Get Mystery Box with random crypto!

#ኢፍጧር በመስቀል አደባባይ ነገ ስለ ሚካሄድ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል። በነገው ዕለት በአዲ | Addis መረጃ™

#ኢፍጧር በመስቀል አደባባይ ነገ ስለ ሚካሄድ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል።

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመስቀል አደባባይ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር  ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

- ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን

- ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ   ኦሎምፒያ

- ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ  አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች  አጎና ሲኒማ፤ለሌሎች ተሸከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡

- ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች  በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ

- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ

- ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ

- ከአዋሬ አካባቢ በካሳንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንትኔታል አካባቢ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጧር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ ይደረጋሉ።

በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅመ ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ነው ተብሏል።

ኅብረተሰቡ ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።

@Addis_Mereja