Get Mystery Box with random crypto!

Ashara Media - አሻራ ሚዲያ

Logo saluran telegram asharamedia24 — Ashara Media - አሻራ ሚዲያ A
Logo saluran telegram asharamedia24 — Ashara Media - አሻራ ሚዲያ
Alamat saluran: @asharamedia24
Kategori: Politik
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 5
Deskripsi dari saluran

ስልክ፥ 251984190114 / 251993111700

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru 5

2024-01-11 15:14:23


ኮለኔሉ ብቻውን ቀረ/ሁለቱ አደገኛ ሴራዎች ተጋለጡ/1.7 ሚሊዮን አማራ ምን ገጠመው?(አሻራ ዜና02/05/2016 ዓ/ም )
12.8K viewsናፍቆት !, 12:14
Buka / Bagaimana
2024-01-11 13:36:24 የብልጽግና ሚስጥራዊ ስብሰባ መረጃ!

የዐብይ አህመድ አገዛዝ ከሰሞኑ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጉ ይታወቃል።

ስለ ትግራይ እና አማራ የቀረቡ ሃሳቦች በብልጽግና ስብሰባ ላይ የቀረበው ሀሳብ በፋኖ የደህንነት መዋቅር ተመንትፎ ለኢትዮ 251 ሚዲያ የደረሰው!

1ኛ. በምክክር ኮሚሽን በኩል በቶሎ በፌደራል መንግስቱ ጣልቃ ገብነት እርቅ ይደርግ በክልል መንግስታት መካከል መግባባት በመፍጠር እና የተቋረጡ የንግድ እና መሰል ተግባራትን በክልል መንግስታት ደረጃ መስራት። ይሄን ማድረጋችን የትግራይ ሃይሎች ከፋኖ ጋር ጥምረት እንዳይፍጥር ያደርጋል። አወዛጋቢ ቦታዎች በፌደራል ቁጥጥር ስር የተዳደራሉ።

  2ኛ. የትግራይ ሃይሎችን ከፌደራል መንግስቱ መካከል ያለውን አለመግባባት በማርገብ ከህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የፌደራል ስልጣን በመስጠት ውጥረቱን በማላላት ጊዜ መግዛት አለብን። በተጨማሪም የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ሪፎርም ላይ ስለሆነ የሚመጡት አመራሮች በአማራ ሃይሎች በኩል በቀላሉ ተቀባይነት ሊያገኙ ይችላሉና ለእኛ ጥሩ ነው።

  3ኛ. በጀነራል ብርሃኑ በቀለ አማካኝነት ማይጠብሪ ላይ እንዲበተን የተደረጉ የሚሊሻ አባላት ወደ ማይጠብሪ መልሶ ማስገባት እና የብሄር ዘውግ ያለው ግጭት ማስነሳት አለብን። በተመሳሳይ በሰሜን ጎንደር ያሉ የትግራይ ዘር ሃረግ ያላቸው ላይ ተመሳሳት ግጭት ማስነሳት አለብን።

  4ኛ. በሱማሊያ እና ኤርትራ መሪነት ጦርነት ሊኖር እንደሚችል መጠቆም ያስፈልጋል። ትግራይንም በዚህ ምክንያት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መክተት አለብን።

አማራ ክልልን በተመለከተ!

1ኛ. ለሚሊሻ እና አድማ ብተና የውጊያ አበል መጨመር

2ኛ. የፋኖ ሃይሎች ወደ ድርድር እንዲመጡ ማድረግ። ለዚህም ከፍተኛ የማዳከም ስራ በመስራት ተስፋቸው ድርድር እንዲሆን ማድረግ።

3ኛ. የሚሊሻ እና አድማብተና እና ከወረዳ በታች ያሉ አባላት እንዳይከዱ ከህዝብ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲነጠሉ ማድረግ እና ህዝቡ እንዳይሸሽጋቸው ማድረግ።

4ኛ. ስለድሮን አሁን ካላቸው እውቀት የተለየ እና የተሳሳተ እነሱን አደጋ ላይ የሚያጋልጥ መረጃ ማስተጋባት

5ኛ. የካቲት 1 ሁሉም የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪ እንዲቀበሉ ማድረግ (ከዚህ በፊት ጥር 1 ላይ እንጀምራለን ብለው የነበረ ያልተሳካላቸው)

6ኛ. የጥር 3 ኦፕሬሽን የተሳካ እንዲሆን ለሚሊሻ እና አድማብተና ደሞዝ ቅድሚያ መስጠት።

ይቀጥላል...

