Get Mystery Box with random crypto!

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል መሪው ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሱዳን ጦር የሚፈጽመውን የአየር | Addis መረጃ™

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል መሪው ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) የሱዳን ጦር የሚፈጽመውን የአየር ላይ ጥቃት እስካላቆመ ድረስ ለድርድር አንቀመጥም ብለዋል።

ጦሩ “በግዴለሽነት” ሃይላችን በቦምብ እየደበደበ ነው ያሉት ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ፥ የተኩስ አቁም ስምምነቱ መጣሱን አብራርተዋል። “ሱዳን እንድትፈራርስ አንፈልግም” በማለትም የጀነራል አልቡርሃን ጦር ግጭት እያባባሰ ነው ስሉ ከሰዋል።

በጎረቤት ሀገራት፣ በአሜሪካ እና በመንግስታቱ ድርጅት አማካኝነት የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከሀሙስ ምሽት ጀምሮ ለ72 ስአት እንዲራዘመ መደረጉ ይታወሳል። ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎም በደቡብ ሱዳን ከጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ጋር ፊት ለፊት ለመደራደር ፍላጎት ማሳየታቸው አይገለጽም።

ይሁን እንጂ ሄሜቲ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ የሱዳን ጦር በቦምብ መደብደቡን እስከቀጠለ ድረስ ድርድር የሚታሰብ ጉዳይ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል። የተኩስ አቁሙ ተገባራዊ ሆኖ ግጭቱ ከበረደ በኋላ ግን ለመደራደር ዝግጁ ነኝ ማለታቸው ተዘግቧል።

“ከአልቡርሃን ጋር የግል ጸብ የለኝም” ያሉት ሄሜቲ፥ ይሁን እንጂ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ታማኝ ደጋፊዎች መሰብሰባቸውን በመጥቀስ በከሃዲነት ከሰዋቸዋል። በ2019 አልበሽርን ከአልቡርሃን ጋር በመሆን ያስወገዱት ሄሜቲ፥ “የሲቪል አስተዳደር ነገ ሳይሆን ዛሬ እንዲመሰረት እፈልጋለሁ” ብለዋል።ይሁን እንጂ በ2021 ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ላይ በተደረገው መፈንቅለ መንግስት ተሳትፎ እንዳላቸው የሚጠቅሱ ተንታኞች፥ የአሁኑ ጦርነት የሲቪል አስተዳደር ከመሻት የመነጨ እንዳልሆነ ያነሳሉ።
 
@Addis_Mereja