድርድር እንደሚጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታወቁ

በትናንት እለት የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እንዲያበቃ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በተዘጋጀ የሽልማት እና የእውቅና መርሃ ግብር  ተካሂዷል።

በዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ ከሚጠራው “ኦነግ ሸኔ” ጋር የሚያደርገውን ድርድር፤ ማክሰኞ ሚያዝያ 17፤ 2015 በታንዛንያ እንደሚጀምር ጠ/ሚ አብይ አህመድ አስታውቀዋል። የሁሉም ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች፤ በትግራይ ክልል የሰፈነውን “የሰላም ጅማሮ በተግባር ለማስቀጠል” በቀጣዮቹ ቀናት ወደ መቐለ እንደሚጓዙም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሲካሄድ የቆየውን የሰላም ንግግር በአመቻችነት ሲመሩ የቆዩት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ “ልዩ ሽልማት” አግኝተዋል። ከኦባሳንጆ ጋር በሰላም ንግግሮቹ ላይ “በደጋፊነት” የተካፈሉት ቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የቀድሞዋ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፑምዚ ለምላምቦ የኢትዮጵያ ካርታን ከወይራ ዘንጣፊ ጋር በጋራ የያዘ ቅርጽን እና የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

በሰላም ንግግሩ በታዛቢነት ሲሳተፉ የቆዩት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ሃና ቴት እና የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመርም ተመሳሳይ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

በትናንትናው መርሃ ግብር ማብቂያ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠ/ሚ አብይ አህመድ፤ በቀጣይ ሳምንት ውስጥ 2 ኩነቶች እንደሚከናወኑ አስታውቀዋል። ከሁለቱ ክንውኖች ውስጥ 1ኛው የኢትዮጵያ መንግስት ከ“ኦነግ ሸኔ” ጋር የሚያደርገው ድርድርን የተመለከተ እንደሆነ ጠ/ሚኒስትሩ ይፋ አድርገዋል።(ኢትዮጵያ-ኢንሳይደር)

@Addis_Mereja
17.8K views07:13
Buka / Bagaimana