ሙሉጌታ አንበርብር
13.1K viewsG T, 10:36
Buka / Bagaimana
2024-01-10 12:54:46
ሰበር መረጃ - ከባህር ዳር

በጎጃም ዕዝ የባህር ዳር ፋኖ ስር ሁለት ሻምበሎች ታሪካዊ ስያሜን ይዘው መመስረታቸው ታውቋል።

1. አንሻ ሰይድ ሻምበል - በጀግናዋ እህታችን ፋኖ ህይወት ጌራ የሚመራው ይሆናል። ይህ ሻምበል ስያሜውን በወለጋ ክልል ቤተሰቦቿን የኦነግ ታጣቂዎች በማጨፍጨፍ ላይ እያሉ እራሷን ለማትረፍ "ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም፤ አትግደሉኝ" በማለት በተማፀነችው ህጻን አንሻ ሰይድ የተሰየመ መሆኑ ታውቋል።

"አንሻ ሰይድ የትግላችን ቃል ኪዳን ሆና፣ ታናናሾቿ በማንነታቸው ኮርተውና ተከብረው የሚኖሩባትን ለሁሉም እኩል የሆነችን ሃገር ለመፍጠር እንታገላለን" ሲሉ የሻምበሏ አባላት ተናግረዋል።

2. ታዲዮስ ታንቱ ሻምበል - ይህም ሻምበል በጎጃም ዕዝ የባህር ዳር ፋኖ ስር የተመሰረተ ሲሆን በቅርቡ ወደ ሻለቃ እንደሚያድግም ተነግሯል። ይህ ሻምበሉ ስያሜውን የወሰደውም ለእውነት ታምነው በእርጅና እድሜያቸው መስዕዋትነት እየከፈሉ ካሉት የወላይታው አንጋፋ ጋዜጠኛና የታሪክ ምሁር ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ስም እንደሆነ ታውቋል። ፋኖዎቻችን በአጋጣሚውም "ለጋሽ ታዲዮስ ታንቱ እጅግ እጅግ ታላቅ አክብሮት አለን" ሲሉ ለሚዲያዎች የላኩት መልዕክት ያስረዳል።

በዚሁ አጋጣሚ በሌሎች አካባቢዎች ያላችሁም ፋኖዎቻችን እነዚህንና መሰል ትልቅ ትርጉም ያላቸውን ስያሜዎች እንድትጠቀሙ ጥሪ እናቀርባለን። ዝቅ ያደረጓቸውን፣ በታሪክ ውስጥ ተገቢና ጉልህ ስፍራ ሰጥተን ከፍ አድርገን እናሳያቸው!
12.9K viewsG T, 09:54
Buka / Bagaimana
2024-01-09 22:29:10 ከጎጃም ዕዝ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ

ፋኖነት ቅንጦት ሳይሆን  የአማራ ህዝብ ፍትህ በተጓደለበት፣ ነፃነቱ በተገፈፈበት፣ ጠላት አገሩንና ሀይማኖቱን ሊያረክስ በመጣበት እና የመኖርና ያለመኖር የህልውና ትግል በገጠመው ጊዜ ለክብሩ ለማንነቱ ለሀይማኖቱ ሲል በአንድነት የሚነሳበት እሴቱ ነው።

በመሆኑም አማራ በአንድነት በተነሳበት በዚህ ጊዜ በተለይም በጎጃም ፈር ቀዳጅ ሆኖ በየወረዳው የተበታተነውን ትግል አንድ አድርጎ አራት ኪሎ ትንሳዔውን ለማክበር በጎጃም ቀጠና ዕዝ ከተመሰረተ ቅርብ ጊዜ ቢሆንም ጥሩ ውጤትን እያስመዘገበ ይገኛል።

ስለሆነም የጎጃም ዕዝ ባደረገው 4ተኛው አስቸኳይ የስራ አስፈፃሚዎች ስብሰባ በተለያዩ የትግሉ ቀዳሚ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት ከተወያዬ በኋላ የሚከተለውን ባለ ሁለት ነጥብ የአቋም መግለጫ በመስጠት ሌሎችን አጀንዳዎች በይበልጥ የማሰቢያ ጊዜ አስቀምጧል።

