Get Mystery Box with random crypto!

Addis መረጃ™

Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™ A
Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™
Alamat saluran: @addis_mereja
Kategori: Berita
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 56.80K
Deskripsi dari saluran

@Addis_Mereja ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹
.
⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬
⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬

መረጃዎችን ለመላክ @Adis_Merejaa_bot

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


Pesan-pesan terbaru 2

2024-03-26 21:01:53
#ኢፍጧር በመስቀል አደባባይ ነገ ስለ ሚካሄድ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል።

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመስቀል አደባባይ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር  ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን

- ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ   ኦሎምፒያ

- ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ  አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች  አጎና ሲኒማ፤ለሌሎች ተሸከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡

- ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች  በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ

- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ

- ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ

- ከአዋሬ አካባቢ በካሳንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንትኔታል አካባቢ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጧር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ ይደረጋሉ።

በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅመ ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው ተብሏል።

ኅብረተሰቡ ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

@Addis_Mereja
13.3K viewsedited  18:01
Buka / Bagaimana
2024-03-15 22:40:19 ታግተው የነበሩ አምስት የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች መገደላቸው ተነገረ!

ለሁለት ሳምንት ያህል ታግተው የነበሩ አምስት የወንጂ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞች ተገድለው መገኘታቸውን የፋብሪካውን አንድ ኃላፊ ለቢቢሲ ገለጹ።ስማቸውን እንዳይጠቀስ የጠየቁት የስኳር ፋብሪካው ኃላፊ የአምስቱ ሠራተኞች አስከሬን ዛሬ ጠዋት መጋቢት 6/2016 ዓ.ም. መገኘቱን ገልጸዋል።

አስከሬናቸው ከፋብሪካው ማሳ ወጣ ብሎ ጨካ በሚባል የገጠር አካባቢ ነው የተገኘው።ከተገደሉት መካከለ ሦስቱ ሠራተኞች ከወንጂ አካባቢ ሲሆኑ፣ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በዛሬው ዕለት መፈጸሙ ተገልጿል።ሌሎቹ ሁለቱ ሠራተኞች አንደኛው ከአዳማ የመጣው ሲሆን ቀብሩ ዛሬ የሚፈጽም ሲሆን፣ እንዲሁም ሌላኛው ከደሴ የመጣው ግለሰብ አስከሬን ወደ ስፍራው ተልኳል ተብሏል።

አራቱ ሠራተኞች በፋብሪካው ውስጥ በትራክተር ኦፕሬተርነት ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ እና ዕድሜያቸው ከፍ ያለ እንደሆኑም እኚሁ የፋብሪካው ኃላፊ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ሌላኛው የኤሌክትሪክ ሠራተኛ (ፎርማን) ወጣት ሲሆን በቅርብ የተቀጠረ እና ለአንድ ዓመት ያህል በፋብሪካው አገልግሏል።

አንደ ኃላፊው ከሆነ ግለሰቦቹ ከሁለት ሳምንታት በፊት የአዳር ስር ላይ ምሽቱን አሳልፈው ጥዋት ላይ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ዶዶታ ከሚባለው ፋብሪካው ከሚገኝበት ስፍራ በታጣቂዎች ታግተው ተወስደዋል።ኃላፊው፣ ሠራተኞቹን ያገቷቸው ሰዎች ገንዘብ ጠይቀው እንደነበር? ወይም የጠየቋቸው ጉዳዮች እንዳሉ ዝርዝሩን እንደማያውቁ አስረድተዋል።

ነገር ግን ፋብሪካው ከአጋቾቹ በኩል ምንም እንዳልተጠየቀ ገልጸው፣ ወዲያውኑ ለመንግሥት አካል ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።ፓሊስም ሠራተኞቹን ለማስለቀቅ እየተከታታለ እንደነበር የገለጹት ኃላፊው፤ ነገር ግን አስከሬናቸው ዛሬ ጥዋት 2 ሰዓት አካባቢ ተገኝቷል ብለዋል።ስለ ግድያው እንዴት? እና ስንት ሰዓት? ተፈጸመ የሚለውን ባያውቁም ምናልባትም ትናንት ምሽት ተገድለዋል ብለው እንደሚጠረጥሩ የተናገሩት ኃላፊው ሰራተኞቹ መገደላቸውን ሰምተው ወደ አካበቢው ሲሄዱ አስከሬናቸውን አግኝተናል ብለዋል።

በፋብሪካው እገታ ሲያጋጥም የመጀመሪያ መሆኑን እና እስካሁን ባለው ሁኔታ ሰላማዊ እንደነበርም ኃላፊው አስረድተዋል።በእገታው ዙሪያ ቢቢሲ የተለያዩ የመንግሥት ኃላፊዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ለማናገር እየሞከረ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃዎችን ስናገኝ እናካትታለን።በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ አቅራቢያ ከአዲስ አበባ 110 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የወንጂ ስኳር ፋብሪካ በ1946 ዓ.ም. ኤች.ቪ.ኤ በተባለ የኔዘርላንድስ ተቋም እና በኢትዮጵያ መንግሥት የጋራ ባለቤትነት የተቋቋሙ በአገሪቱ ቀዳሚ የስኳር ፋብሪካ ነው።

