Get Mystery Box with random crypto!

Addis መረጃ™

Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™ A
Logo saluran telegram addis_mereja — Addis መረጃ™
Alamat saluran: @addis_mereja
Kategori: Berita
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 56.59K
Deskripsi dari saluran

@Addis_Mereja ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ 🇪🇹 🇪🇹
.
⏬ምርት እና አገልግሎቶን ለማስተዋወቅ ከፈለጉ⏬
⏬ ꜰᴏʀ ᴘᴀɪᴅ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ⏬

መረጃዎችን ለመላክ @Adis_Merejaa_bot

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


Pesan-pesan terbaru 13

2023-10-21 14:05:19
አሜሪካ በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ዜጎቿ በሙሉ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች፡፡

የአሜሪካ መንግስት በውጭ ሀገራት ለሚኖሩት ዜጎቹ ማስጠንቀቂያውን የሰጠው የሽብር ጥቃት ሊደርስባቸው ይችላል ሲል ነው፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫው አሁን ከምንጊዜም በላይ በመላው ዓለም ለሚኖሩት የአሜሪካ ዜጎች የሽብር ጥቃት የሚያሰጋበት ጊዜ ነው ሲል በጥብቅ አስጠንቅቋል፡፡
የእስራኤልና ሀማስን ከባድ ጦርነት ተከትሎ በመላው ዓለም የአሸባሪዎቹ ዝግጅት ከፍተኛ እንደሆነ ነው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያስታወቀው፡፡በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ሀገራት ማለትም ዮርዳኖስ፤ ኢራንና ሊባኖስ ጨምሮ በሌሎች የዓለም ሀገራት ተቃውሞው መቀጣጠሉ እየተዘገበ ነው፡፡

@Addis_Mereja
20.6K viewsedited  11:05
Buka / Bagaimana
2023-10-20 23:50:15
በጋዛ ተፈናቃዮችን አስጠልላ የነበረችው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የአየር ጥቃት አንደደረሰባት አስታወቀች

በጋዛ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ተፈናቃዮችን አስጠልላ የነበረችው የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በእስራኤል የአየር ጥቃት ተፈጽሞባታል። የፍልስጤም ባለስልጣናት እና የእየሩሳሌም ሀገረስብከት እንደገለጹት በተፈጸመው የአየር ጥቃት 16 ሰዎች ተገድለዋል።

የእስራኤል ጦር ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ ኢላማ አድርጎ ባደረሰው ጥቃት የቤተክርስቲያኗ አካል መጎዳቱን እና ሁኔታውን እየመረመረው መሆኑን ተናግሯል። የፍልስጤም ባለስልጣናት በቤተክርስቲያኗ 500 የሚሆኑ ሙስሊሞች እና ክርስሲያኖች ተጠልለው ነበር ብለዋል። እስራኤል ሀማስ ያደረሰባትን ጥቃት ተከትሎ የምትሰጠውን የአጸፋ ምላሽ ጋዛን በመክበብ አጠናክራ ቀጥላለች።

@Addis_Mereja
13.6K viewsedited  20:50
Buka / Bagaimana
2023-10-18 19:05:01
የኢሚግሬሽን ምክትል ዳይሬክተርን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸው ተሰማ

የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ታምሩ ገምበታን ጨምሮ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ሰዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው መታሰራቸው ተሰማ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰሞኑን መሆኑንና አቶ ታምሩ ገምበታ ግን ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. መሆኑ ታውቋል፡፡ የምክትል ዳይሬክተሩ ቤት በፍርድ ቤት የብርበራ ፈቃድ መበርበሩንና ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ሊቀርቡ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

የመንግሥት አስተዳደር ለውጥ ከተደረገ ጀምሮ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ አገልግሎት ተቋም ውስጥ የተለያዩ ለውጦች የተደረገ ቢሆንም፣ አንዳንድ የተቋሙ ሠራተኞች በድለላ ሥራ የተሰማሩ አካላት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በቁጥጥር ሥር ውለው በምርመራ ላይ እንዳሉም ይታወቃል፡፡

አገልግሎቱን በዋና ዳይሬክተርነት ይመሩ የነበሩት አቶ ብሩህተስፋ ሙሉጌታ፣ ምክትል ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ፍራኦል ጣፋና አቶ ታምሩ ገምበታን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከ3 ወራት በፊት ሐምሌ መጀመሪያ ሳምንት አካባቢ ከኃላፊነት ማንሳታቸው ይታወሳል፡፡

