Get Mystery Box with random crypto!

Ashara Media - አሻራ ሚዲያ

Logo saluran telegram asharamedia24 — Ashara Media - አሻራ ሚዲያ A
Logo saluran telegram asharamedia24 — Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
Alamat saluran: @asharamedia24
Kategori: Politik
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 5
Deskripsi dari saluran

ስልክ፥ 251984190114 / 251993111700

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru 8

2023-12-22 16:15:34
መረጃ ሸዋሮቢት! ..

በአሁን ሰዓት በሸዋሮቢት ጀግናው ፋኖ ከኦነጉ ብርሀኑ ጁላ ሙት ሰራዊት ጋር ከባድ ትንቅንቅ እያደረገ ይገኛል!
እነዚህ በሸዋ ምንጃር ከተማ በፍም እሳት ፋኖዎቻችን በውጊያ የተማረኩ የኦሮሚያ ክልል ልዮ ኃይል አባላት ናቸው። ትግላችን ፈጽሞ ለበቀል አይደለም ነገር ግን የኦሮሞን ህዝብ የማይወክሉ ፖለተከኞች "ሰበርናቸው" እንዳላሉን፣ ዛሬ የእነሱ መልዕክተኞች አይናችንን ለማየት ቸግሯቸው ለምን አንገት እንደደፉ አልገባንም።
(ለማንኛውም የምርኮን ህግ የተከተለ ጥበቃ ውስጥ ናቸው)
13.9K viewsናፍቆት !, 13:15
Buka / Bagaimana
2023-12-22 13:47:54 ባህር ዳር አሁን ቀበሌ 14 ኤፍራታ አካባቢ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እንዳለ የመረጃ ምንጮች ነግረውናል። ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን ይዘን እንመለሳለን!
13.5K viewsናፍቆት !, edited  10:47
Buka / Bagaimana
2023-12-22 13:02:15

14.0K viewsናፍቆት !, 10:02
Buka / Bagaimana
2023-12-22 09:35:37
አስደናቂ አስደማሚ ኦፕሬሽን በቡሬ ተፈፅሟል!..

ይህ ዜና ለመተኛት ለምትሰራዱ የመልካም ሌሊት፣ ቀናችን ለምትጀምሩ ደግሞ የብሩህ ቀና ዜና ይሁንልን።

ቡሬ ከተማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ መሽጎ የነበረው የጠላት ኃይል ዙ -23 እና ሞርታር በመያዝ በካምፑ የተወሰነ ኃይል አስቀርቶ ግዳጅ ተሰጥቶት ወደ ሽንዲ ከተማ ከተማ ይሄዳል፤ ሌላ 2 ሲኖትራክ ኃይል ደግሞ ድጋፍ ለመስጠት በካምፑ ውስጥ ለጉዞ ተዘጋጅቷል።

ይኸኔ ኦፕሬሽን ነድፎ ይጠብቅ የነበረው መቶ አለቃ ኢንጅነር ዘመኑ አማረ ስር ያለው የዳሞት ብርጌድ የአሳምነው የሻለቃ ታህሳስ 11/2016 ዓ.ም ማታ 2:00 ወደ ካምፑ ዘልቆ በመግባትና ጥቃት በመክፈት ዋርድያን ጨምሮ ካምፕ ውስጥ የነበረውን አራዊት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ በ25 ደቂቃ ውስጥ መደምሰሱ ታውቋል።

በዚህ ኦፕሬሽንም ጀግናው የዳሞት ብርጌድና ሻለቃ ብሬን፣ መትረጊስ፣ የነፍስ ወከፍ ክላሽ፣ ተተኳሽና የምግብ ሬሽኖችን (ብስኩት እና አስቃፅላ) የላከላቸውን ከአሰላው የአህያ ቄራ ያመለጠውን ብርሃኑ ጁላን አመስግነው ገቢ ማድረጋቸው ታውቋል።

በዚሁ ኦፕሬሽን ባህርዳር ዊክሊክስን እጅግ ያስደሰተው ነገር ደግሞ ከሰሞኑ እዛው በቡሬ ከተማ መስጅድ ውስጥ ገብተው አንድን ሼክ ከገደሉት ውስጥ የነበሩ የአገዛዙ ታጣቂዎችም አብረው መደምሰሳቸውን መስማታችን ነው።

