Get Mystery Box with random crypto!

Addis መረጃ™

Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™ A
Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™
Alamat saluran: @addis_mereja
Kategori: Berita
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 56.80K
Deskripsi dari saluran

@Addis_Mereja ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹
.
⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬
⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬

መረጃዎችን ለመላክ @Adis_Merejaa_bot

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


Pesan-pesan terbaru 6

2024-01-18 19:30:35
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አዉሮፕላን ለበረራ በማኮብኮብ ላይ ሳለ አደጋ አጋጠመዉ!

ዛሬ እኩለ ቀን ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ መቐለ ሊያመራ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦንባርዲየር አውሮፕላን አደጋ ደረሰበት፡፡

አውሮፕላኑ በጎማው ላይ በገጠመው ችግር ከመንደርደሪያ መስመሩ ወጥቶ ጉዳት እንደደረሰበት የዘገበው ካፒታል በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ጠቁሟል።

Via Capital
@Addis_Mereja
12.6K viewsedited  16:30
Buka / Bagaimana
2024-01-16 22:50:07 የነዳጅ ድጎማ መጠን ላይ ማሻሻያ ተደረጓል

#Ethiopia | የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ስጪ በሆኑ ተሽከርካሪዎች ላይ የነዳጅ ድጎማ መጠን ላይ በተደርገ ማሻሻያ ቀደም ሲል ሲሰጥ ከነበረው የድጎማ መጠን ዝቅ አንዲል መደረጉን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የነዳጅ ድጎማ መጠን ላይ ማሻሻያ የተደረገው በአገር አቋራጭ አውቶብሶች ፣የከተማ አውቶብሶች አና ፐብሊክ ባስ አንዲሁም ሚዲባስ፣ሚኒባስ፣ታክሲዎችና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ መሆኑን ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መረጃ ገልጿል፡፡

በየስድስት ወሩ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች የድጎማ መጠን ማስተካከያ የሚደረግ ሲሆን÷ ከጥር 1 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016ዓ.ም ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት ለቤንዚን ተጠቃሚ አገር አቋራጭ አውቶብሶች ፣የከተማ አውቶብሶች እና ፐብሊክ ባስ ብር 22.36 በሊትር ሲሰጥ የነበረውን ድጎማ ወደ 19.16 በሊትር ዝቅ እንዲል፣ ለነጭ ናፍጣና ለኬሮሲን ሲሰጥ የነበረው ብር 23.21 በሊትር ድጎማ በሊትር 19.89 ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡

እንዲሁም የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ ሚዲባስ፣ሚኒባስ፣ ታክሲዎችና ባለሶስት እግር የሚሰጠው ድጎማ በየሶስት ወሩ የሚከለስ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ከጥር 1 ቀን 2016ዓ.ም እስከ መጋቢት 30 ቀን 2016ዓ.ም ድረስ ለቤንዚን ተጠቃሚዎች ሲስጥ የነበረው ብር 12.78 በሊትር ድጎማ ወደ 6.39 በሊትር፣ ለነጭ ናፍጣና ለኬሮሲን ሲስጥ የበነረው የብር 13.27 ድጎማ ወደ ብር 6.63 በሊትር ተቀናሽ እንዲሆን የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

@Addis_Mereja
14.2K viewsedited  19:50
Buka / Bagaimana
2024-01-15 14:36:31
የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ቀብር በኢትዮጵያ እንደሚፈጸም ተነገረ!

በእሁድን በኢቢኤስ ፕሮግራም አዘጋጅነትና አቅራቢነት ተወዳጅነትን ያተረፈው አንጋፋው የራዲዮና ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ አስፋው መሸሻ አስከሬን ረቡዕ ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ቤተሰቦቹ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት የሥንብት ሥነስርዓት እንደሚካሄድ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን አስታዉቋል፡፡

የፊታችን ሃሙስም ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም በሜሪላንድ በሚገኘው መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን የፍትሃት ሥርዓት እንደሚከናወንለትና ቅዳሜ ጥር 11 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የአስከሬን ሽኝት ይደረግለታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

በአዲስ አበባም በቀብር ሥነስርዓቱ አፈጻጸም ዙሪያ በአገር ውስጥ ኮሚቴ ተዋቅሮ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን የቀብሩን ቀንና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች በይፋ በሚሰጥ መግለጫ እንደሚነገር ኮሚቴው አሳውቋል።ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ባደረበት ህመም በህክምና ሲታገዝ ቆይቶ ለህክምና በሄደበት በአሜሪካ ዋሽንግተን ቅዳሜ ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ለሊት ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

[ዳጉ ጆርናል]
@Addis_Mereja
12.7K viewsedited  11:36
Buka / Bagaimana
2024-01-14 15:55:39
አምባሳደር ሆቴል ፊቱን ወደ ቤቶች ግንባታ በማዞር በሆቴል ዘርፉ ያለዉን ስራውን አቆመ

አምባሳደር ሆቴል ስራዉን በማቋረጥ ፊቱን ወደ ቤቶች ልማት ማዞሩን አሳዉቋል። የአምባሳደር የንግድ ድርጅቶች ከሚያስተዳድራቸው የንግድ ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነውና በዘርፉ ከ 15 ዓመታት በላይ የቆየዉ አምባሳደር ሆቴል ከረቡዕ ጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ስራዉን ማቋረጡን አሳዉቋል።

የአምባሳደር የንግድ ድርጅቶች ከጥንስሱ ጀምሮ የሚያስተዳድራቸውን የንግድ ዘርፎች በጥልቀት በማጥናት የማስፋፋት እና የንግድ ዘርፍ ለውጦችን ሲያደርግ የቆየ ተቋም መሆኑን ገልጿል።