ተቋሙ ከፓስፖርትና መሰል አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ቅሬታ ሲቀርብበት መቆየቱንና ከዜጎች ከፍተኛ ገንዘብ በመቀበል በሕወጥ መንገድ ወደ ውጭ አገር ሲልኩ ነበር የተባሉ 16 የተቋሙ ሠራተኞች፣ እንዲሁም አምስት በአሠሪና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ስም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም ይታወሳል፡፡

በተያዘው ሳምንት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የተሰማው ምክትል ዳይሬክተሩን ጨምሮ ሌሎች ሰዎችም ከሙስና ጋር በተያያዘ መጠርጠራቸው ተገልጿል፡፡

(ሪፖርተር)
@Addis_Mereja
13.6K viewsedited  16:05
Buka / Bagaimana
2023-10-18 14:20:22
ጠ/ሚ ዐቢይ በወደብ ዙሪያ አማራጭ ብለዉ ከጠቀሷቸው ሀገራት ሁለተኛዋ ሶማሊያ ሀሳቡን ዉድቅ አደረገች

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ባሳለፍነዉ ሳምንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ወደብን እና የባህር በርን አስመልክቶ ያቀረቡት ሃሳብ በኤርትራ መንግስት ተቀባይነት እንዳላገኘ መዘገቡ ይታወሳል።

ጠ/ሚኒስትሩ በማብራሪያቸዉ ኤርትራ ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ ለኢትዮጵያ የባህርበር ማግኛ አማራጭ ሀገራት እንደሆኑ ገልጸዉ ነበር።

ብሉምበርግ በትናንትናው እለት ባወጣዉ መረጃ ደግሞ ሶማሊያ የቀይ ባህርን በተመለከተ ከኢትዮጵያ የተነሳዉን ሃሳብ ዉድቅ ማድድጓን ዘግቧል።

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ የባህር በር አለማግኘቷ ለወደፊት ግጭት መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዉ ፤ ቀጠናዊ መረጋጋትን ለማስጠበቅ ጉዳዩን ለመፍታት ጥረት እንዲደረግ መጠየቃቸዉ አይዘነጋም።

የዜና ምንጩ ሶማሊያ ይህንን ጥያቄ እንደማትቀበለዉ አስነብቧል። ሶማሊያ ስትራቴጅካዊ ንብረቶቿንን እንደምትቆጣጠርም በዘገባው ተጠቅሷል።ኢትዮጵያ የኤርትራን ነጻ ሀገርነት ተከትሎ ላለፉት ከሶስት አስርት አመታት በላይ የባህር በር አጥታ ቆይታለች።

@Addis_Mereja
13.8K viewsedited  11:20
Buka / Bagaimana
2023-10-17 23:44:36
"ብንሄድ ይሻለናል" ብላ ፖስት አድርጋ ራሷዋን ወሰደች

ብንሄድ ይሻለናል የሚል መልዕክት በፌስቡክ ገጿ ላይ ያሰፈረችው ወጣት ራሷ አጠፋች !

ናዝራዊት ተስፋዬ ትባላለች። ከሁለት ቀን በፊት ስንብት የሚመስሉ ልጥፎችን አጋርታ ዛሬ ራሷን ማጥፋቷ ተሰምቷል። ይሄ ድርጊት እየተለመደ መጥቷል። ይህቺ ነፍስ ብዙ መከራ ብቻዋን እንደታገለች፣እምባ ዘመዷ እንደሆነ፣የምታዋየው፣ልቧ የሚያርፍበት ሰው ማጣቷን ያሳብቃሉ ልጥፎቿ። ምንም ማድረግ ባንችል አጠገባችን ያሉ ሰዎችን እናስተውል፣የአንዳንዱ ችግር ''አይዞን'' በሚል ነጠላ ቃል ይቀረፋል። በሰው ረሃብ ቸነፈር የተገረፈ ስንቱ አለ? ብዙ የነገ ተስፋዎቻችንን አይነጠቁብን፤የአንዳችን መኖር ለሌላኛችን ነው!! የነፍሳችን ባለቤት ፈጣሪ ነውና እስከ ፈቀደልን ጊዜ እንቆይ!!