ከድሉ በኋላም እነ መቶ አለቃ ኢንጅነር ዘመኑ አማረ ለሚሊሽያ፣ ለፖሊስና ለሰራዊቱ አባላት እስከ ታህሳስ 30 ድረስ የእጅ ስጡ ጥሪ ወረቀት ካምፓቸው ውስጥ በትነውላቸው በሰላም ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል። መቶ አለቃ ኢንጅነር ዘመኑ አማረና ጓዶቹ እየከፈላችሁት ስላለው የተግባር መስዕዋትነት ትልቅ ትልቅ አክብሮት አለን።
14.8K viewsG T, 06:35
Buka / Bagaimana
2023-12-19 11:41:21 አስገራሚው የእስር ዜና

የአማራ ክልል መንግሥት ነኝ ተብየው ያደረገውን ልዩ ኃይልን እንደገና አደራጃለሁ፣ ካሳ 80 ሽህ ብር እሰጣለሁ፣ የመኖሪያ ቦታ እሰጣለሁ ጥሪ ተቀብለው ለመንግስት እጅ የሰጡ ከ40 በላይ ከሃዲ ባንዳ ልዩ ኃይሎች ሰሜን ጎንደር ላይ ታስረው ዛሬ እየተገረፉ ሲሆን የግርፋቱም ምክንያት

፩/ መጀመሪያ የታጠቃችሁትን ትጥቅ ለፋኖ ለምን ሰጣችሁ

፪/ እስከ ዛሬ ፋኖን በመደገፍ መከላከያን ወግታችኃል

፫/ አሁንም መሳሪያና ገንዘብ ፍለጋ ነው እንጅ የመጣችሁት ጥረ‍ኢአችንን አምናችሁበት አይደለም በማለት እየተገረፉ ይገኛሉ።

ከታሳሪ ቤተሰቦች በተገኘ መረጃ የተወሰኑት በድብደባው እና በርሃብ ምክንያት በሞትና በህይወት መካከል እንደሚገኙ ተጠቁሟል። እንደሚረሽኗቸውም ተነግሯቸዋል ስለተባለ ቤተሰቦቻቸው ትልቅ ጭንቀት ውስጥ ናቸውም ተብሏል።

ስለሆነም በብልጽግና ስጦታ የተማለለ ሆዳም ባንዳ እንዲህ እየተልከሰከሰ ዋጋውን እያገኘ ነው። ህዝብንም ክዶ በብልፅግና ስጦታ እየተማለለ ለመግባት የሚንቀሳቀስን ኋይል ከእነኝህ ካልተማረ ዋጋውን ያገኛል ተብሏል።

ሌላው የማስጠንቀቂያ መልእክት  !

ወደ ፊት ስሙ እና ስልክ ቁጥሩ ለህዝብ የሚጋለጥ አንድ  በአሁኑ ሰዓት ላሊበላ ማረሚያ ቤት የገባ የክልሉ ልዩ ኃይል ነኝ ባይ ግን ኦሮሚያ ክልል የኖረ ሰርጎ ገብ ከፍተኛ ክፍያ ተከፍሎት ጀግኖች ፋኖወች ላይ ፕሮፖጋንዳ በመንዛትና በጥቅምም በመደለል ከእየ ቦታው ስልክ እየደወለ ለማስኮብለል ስራ እየሰራ  ይገኛል። ስለሆነመ‍እ ምን ምን እንዳደረገ በቅርብ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

ዘላለማዊ ክብር እና ሞገስ ለእውነት ሲሉ ለህዝባቸው ለተሰውና እየተሰው ላሉ ሰማእታት !!!
12.6K viewsG T, 08:41
Buka / Bagaimana
2023-11-22 16:33:40 ላልይበላን ጨምሮ በጥንታውያን ቅርሶቻችን አቅራቢያ ውጊያ ማድረግ በጥብቅ ሊወገዝ ይገባል!
**
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ!