1ኛ.የዲያስፖራ ክንፉ በአማራ ህዝብ ትግል ውስጥ ከሀሳብ እስከ ፋይናንስ በማገዝ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ይታወቃል። በመሆኑም በጎጃም ዕዝ ፋኖ በውጭ የሚገኙ የአማራ ተወላጆችን እና ሌሎች የፋኖን እንቅስቃሴ ደጋፊዎች ለማስተባበር እና የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ በማሰብ በዕዙ ስራ አስፈፃሚ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ የውጭ ማህበረሰባችንን እንዲያስተባብሩና አስቸኳይ የሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ (Emergency Fundraising Committee) ያዋቀረ ሲሆን በኮሚቴው በኩል ለሁለት ሳምንታት ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል።  

ኮሚቴውም ዘጠኝ አባላት ያሉት ሲሆን ጋዜጠኛ ተስፋዬ ወልደስላሴን ሰብሳቢ አድርጎ መርጧል።

ስለሆነም በውጭ የምትኖሩ የአማራ  ባለሀብቶች፣  የማህበረሰብ አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ዩቲዩበሮች፣ ቲክታከሮችና በሁሉም የሚዲያ ፕላትፎርሞች ውስጥ ያላችሁና የፋኖን የህልውና ትግል የምትደግፉ ወገኖቻችን ትብብራችሁን የምንጠይቅ መሆኑን እየገለጽን እናንተ በምትሳተፉባቸው ሚዲያዎች ያሉትን አድማጭ-ተመልካቾቻችሁን፣ አድናቂዎቻችሁንና ደጋፊዎቻችሁን ግንዛቤ በመፍጠር ጥር አስር ለሚጀመረው ዘመቻ የበኩላችሁን አሻራ እንድታሳርፉ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

2ተኛ.ሐሰተኛ በቃሉ፣ ስደተኛ በቅሉ ይታወቃሉ እንዲል ብሂሉ የፋሽስታዊ አገዛዙ ክልል ብሎ ባስቀመጠው በረት/ክልል/ ውስጥ ሰላም ያለ ለማስመሰልና ተማሪዋችን የፕሮፖጋንዳው/የፖለቲካው ሚዛን ማስጠበቂያ ቀብድ በማድረግ የስርዓቱ ስልጣን አስጠባቂ የሆነውን የትምህርት ስርዓት በመጠቀም በአማራ ክልል* ውስጥ የሚገኙ ዩንቨርስቲዎች በከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር በኩል በተደረጉ ጫናዎችና በምንጣፍ ጎታች የዩኒቨርሲቲ ፕሪዝዳንቶች  አማካኝነት የተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ለተማሪዎቻቸው ጥሪ ማድረጋቸው ይታወቃል።

ነገር ግን በክልሉ ውስጥ የአማራ ህዝብ ለህልውናው (ለነጻነት፣ ለእኩልነትና ፍትሃዊነት) እልህ አስጨራሽ ትግል ከጨፍጫፊውና ፋሽስታዊው አገዛዝ ጋር እያደረገ ይገኛል። በዚህ ትግልም አመርቂ ውጤቶችን በማስመዝገብ የጨፍጫፊውን አገዛዝ እያፈራረሰው ይገኛል።

ስለሆነም ውድ ተማሪዎች ትምህርት ለአማራ ልጅ በዚህ ሰዓት ቅንጦት ሆኖበት ከክርስቲያን እስከ ሙስሊሙ፣ ከህጻናት እስከ ሽማግሌውና  ከአርሶ አደር እስከ መንግስት ሰራተኛው/ምሁራን/የአያቶቹን ታሪክ በመድገም በዱር በገደሉና በፀሃይ በብርዱ ለህልውናው በከፍተኛ ደረጃ እየተዋደቀ በሚገኝበት በዚህ ሰዓት  የተማሪዎችን እንቅስቃሴ መሰረት በማድረግ መፈርጠጥ ልምዱ የሆነው ጨፍጫፊው ቡድን በፋኖ ላይ ጥቃት ለመሰንዘርና በሚወሰደው የአጻፋ እርምጃ በሚደርስ ጉዳት ፋኖ በንፁሀን ተማሪዋች ላይ ጥቃት ፈጸመ በማለት ፕሮፖጋንዳ ለመንዛት እየሰራ እንደሆነ መታወቁ የአደባባይ ሚስጥር ሁኗል።

ስለሆነም የፋሽስታዊ አገዛዙን ጥሪ ተቀብለው በሚመጡ ተማሪዋች ላይ  ለሚደርሰው ጉዳት ሃላፊነቱን መንግስት ነኝ የሚለው ጨፍጫፊው ቡድንና እራሳችሁ ተማሪዎች የምትወስዱ መሆኑን እንድታውቁ በአፅዕኖት እናሳስባለን።

ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ!
ድል ለፋኖ!