ወታደራዊው መንግሥት ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግሥት ባለቤትነት ስር መግባቱ ይታወሳል።ወንጂ ስኳር ፋብሪካ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 496/2014 ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ ከተደረጉት አምስት ስኳር ፋብሪካዎች መካከከል አንደኛው ነው።

@Addis_Mereja
15.5K viewsedited  19:40
Buka / Bagaimana
2024-03-15 11:04:24
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና ሰዋሰው መልቲሚዲያ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

ሁለቱ አካላት በሙዚቃዉ ዘርፍ እና በኤቨንቶች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ነው የተስማሙት።


ከአንድ መቶ በላይ ድምፃዉያንን እና ሙዚቀኞችን በማስፈረም እየሰራ የሚገኘው ሰዋሰዉ መልቲሚዲያ እና በቴሌኮም ዘርፍ ላየ ተሰማርቶ የሚገኘው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሙዚቃ አልበሞች እና በኤቨንቶች ዙሪያ በጋራ ለመስራት በዛሬዉ እለት ተፈራርመዋል።

ከሰዋሰዉ ድምፃዉያን መካከል አንዱ የሆነዉ እና ከፋሲካ ፆም በኋላ የሚለቀቀዉን የአማኑኤል ሙሴ አልበምንም ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ የስፖንሰርሺፕ ድርሻዉን መዉሰዱ በዛሬዉ እለት ይፋ ተደርጓል።

በዝናር ዜማ የድምፃዉያን ስብስብ የሚታወቀው የአማኑኤል ሙሴ ‘’ጥቁር ዉሃ’’የተሰኘዉ አልበምም በሳፋሪኮም አጋርነት በሰዋሰዉ አፕ የሚለቅቅ መሆኑ ተነግሯል።

ከዚህ በተጨማሪ የሌላ ሴት ድምፃዊ አልበምን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስፖንስር እንደሚያደርግ የተነገረ ሲሆን፤ የድምፃዊቷን ማንነት ግን ይፋ ከማድረግ ተቆጥበዋል።

ድምፃዉያኑ በመልቲሚዲያው በኩል ለአልበማቸዉ ከሚያገኙት ገንዘብ በተጨማሪ ከስፖንሰር አድራጊዉ ካምፓኒም ክፍያ እና የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን የሚያገኙ ይሆናል ተብሏል።

የሰዋሰዉ መልቲሚዲያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀብቱ ነጋሽ ድምፃዉያን የስራቸውን ዋጋ እንዲያገኙ ከዚህም በላይ መስራት ይጠበቅብናል ያሉ ሲሆን ፣ እንደ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ያሉ ካምፓኒዎች ወደ ሀገራችን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ መቀላቀላቸዉ ዘርፉን በሚገባ ይደግፈዋል ብለዋል።

@Addis_Mereja
12.6K viewsedited  08:04
Buka / Bagaimana
2024-03-13 16:48:14
ፒያሳ ዶሮ ማነቂያ መፍረስ ጀምሯል

@Addis_Mereja
14.9K viewsedited  13:48
Buka / Bagaimana
2024-03-11 11:57:22
በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ የተነሳው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋል!

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  በዛሬው እለት የእሳት አደጋ ደርሷል። አደጋው ሲቀሰቀስ ከህንጻው ያልወጡ አራት ተማሪዎች የነበሩ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተማሪዎቹ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው መውጣት መቻላቸው ተነግሯል፡፡

በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ  ቢዝነስና ኢኮኖሚ ፉክልቲ በተለምዶ ኤፍቢ ግቢ በተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ ላይ ማለዳ 2:30 አደጋው መነሳቱ እና የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን  የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን አስታውቋል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር አራት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት አምቡላንስ ከ32 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደረጉት ርብርብ እሳቱን በፍጥነት መቆጣጠር መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቭዥን ተናግረዋል፡፡በአደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም። የአደጋው መንስኤ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን አቶ ንጋቱ ጨምረው ተናግረዋል።

Via Bistat FM
@Addis_Mereja
16.0K viewsedited  08:57
Buka / Bagaimana
2024-03-11 11:57:22
ረመዳን ሙባረክ!

በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ የረመዳን ወር ነገ ሰኞ march 11 እንደሚጀምር ታውቋል::

@Addis_Mereja
14.2K viewsedited  08:57
Buka / Bagaimana
2024-03-09 12:36:17 የሎተሪ አሸናፊ ባለመቅረቡ ስምንት ሚሊዮን ብር ተመላሽ መደረጉ ተገለጸ

እያንዳንዳቸው የአራት ሚሊዮን ብር ዕጣ ያላቸው ሁለት የሎተሪ ቲኬቶች አሸናፊዎች ባለመቅረባቸው ስምንት ሚሊዮን ብር ዛሬ የካቲት 29/ 2016 ዓ.ም ተመላሽ መደረጉን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አስታወቀ።

እነዚህ ሁለት ዕጣዎች ብሔራዊ ሎተሪ ከሚያሳትማቸው ከፍተኛ ዕጣ የሆነው 20 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ቲኬቶች መሆናቸውን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ዳይሬከተር አቶ ቴዎድሮስ ንዋን ለቢቢሲ ገልጸዋል።

በእንቁጣጣሽ ሎተሪ ከቀረቡት አምስት ቲኬቶች ሶስቱ ቀርበው 12 ሚሊዮን ብር ሁለት አሸናፊዎች ቢረከቡም የቀሪዎቹ ሁለት ቲኬቶች አሸናፊዎች ባለመቅረባቸው ገንዘቡ ወደ ተቋሙ ገብቷል ብለዋል።

ጳጉሜ 2015 ዓ.ም የወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ የሁለቱ ቲኬቶች ወይም የስምንት ሚሊዮን ብር አሸናፊ በቀን ስራ የሚተዳደር አንድ ግለሰብ ሲሆን ዕጣው ከወጣ ከሶስት ወር በኋላም ወስዷል።

ሌላኛው አሸናፊ የቀን ሰራተኛው የሚሰራበት መኪና አሽከርካሪ የሆነ ግለሰብ ሲሆን መስከረም ወር መጨረሻ ላይ መጥቶ የአራት ሚሊዮን ብር ሽልማቱን ወስዷል።

በ2010 ዓ.ም የወጣው 20 ሚሊዮን ብር የሚያስገኘው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ በተመሳሳይ መልኩ ስምንት ሚሊዮን ብር ዕጣ ያላቸው ሁለት የሎተሪ ቲኬቶች የያዙ አሸናፊዎች አልቀረቡም።

የዕጣው አሸናፊዎች አለመቅረባቸውን በተመለከተ በሚዲያ ከተነገረ በኋላ ጊዜው ሊያልፍ አምስት ቀን ሲቀረው አንድ ግለሰብ ሶስቱን ቲኬቶች አቅርቦ 12 ሚሊዮን መቀበሉን አስረድተዋል።

የዕጣ አሸናፊዎች መጥተው ገንዘባቸውን አለመውሰድ በተደጋጋሚ እንደሚያጋጥም የሚገልጹት አቶ ቴዎድሮስ በዚህ አጋጣሚም ገንዘቡን የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ተመላሽ ያደርገዋል ብለዋል።

“ህብረተሰቡ ሎተሪ የመግዛት ከፍተኛ ፍላጎት አለው። የዚያን ያህል ደግሞ የማያዩ በርካታ ደንበኞች አሉ” ብለዋል።

በእንቁጣጣሽ የሎተሪ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ዕጣ ዓይነቶችም በተደጋጋሚ ይህ እንደሚያጋጥምም ገልጸዋል።

@Addis_Mereja
14.0K viewsedited  09:36
Buka / Bagaimana
2024-03-08 09:08:47
ፐርፐዝ ብላክ  የቢጂአይ ኢትዮጵያን  ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ  እንዳይሸጥ እና  የባንክ አካውንት እንዳይንቀሳቀስ  በፍርድ ቤት አሳገደ


ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ በዛሬው እለት በከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሃ ብሄር ምድብ ችሎት የቢጂአይ ኢትዮጵያ  የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችና  የባንክ አካውንቶች እንዳይንቀሳቀሱና ገንዘብ እንዳይሰወርብኝ በሚል ባቀረበው የእግድ ጥያቄ መሰረት ፍርድ ቤቱ አቤቱታውን ተቀብሎ  1, 519,000000 (አንድ ቢሊዮን አምስት መቶ አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን) ዛሬን  ጨምሮ ለቀጣይ ሀያ ቀናት ቢጂአይ የተጠቀሰውን ብር እንዳይንቀሳቅስ እግድ ጥሏል።


    እንዲሁም    በአመልካችና በተጠሪ መካከል እኤአ በ15/06/2023 (08/10/2015) በተፈረመ የሽያጭ ውል የተጠሪን ዋና መስሪያ ቤትና ተጨማሪይዞታውን በአጠቃላይ ስፋቱ 29 ሺህ 896.51  ካ .ሜ  የሆነ ቦታ ለሶስተኛ ወገን ቢጂአይ እንዳይሸጥ ወይም እንዳያስተላልፍ እግድ ወጥቶበታል።

@Addis_Mereja
14.2K views06:08
Buka / Bagaimana
2024-03-05 09:21:27
ነዳጅ በነበረበት ይቀጥላል

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በካቲት ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ በመጋቢትም እንደሚቀጥል ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

@Addis_Mereja
13.3K viewsedited  06:21
Buka / Bagaimana
2024-03-02 10:18:37
መልካም በዓል ይሁንሎ።

በዓሉ የህዝብ ነበር

@Addis_Mereja
13.7K viewsedited  07:18
Buka / Bagaimana