Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በመቀሌ በአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ የመንሸራተት አደጋ | Addis መረጃ™

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በመቀሌ በአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ የመንሸራተት አደጋ እንዳጋጠመዉ አየርመንገዱ አስታወቀ!

በዛሬው ዕለት ከቀኑ በ06፡30 አካባቢ ከአዲስ አበባ ወደ በመቀሌ በረራ ያደረገው ET106 የመንገደኞች አውሮፕላን፤  በ08፡00 ሰዓት በአሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ካረፈ በኋላ የመንሸራተት እክል እንደገጠመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡

በጉዞው ላይ የነበሩ ሁሉም ሠራተኞች እና ተሳፋሪዎች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም መውረዳቸውን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል። የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የገለጸው አየር መንገዱ፤ ለተፈጠረው እክል ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።

@Addis_Mereja