አማራ ክልል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት እና ቅርሶች የተዋበ አካባቢ ነው። ከእነዚህ የኢትዮጵያውያን ጥበብ በጉልህ ከተገለጠባቸው ሥፍራዎች ውስጥ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባሕል ድርጅት የሆነው ዩኔስኮ በ፲፱፸፱ ዓ.ም በቅርስነት የመዘገበው የቅዱስ ላልይበላ አብያተ ክርስቲያናት ተጠቃሽ ናቸው። ቤተ ጊዮርጊስ (ባለ መስቀል ቅርፁ) እና ቤተ መድሃኔዓለምን ጨምሮ ፲፩ ውቅር አብያተ ክርስትያናትን ያካተቱት የላልይበላ ቤተ እምነት እየሩሳሌምን ታሳቢ አድርገው በ፲፪ኛው መ.ክ.ዘ በንጉሥ/ቅዱስ ላልይበላ አማካይነት የተገነቡ ናቸው፡፡

እነዚህ የአባቶቻችን ጥበብ ጎልቶ የሚታይባቸው አካባቢዎች ላለፉት ምዕተ ዓመታት የአለም አቀፉን ሕብረተሰብ ልብ የሳቡ፣ ለአገራችን የገቢ ምንጭ ሆነው ያገለገሉ፣ የነፍስና የሥጋ ድህነትን የቸሩ እንዲሁም ጎሳና ሃይማኖት ሳይለያቸው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሚኮሩበት ቅርሳቸው ነው።

ይሁን እንጂ የፌደራል መንግሥቱ ከሕወሓት ጋር ገብቶበት በነበረው ጦርነት በቅርሱ ላይ ተደቅኖበት ከነበረው አደጋና ስጋት ገና ሳያገግም፤ በአሁኑ ወቅት ደግሞ መንግሥት ከፋኖ ኃይሎች ጋር በገባው ጦርነት በቅርሶቹ አካባቢ የከባድ መሳሪያ ተኩስ ማከናወኑ መላውን የዓለም ማህበረሰብ እጅግ ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሏል። በተፈጸመው አስነዋሪ ድርጊትም ጥንታዊ ቅርሱ አስጊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ መሆኑን ከአይን እማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ለማረጋገጥ ችለናል። የሃይማኖታዊ መዳረሻ፣ የሰላምና ፍቅር መገኛ እንዲሁም ቅዱስ ስፍራ የሆነው ላልይበላን ጨምሮ ኹሉም ታሪካዊ ቅርሶቻችን የጦርነት ሥፍራ እንዲሆኑና ለአደጋ እንዲጋለጡ በየትኛውም መልኩ ሊፈቀድ አይገባም። ስለዚህ:-

፩. ዩኔስኮ "እጅግ የላቁ የዓለም እሴትና ቅርሶች ናቸው" ያላቸው ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት ጥንቃቄና እንክብካቤ የሚሹ በመሆናቸው፤ መንግሥት በዓለም አቀፍ ሕግጋት መሠረት ቅርሶቹን ለጉዳት ከሚያጋልጡ ማንኛውም ድርጊቶች እጁን እንዲሰበሰብና ምንም ዓይነት ከባድ መሣሪያ በቅርሶቹ አካባቢ እንዳይጠመድ እንዲሁም እንዳይተኮስ እንጠይቃለን።

፪. የመንግሥት የጸጥታ አካላትም ሆኑ የፋኖ ኃይሎች በክልሉ በሚገኙ ጥንታዊ ቅርሶች አቅራቢያ ውጊያ እንዳያካሂዱና የቅርሶቹን ህልውና አደጋ ላይ ከሚጥሉ ማናቸውም እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ አጥብቀን እናሳስባለን።

፫. የአካባቢው ማኅበረሰብ እነዚህን በምህንድስና ሥራ ዓለምን ያስደመሙ አብያተ እምነት ለብዙ መቶ ዓመታት ጠብቆ እንዳቆየ ሁሉ ዛሬም ይህን ኃላፊነቱን በላቀ ሁኔታ እንዲወጣና የኢትዮጵያ ሕዝብና የዓለም ማኅበረሰብ የጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ አጥብቀን እናሳስባለን።