ጎጃም ዕዝ ፋኖ!
ታህሳስ 30/2016 ዓ.ም
12.9K viewsG T, 19:29
Buka / Bagaimana
2024-01-09 16:45:04 በፍኖተሰላምና አካባቢው ዛሬ የተሰራው ጀብዱ!

︎ከፍኖተሰላም በቅርብ ርቀት ላይ ወዳሉት
መንዝና ገራይ አካባቢዎች አራዊት ሰራዊቱ በ3 አቅጣጫዎች ለመክበብና ጥቃት ለመሰንዘር እንዳሰበ የፋኖ የደህንነት መዋቅር መረጃ ደርሶበታል። ፋኖዎቻችን የእራሳቸውን እቅድ ነድፈው ይጠብቁ ጀመር።

︎አራዊት ሰራዊቱም በጠዋቱ ወደ ሁለቱ ቀበሌዎች ተንቀሳቀሰ፤ ሚሊሽያም ሆነ አድማ ብተና አብረውት የሉም። በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ግን  ፋኖዎቻችን በእራሷ በፍኖተሰላም ከተማ ውስጥ በቀረው ኃይል ላይ ከ3 አቅጣጫዎች ጥቃት ከፈቱ።

ወዲያውም፦

1) በባዕታ ቤተክርስቲያን አካባቢ ከ10 በላይ አራዊት ሰራዊት አስክሬን ሲሆን ከ15 ላይ ደግሞ ቁስለኛ ሆኗል። ሌሎች ደግሞ ቀጠሉ…

2) በገወቻ ስላሴ መውጫ ከ40 በላይ ሚሊሻ እና አድማ ብተና ተደመሰሰ። ቀጠሉ…

3) በመምህራን ኮሌጅ አካባቢ ደግሞ በርካታ አራዊት ሰራዊት፣ ሚሊሽያና አድማ ብተና ሲደመሰስ፣ ቀላል የማይባል ቁስለኛም እንደተመዘገበ ታውቋል።

︎ፋኖዎቻችን ይህን ጥቃት ፈፅመውም ከድልድዮ (ከፍርን ከላህ ወንዝ) ማዶ ያለውን የከተማውን ግማሽ ክፍል በቅፅበት ውስጥ ተቆጣጥረዋል።

︎ይህ እየሆነ እያለ ወደ መንዝ እና ገራይ የተንቀሳቀሰው ሰራዊት ወደ ቀበሌዎቹ እየደረሰ ነበር። ቢሆንም ግን ገና ሳይረጋጋ ቦታ ይዘው የነበሩት ፋኖዎቻችን ተኩስ ሲከፍቱበት ያን ያክል የአፀፋ ምላሽ ሳይሰጥ በፋኖ ወዳልተያዘው የከተማዋ ክፍል ሲሮጥ መግባቱ ታውቋል።

︎በነገራችን ላይ አራዊት ሰራዊቱ ሚሊሽያና አድማ ብተና አብረው ከሌሉ የመዋጋት ድፍረትም ሞራልም እንደሌለው ይነገራል፤ አብረው ሲኖሩ ግን ከፊት እያሰለ የእሳት እራት እያደረጋቸውና ሲሸሹ ደግሞ እራሱም እየጠበሳቸው እንዳለ የሚታወቅ ነው።
13.0K viewsG T, 13:45
Buka / Bagaimana
2024-01-09 14:22:12 በመካነሰላም እንጅባራና ጎንደር/የመከላከያ እርስበርስ ውጊያ/የአገኜሁ ተሻገር ከሀገር የመኮብለል እቅድ(አሻራ ዜና30/5/2016 ዓ/ም )

13.1K viewsናፍቆት !, 11:22
Buka / Bagaimana
2024-01-09 12:55:00
በእንጅባራ ወታደራዊ ካምፕ ምን ተፈጠረ? ..

