Get Mystery Box with random crypto!

ዩክሬን በመጨረሻ ኔቶን እንደምትቀላቀል የኔቶ ዋና ጸኃፊ አረጋገጡ!! ሁሉም የኔቶ አጋሮች ዩክሬን | Addis መረጃ™

ዩክሬን በመጨረሻ ኔቶን እንደምትቀላቀል የኔቶ ዋና ጸኃፊ አረጋገጡ!!

ሁሉም የኔቶ አጋሮች ዩክሬን የህብረቱ አባል እንድትሆን ተስማምተዋል፤ አሁን ግን ዋናው ትኩረት ሀገሪቱ በሩሲያ ላይ የበላይነትን ማረጋገጥ ነው ሲሉ የኔቶ ዋና ፀሃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ተናግረዋል።

በጀርመን ራምስቴይን የአየር ኃይል ጣቢያ ከሚካሄደው የዩክሬን መከላከያ ቡድን ስብሰባ በፊት ሲናገሩ፣ በዩክሬን ያለው ጦርነት አንዴ ካበቃ ኪየቭ “አዳዲስ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያስችል መከላከያ” ሊኖራት ይገባል ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ዩክሬን የምዕራባውያን ወታደራዊ ጥምረት የሆነውን ኔቶ ለመቀላቀል በተደጋጋሚ ጥያቄ ብታቀርብም፣ ህብረቱ አስቸኳይ መፍትሄ አልሰጣትም።ከሩሲያ ጋር ጦርነት የገጠመችው ዩክሬን ኔቶን ለመቀላቀል ጥረቷን ቀጥላለች። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ያወጀችው ኔቶ ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት መስፋፋቱን እና ይህም ለደህንነቷ እንደሚያሰጋት ከገለጸች በኋላ ነበር።

ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት ከጦር መሳሪያ ጀምሮ በርካታ ድጋፍ እያደረጉ ያሉት አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራት በዩክሬን ኔቶን መቀላቀል ላይ ቁርጥ ያለ ውሳኔ አላሳለፉም።በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ስጋት የገባቸው ስዊድን እና ፊንላንድ ኔቶን ለመቀላቀል ጥያቄ አቅርበው፣ ፊንላንድ ወታደራዊ ጥምረቱን ተቀላቅላለች።
ሁለቱ ሀገራት ጥያቄ ያቀረቡት ቀደም ብለው የነበረ ቢሆንም በቱርክ ተቃውሞ ጥያቄያቸው ተጓትቶ ነበር።

የቱርክ ፖርላማ መፍቀዱን ተከትሎ ፊንላድ አባል ሆናለች። ነገርግን ቱርክ በስዊድን አሉ ከምትላቸው የኩርድ አማጺያን ጋር በተያያዘ ያቀረበችው ጥያቄ ስላልተመለሰ የስዊድንን የአባልነት ጥያቄ አላጸደቀችውም።

@Addis_Mereja