Via Tiblets Tesfaye Ritha
ነፍስሽ በሰላም ትረፍ Rest in peace

 @Addis_Mereja
13.5K viewsedited  20:44
Buka / Bagaimana
2023-10-16 20:38:07
ኤርትራ የባህር በር ጉዳይ ላይ ለድርድር እንደማትቀመጥ አስታወቀች

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተነሳዉ የባህር በር ጉዳይ ላይ፤ ኤርትራ ለድርድር እንደማትቀመጥ የኤርትራ መንግሥት የመረጃ ሚኒስትር አስታውቋል፡፡

የኤርትራ መንግሥት የመረጃ ሚኒስትር ዛሬ ባወጣው አጭር መግለጫ፤ “በቅርብ ጊዜ ስለ ውሃ እና ስለ ባህር በሮች እንዲሁም ተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳዮች የተነገረው እና የተባለው ቁጥር የለውም” ያለ ሲሆን፤ “በዚም ያልተገረመ ታዛቢ የለም” ብሏል፡፡

የኤርትራ መንግሥትም እንደኹልጊዜው በእንደዚህ ዓይነቱ ጉዳዮች ላይ ለውይይት እንደማይታደም ያስታወቀው ሚኒስቴሩ፤ ይህ ነገር ይመለከተናል የሚሉ ኹሉም አካላት ጉዳዩን እንዳይነኩት በመግለጫው ማሳሰቡን አዲስ ማለዳ ከሚኒስቴሩ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አርብ ጥቅምት 2/2016 ምሽት፤ በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በተላለፈውና ‹‹ከጠብታ ውኃ እስከ ባሕር ውኃ›› የሚል ርዕስ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ባደረጉት ገለጻ፤ ቀይ ባህርን አስመልክተው ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

በመግለጫቸውም፤ "በታሪክ፣ በጂኦግራፊ፣ በዘር (በብሄር) እና በኦኮኖሚ ምክንያቶች የቀይ ባህር ጉዳይ ይመለከተናል።" ያሉ ሲሆን፤ "ቀይ ባህር ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ እንጂ ቅብጠት አይደለም።

አባይና ቀይ ባህር የኢትዮጵያን ልማትና ጥፋት የሚወስኑ የኢትዮጵያ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ናቸው።" ብለዋል፡፡

@Addis_Mereja
14.3K viewsedited  17:38
Buka / Bagaimana
2023-10-15 17:47:04
የቀድሞው ትዊተር የአሁኑ ኤክስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከሃማስ ጋርግንኙነት ያላቸው አካውንቶችን ዘጋ!!

የቀድሞው ትዊተር የአሁኑ ኤክስ ሀማስ ባሳለፍነው ሳምንት ቅዳሜ እስራኤል ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከቡድኑ ጋር የተገናኙ አካውንቶችን መዝጋቱን አስታውቋል።

የማህበራዊ የትስስር ገጹ በተጨማሪም በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ ልጥፎችን የማስወገድ ወይም የመለየት እርምጃ መውሰዱን ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ሊንዳ ኦፊሰር ያሳሪኖ ተናግረዋል።

እርምጃው የመጣው የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የአውሮፓ ህብረት የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ነው። የአውሮፓ ህብረት ሀማስ ህገ-ወጥ ልጥፎችን እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ለማሰራጨት ኤክስን እየተጠቀመበት መሆኑን የሚጠቁሙ ምልክቶች እንዳሉ ተናግሯል። ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ከጥቃቱ በኋላ ማህበራዊ የትስስር ገጹ በአፋጣኝ ቡድን አቋቁሞ ሁኔታውን መፈተሹን ገልጸዋል።

@Addis_Mereja
12.9K viewsedited  14:47
Buka / Bagaimana
2023-10-14 12:41:09
"የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን" ሥነ-ስርዓት በትግራይ ክልል እየተከናወነ ነው!!

በፌደራል መንግስሥቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል በተካሄደው ደም አፍሳሽ ጦርነት ወቅት ሕይወታቸው ያለፉ ተዋጊዎችን ለመዘከር፤ "የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን" ሥነ-ስርዓት በትግራይ ክልል እየተከናወነ ይገኛል።

"የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን" ሥነ-ስርዓቱ በመቀለ ከተማ በሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት እየተከናወነ ሲሆን፤ በሥነ-ስርዓቱ ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገ/ማርያም (ዶ/ር)፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ የሰማእታት ቤተሰቦች እንዲሁም በጦርነቱ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው ታጋዮች ተገኝተዋል።

በመታሰቢያ ሃውልቱ ላይም የክልሉ አመራሮች፣ የትግራይ ተወላጆች፣ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እንዲሁም የተለያዩ አካላት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