በመጨረሻም ከዚህ ቀደም ደጋግመን እንደገለጽነው አገር ከምትገኝበት ችግር ብቸኛ መውጫ መንገድ ኹሉን አቀፍ፣ ግልጽና በአግባቡ የሚመራ የፖለቲካ ድርድር መሆኑን ዛሬም አጽንኦት ሰጥተን እየገለጽን፤ መንግሥት ለሰላማዊ መፍትሄ በሮቹን እንዲከፍት እናሳስባለን።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያ እና ሕዝቧን ይጠብቅ!
እናት ፓርቲ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ህዳር ፲፪ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም
13.5K viewsG T, 13:33
Buka / Bagaimana
2023-11-18 14:08:48 ወገልሳ ሮቢት ጭንባ አቸፈር | በአማራ ላይ ግልፅ ጦርነት ያወጀው ባለስልጣን | ስሃላ፣ ዝቋላና አብርገሌ ዋግኸምራ

12.7K viewsናፍቆት !, 11:08
Buka / Bagaimana
2023-11-17 20:40:38
እብዱና ወራሪው አብይ አህመድ በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ አለም እየመዘገበ ነው።
13.5K viewsኢት ኤል, 17:40
Buka / Bagaimana
2023-11-17 20:28:59
የፋኖን ግስጋሴ የተረዳዉ የብልፅግና መንግስት ለድርድር በሬን ከፍቻለሁ እያለ ነዉ።

በአማራ ክልል ጦርነት ያወጀዉ ብልፅግና በሁሉም ግንባሮች አይበገሬዉ ፋኖ  የኦገግን ሰራዊት በጥይት እየቆላ አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣዉ እንደከረመ እሙን ነዉ።

ይሔንን የተመለከተዉ  ብልፅግና የፋኖ ግስጋሴ እና አመጣጥ እጅ እንደሚያሰጠዉ ስለተገነዘ አሁንም አቋራጭ መንገድ መፈለጉን ተያይዞታል ።

በሰላም ሰላም ስጡን  ብሎ ለጠየቀ ህዝብ ጦር አዉጆ ሰላማዊ ዜጎችን ሲጨፈጭፍ የነበረ አገዛዝ ዛሬ ለድርድር ለምን በሩን ከፈተ? እዉነታዉ እና ከህዝብ ጋር ያለዉ ሀቅ ፋኖ በመብረቃዊ ግስጋሴ በሁሉም ግንባሮች ድል እና ግስጋሴ ስላስመዘገበ ነዉ ። የፋኖን ግስጋሴ እና የጦር ስልት መቋቋም ያልቻለዉ ብልፅግና በአፈ ቃለጤዎቹ በኩል ዛሬ ለድርድር ማንኛዉም አካል ጥያቄ ካለዉ በሰላማዊ መንገድ ድርድር ማድረግ እንደሚቻል በአቶ ተስፋየ በኩል ፍላጎቱን አንፀባርቋል ። አያይዞም ሀይልን በመጠቀም ፋኖን አንበረክካለሁ ብሎ ክንፉን ተሰብሮ የተመለሰዉ ብልፅግና  ህብረተሰቡ በሀይል የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን እንዲያወግዝለት ለመና የሚመስል ተማፅኖ አሰምቷል።

አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-
#Youtube:- Ashara Tv - https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng#facbook:- https:www.facebook.com/asharamed4
#ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedi#instagram:- https://instagram.com/asharamediaofficial?utm_source=qr&igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg==
#ዋትስአፕ :-https://whatsapp.com/channel/0029Va5CGsH2ER6bIAUd2L1T#
12.8K viewsG T, edited  17:28
Buka / Bagaimana
2023-11-17 13:38:52 የላሊበላ ቅርስ አስደንጋጭ ውድመት | የአፍሪካ ልማት ባንክ ከኢትዮጵያ ወጣ? የህገመንግስቱ መቀየር ያልተጠበቀ

13.0K viewsናፍቆት !, 10:38
Buka / Bagaimana