Get Mystery Box with random crypto!

በጋዜጠኞች እስር ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሃገራት ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ሲፒጄ ገለጸ! ኢትዮጵያ | Addis መረጃ™

በጋዜጠኞች እስር ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሃገራት ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን ሲፒጄ ገለጸ!

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማሰር ከአፍሪካ ሃገራት ሶስተኛ ደረጃ መያዟን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች (ሲፒጄ) ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርቱ አስታውቋል። በአፍሪካ በታሳሪ ጋዜጠኞች ብዛት ቀዳሚውን ቦታውን የያዘችው የኢትዮጵያ ጎረቤት ኤርትራ ስትሆን፤ ግብጽ ሁለተኛ ቦታን ይዛለች።

ሲፒጄ ዓመታዊ ሪፖርቱን ባጠናቀረበት ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ገደማ፤ በመላው ዓለም የታሰሩ ጋዜጠኞች ብዛት 320 እንደነበር ገልጿል። ይህ ቁጥር ድርጅቱ መሰል ሪፖርቶች ማዘጋጀት ከጀመረበት ከ1985 ዓ.ም. ወዲህ በከፍተኛነቱ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ መሆኑንም ጠቁሟል። የ360 ጋዜጠኞች እስር የተመዘገበበት የፈረንጆቹ 2022 ዓመት፤ የምንጊዜውንም ከፍተኛ ቁጥር ያስተናገደ ነው።

በአፍሪካ እስካለፈው ህዳር መጨረሻ ድረስ ባለው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ፤ ቢያንስ 67 የሚሆኑ ጋዜጠኞች “ከስራቸው ጋር በተያይዘ ለእስር መዳረጋቸውን” ሲፒጄ በሪፖርቱ አመልክቷል። ከእነዚህ ጋዜጠኞች ውስጥ አስራ ስድስቱን በማሰር እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ በመጀመሪያ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ኤርትራ ናት።

[Ethiopia Insider]
@Addis_Mereja