የአምባሳደር ንግድ ሥራዎች መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሰዒድ መሐመድ አስፈፃሚ ከካፒታል ጋር ባደረጉት ቆይታ በአምባሳደር ሆቴል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በማቆም ሌሎች የንግድ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አሳዉቀዋል።

ከዚህ ቀደም ይታወቅበት የነበረውን የሆቴል ዘርፍ በመተዉ ፊቱን ወደ አፓርትመንትና ሆስፒታል አዙሯል። ከዚህ ቀደም 48 አፓርትመንት እንዳለዉ ያሳወቀዉ ድርጅቱ አሁንም ተጨማሪ 4 ብሎኮችን ግንባታዎች አካሄዷል።

በተጨማሪም አቶ ሰኢድ እንደተናገሩት በአምባሳደር ጃንጥላ ስር ያሉ ዘርፎች በአዳዲስ ስራዎች ላይ ኢንቬስት ይደረጋሉ ብለዋል።

እኤአ ከ 2008 ጀምሮ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ ፊት ለፊት የሚገኘው እና በሆቴል ኢንዱስትሪ ውስጥ ታዋቂነትን ያተረፈዉ አምባሳደር ሆቴል ከአሁን በኃላ በሌላ ዘርፍ ይመጣል ተብሏል ።

Via Capital Newspaper
@Addis_Mereja
13.0K viewsedited  12:55
Buka / Bagaimana
2024-01-13 17:36:10 https://t.me/+3ybt14MIvf40MDE0
12.6K views14:36
Buka / Bagaimana
2024-01-13 05:17:19
ሀዋሳ ሀይሌ ሪዞርት ቲክቶከሩን ናፒ ወደ ሆቴሉ ገብቶ እንዳይቀርፅ ከለከለ

ሐዋሳ የሚገኘው ኃይሌ ሪዞርት ባወጣው መግለጫ ናፒ  የተባለ ቲክቶከር ለሆቴሉ ተጠቃሚዎች ምቾት ስለሚነሳ ወደ ሆቴሉ ገብቶ እንዳይቀርፅ መግቢያ በር ላይ እንዳይገባ መከልከላችንን ለህዝብ ማሳወቅ እንወዳለን ብሏል።

ይህ ሰው ቪአይፒ እንግዶቻችን ጨምሮ ምቾት እንዳይሰማቸው እና ስጋት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ስለሆነ የእንግዶቻችንን እና የስራ ባልደረቦቻችንን ምቾት እና ደህንነት እናከብራለን፣ እናም ማንኛውም ሰው የስነምግባር ደንባችንን የማያከብር ከሆነ ወደ ግቢያችን እንዳይገባ የመከልከል ፖሊሲ አለን። ይህ ክስተት በእንግዶቻችን እና በህዝቡ ላይ ላደረሰው ማንኛውም ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን ሲል ሃይሌ ሪዞርት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

@Addis_Mereja
15.6K viewsedited  02:17
Buka / Bagaimana
2024-01-12 18:56:15 የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ በአማራ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት 61 የጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ መውደማቸውንና 39 የሚኾኑት በከፊል መጎዳታቸውን ትናንት በጄኔቫ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

የእንቅስቃሴ ገደቦች በሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ላይ መሰናክል መኾናቸውን የገለጡት ዶ/ር ቴድሮስ፣ በመንግሥት ኃይሎችና በታጣቂ ወገኖች መካከል በሚደረጉ ውጊያዎች ምክንያት በሚፈጠር የመንገድ መዘጋት ወይም የጤና ተቋማት ውድመትና መጎዳት፣ በጤና አገልግሎት ላይ ጫና እያሳደረ ነው ብለዋል።

ግጭት፣ ድርቅና መፈናቀል በሰሜን ኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ ርሃብ እና የበሽታ መቀስቀስ እያስከተሉ መኾኑንም ዶ/ር ቴድሮስ ገልጸዋል። ዶ/ር ቴድሮስ፣ በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል ሰሜን ምዕራብ አካባቢዎች ካለፈው ዓመት ሚያዚያ ጀምሮ በተከሰተው ግጭት የጤና ተቋማት ክፉኛ መጎዳታቸው አሳሳቢ መሆኑንም ተናግረዋል። የዓለም ጤና ድርጅት፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በሱዳን እና ጋዛ ሥራውን ለመስራት በርካታ መሰናክሎች እንደተደቀኑበትም ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

@Addis_Mereja
14.5K viewsedited  15:56
Buka / Bagaimana
2024-01-11 22:27:55
ቻይና  ሶማሊላንድ የሶማሊያ ግዛት ናት የሚል አቋም  እንዳላት ገልፃ የቀጠናው ሀገራት ጉዳያቸውን  በወዳጅነት እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ  ሊፈቱ ይገባቸዋል ብላለች

"ቻይና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር አላማዎችን እና መርሆዎችን ለማስከበር የቆመች ሲሆን ሀገራትን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነትን በማስጠበቅ ረገድ ትደግፋለች" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ ተናግረዋል።

ማኦ “ሶማሊላንድ የሶማሊያ አካል ነች" ብለዋል
@Addis_Mereja
14.9K viewsedited  19:27
Buka / Bagaimana
2024-01-11 22:14:29 https://t.me/+SLfkHSMAY79kZWY0

Join the group get ur free product
12.7K viewsedited  19:14
Buka / Bagaimana
2024-01-11 22:07:54
ከላችንን ከታጠብን ቡሀላ ከዉነታችንን ማለስለስ ግድ ነዉ

ከድርቀት እና ከመሰነጣጠቅ ለመከላከል አፀባራቂ ቆዳ እንዲኖሮት ከ elegant cosmetics ይሸምቱ ከነፃ ትራንስፖርት ጋር
12.9K views19:07
Buka / Bagaimana