Get Mystery Box with random crypto!

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ቤቲንግ ቤቶች አይዘጉም ሲል አስታወቀ። የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በ | Addis መረጃ™

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ቤቲንግ ቤቶች አይዘጉም ሲል አስታወቀ።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳስታወቀው አንዳንድ ግለሰቦች በማህበራዊ ሚዲያ ቤቲንግ ሊዘጋ ነው በማለት የሚያሰራጩት መልእክት ፍጹም ስህተት ነው ብሏል።

አክሎም የስፖርት ውርርድ ጨዋታዎችም ሆነ ሎተሪን በተመለከተ ማንኛውም መረጃ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ማግኘት እንደሚቻል አስተዳደሩ ገልጻል።

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " ቤቲንግ " ሊታገድ መሆኑን የሚገልፁ በትክክል ምንጫቸው ያልተገለፁ ፅሁፎች ሲሰራጩ ተስተውሏል።

አንዳንድ ግለሰቦች በማህበራዊ ሚዲያ ቤቲንግ ሊዘጋ ነው በማለት የሚያሰራጩት መልእክት ፍጹም ስህተት መሆኑን እንገልፃለን " ያለው አስተዳደሩ " የስፖርት ውርርድ ጨዋታዎችም ሆነ ሎተሪን በተመለከተ ማንኛውም መረጃ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ብቻ ማግኘት እንደሚገባ አመልክቷል።

ከዚህ ቀደም ከ ' ቤቲንግ / ስፖርታዊ ውርርድ / ' ጋር በተያያዘ ፤ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲታገድ እየሰራ መሆኑን አሳውቆ እንደነበር ይታወሳል።

ሚኒስቴር መ/ቤቱ ፤ ከታዲጊዎች እና ወጣቶች ስብዕና ግንባታ እንዲሁም በተለያየ መንገድ ከሚያስከትላቸው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውሶች አንጻር ነው ዘርፉ ሊታገድ ይገባል በሚል እየሰራ እንደሆነ አሳውቆ የነበረው።

Via Ethio FM
@Addis_Mereja