ታህሳስ 29 ከምሽቱ 3:00 እስከ ሌሊት 6:00 አካባቢ በእንጅባራ ከተማ ካምፕ ውስጥ የነበረ አራዊት ሰራዊት እርስበርሱ ሲለባለብ እንዳደረ ታውቋል። በዚህ ለሰዓታት በቀጠለው የተኩስ ልውውጥ በርካቶች እንዳለቁ ተገምቷል። በርካታ የሰራዊቱ አባላትም መክዳታቸው የታወቀ ሲሆን እንደምርጫቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ የሚመቻችላቸው መሆኑን ከወገን ኃይል በኩል ተሰምቷል።

በሌላ በኩል ደግሞ በአዲስ አበባ 6 ኪሎ አካባቢ ለጊዜው ምክንያቱን ያላወቅነው የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ተነግሯል። ያው ነገሮች ወደ መቋጫቸው ሲቃረቡ ይህን መሰል ነገር የሚጠበቅ መሆኑም ተነግሯል።
13.2K viewsናፍቆት !, 09:55
Buka / Bagaimana
2024-01-08 22:45:35 ፋኖ የቀየረው የዜማምት እና ውጤቱ/የግንባታ ፕሮጀክቶች እናሚስጥራዊ ተልዕኳቸው/የግንባታ ተቋራጭ ባለሀብቶች እና የመንግስት እጅ (አሻራ ትንታኔ 29/4/2016ዓ/ም

14.1K viewsናፍቆት !, 19:45
Buka / Bagaimana
2024-01-07 18:19:55
#Amhara

"በሰላም እጅ ሰጥተዋል" የተባሉት ጎንደር ካምፕ አስቀምጠዋቸው የነበሩትን ፋኖ ባደረገው ኦፕሬሽን አስለቅቋቸዋል።  ሙሉ በሙሉ ሚሊሻና የቀን ሠራተኛ የነበሩና ገንዘብና ቤት እንሰጣችኋለን ብለው  ለፕሮፖጋንዳ ያመቻቿቸው የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት አብዛኛው ፋኖን ተቀላቅሎ ውጊያ እያደረገ ነው!!

ቅጥፈት ውሸት የአገዛዙ መለያ ሲሆን  እንደለመደው ብዙ ጊዜ አታልልበታለሁ  ያለውን ያረጀ ያፈጀ ስልት ከሣምንት በላይ አልተጠቀመበትም።
13.3K viewsG T, 15:19
Buka / Bagaimana
2024-01-07 16:28:01
ተጨማሪ ሰበር ዜና! ጐንደር ..

የጎንደር ህዝብ በአውደ-ዓመቱ ምድር ከባድ ትንቅንቅ እያካሄደ ነው!

በጎንደር ከተማ አይባ ኪዳነምህረት፣ ፆር ማርያም፣ ሸዋ ዳቦ፣ ማረሚያ ቤቱ እና እንዲሁም በገንፎ ቁጭ እና በህዳሴ አከባቢ በአሁን ሰዓት እልህ አስጨራሽ ግብግብ እየተካሄደ መሆኑ ተረጋግጧል።

በተለይ አይባ ኪዳነምህረት አከባቢ ትናንት ምሽት የተጀመረው ውጊያ ዛሬ በአውደ ዓመቱ ምድር የቀጠለ ሲሆን፡ በዚህ ስፍራ የጠላት ጦር አስከሬን ተደራርቦ መከመሩን ሪፖርተሮቻችን ተመልክተዋል።

ከጎንደር ከተማ በተጨማሪ ትንቅንቁ በሌሎች የማዕከላዊ ጎንደር አከባቢዎችም ቀጥሏል።

በደምቢያ ምድር በሻለቃ ደርጀ በላይ የሚመራው ፋኖ የጠላት አብይ አህመድን ወታደር ውሃ ውሃ እያስባለው ይገኛል።

በታች አርማጭሆ በፋኖ ሲሳይ አሸብር የሚመራው ግዙፍ አስፈሪ ጦር የጠላት አብይን ወታደር ዙሪያውን ከቦ በአፈሙዘኛ ቋንቋ እያናገረው መሆኑንም  ለማረጋገጥ ተችሏል።

በኮማንደር ሳሙኤል የሚመራው ኃይል በሻውራ ደልጊ ደለጎ፣ በአለፋ ጣቁሳ ተሰማርቶ የነበረውን የጠላት ጦር ቀለበት ውስጥ አስገብቶ ልክ እንደ ገና ዳቦ በላይ እሳት በታች እሳት እያዘነበበት መሆኑን የአማራ ድምፅ ሚድያ ከንጋት ጮራ ብርጌድ አዛዦች ጋር ባደረገው የስልክ ቆይታ ለማወቅ ችሏሎ።
#አማራ ድምፅ
12.8K viewsናፍቆት !, 13:28
Buka / Bagaimana