በተመሳሳይ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በጦርነቱ ወቅት መስዋዕትነት የከፈሉ የትግራይ ሰማዕታትን ለማሰብ ሻማ የማብራት እና ሌሎች ሥነ ስርዓቶች እየተካሄዱ ይገኛል።

በትግራይ ደረጃ የሚከናወነው "የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን" ሥነ-ስርዓት ከትናንት ጥቅምት 2 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 5/2016 ባሉት ሦስት ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት በጊዜያዊ አስተዳደሩ ቁጥጥር ሥር ባሉ ኹሉም የክልሉ አካባቢዎች ይከናወናል።

@Addis_Mereja
15.0K viewsedited  09:41
Buka / Bagaimana
2023-10-10 22:03:39
መሀመድ ቢን ዛይድ ለፍልስጤም የ20 ሚሊየን ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግ አዘዙ

የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ለፍልስጤም በአስቸኳይ 20 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንዲደረግ አዘዙ።

ፕሬዝዳንቱ ባለፈው ቅዳሜ በጀመረው የሃማስ እና እስራኤል ግጭት ምክንያት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ፍልስጤማውያን መድረስ እንደሚገባ መናገራቸውን የሀገሪቱ ዜና አገልግሎት ዋም ዘግቧል።

ድጋፉ ለፍልስጤም ስደተኞች አስቸኳይ ድጋፍ በሚያቀርበው የመንግስታቱ ድርጅት ኤጀንሲ በኩል ይቀርባል ተብሏል። በሃማስ እና እስራኤል መካከል አራተኛ ቀኑን በያዘው ጦርነት ከ1 ሺህ 750 በላይ ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል።እስራኤል በጋዛ በቀጠለችው ድብደባም የሚያልፈው የሰው ህይወት እና የመኖሪያ ቀያውን ጥሎ የሚሸሸው እየተበራከተ ሄዷል።

የመንግስታቱ ድርጅትም በጋዛ ፈጣን ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች አለማቀፉ ማህበረሰብ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጥ ከጠየቀ ዋል አደር ብሏል።የሃማስ እና እስራኤል ግጭት እንዲቆምና ሁለቱም ወገኖች ወደ ንግግር እንዲመለሱ የጠየቀችው ኤምሬትስ ፈጣን የሰብአዊ ድጋፍ እንዲደረግ በመወሰን ቀዳሚ ሆናለች።

አቡዳቢ ሁለቱም ወገኖች ንጹሃንን ኢላማ ከሚያደርጉ ጥቃቶች እንዲታቀቡ አሳስባለች። ግጭቱ የፍልስጤም እና እስራኤልን የአመታት ውጥረት ለማርገብ የሚደረጉ ቀጠናዊ እና አለማቀፋዊ የዲፕሎማሲ ጥረቶችን ያስቆማል በሚልም ተቃውሞዋን ማሰማቷ ይታወሳል።

@Addis_Mereja
14.3K viewsedited  19:03
Buka / Bagaimana
2023-10-09 17:50:20
በ2015 የተፈተኑ ተማሪዎች ብዛት 845,099 ፤ 50 በመቶና በላይ ያመጡ 27,267 ተማሪዎች (3.2%) ብቻ ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ ፦

ከተፈጥሮ ሳይንስ ያለፉ 19,017 ተማሪዎች
ከማህበራዊ ሳይንስ ያለፉ 8,250 ተማሪዎች

በማታ የተፈተኑ 16,541 ያለፉ 12 ተማሪዎች ብቻ

በግል የተፈተኑ 169,502 ያለፉ 498 ተማሪዎች ብቻ

በመደበኛ የተፈተኑ 659,056 ያለፉ 26,757 ተማሪዎች ብቻ


- የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ት/ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች አንድም_ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም / ምንም ተማሪ አላሳለፉም። ይህም ማለት በሀገሪቱ ካሉትና የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑት ትምህርት ቤቶች 42.8 በመቶ የሚሆኑት አንድም እንኳን ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

27 ሺህ 267 ተማሪዎች በቀጥታ ፍሬሽ ማን ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ 160 ሺህ ገደማ ተማሪ በሬሜዲያል ይገባሉ።

#ውጤት

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች ነገ ጥዋት 12 ሰዓት ጀምሮ በዌብሳይት እና በSMS ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

@Addis_Mereja
14.8K viewsedited  14:50
Buka / Bagaimana