2024-02-15 18:52:36
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና (12ኛ ክፍል) የተፈታኞ ምዝገባ በሚመለከት ለሚዲያ አካላት ማብራሪያ ሰጥቷል።
የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ምን አሉ ?
- የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ለፈተና ከመቀመጣቸው በፊት የመመዝገቢያ መስፈርቱን ማሟላት አለባቸው። በተቀመጠው የጊዜ ገድብ ውስጥም መምዝገብ አለባቸው።
- ምዝገባዉ የሚከናወነዉ በበይነመርብ /Online Registration / አማካኝነት ሲሆን ከየካቲት 3 -30/2016 ዓ.ም
ይሆናል።
- በየደርጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ትኩርት ማድርግ ያለባቸውን ጉዳዮችም የሚከተሉት ናቸው ብለዋል ፦
1ኛ. ተፈታኞች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መምዘገብ አለባቸው። ከየካቲት 3 -30 /2016 ዓ.ም ብቻ።
2ኛ. ምንም አይነት ስህትት ማለትም የፆታ ߹የስም ስህተት߹የፎቶ ߹የትምህርት መስክ እና የመሳስሉት ችግሮች እንዳይፈጠሩ በትኩርት መስራት መቻል አለባቸው።
3ኛ. ከየካቲት 30 /2016 ዓ.ም በኃላ የሚመጣ ምዝገባ ተቀባይነት እንደሌለዉ ማወቅ አለባቸው።
4ኛ. የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወንው በተማሩበት ት/ቤት ይሆናል።
5ኛ. የግል ߹ የርቀት /የበይነ መርብ /ተፈታኞ ምዝገባ በክፍለ ከተማ ߹በወርዳና ትምህርት ፅ/ቤቶች ይሆናል።
Via Ethio FM
@
Addis_Mereja
25.3K viewsedited 15:52