2023-11-16 10:50:44
<< 66 በመቶ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስትር የስልጣን ዘመን ገደብ እንዲኖረው ይፈልጋሉ >> - የአፍሮ ባሮ ሜትር ጥናት
<< በኢትዮጵያ የስልጣን ሁኔታ በተለይ የጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን እንዲገደብ የሚፈልገው ኢትዮጵያዊ ቁርጥ ከ66 በመቶ በላይ ማለፉን >>አፍሮ ባሮ ሜትር አስታወቀ።
ተቋሙ ይሄን ያለው ባለፉት ሶስት ተከታታይ አመታት ያስጠናውን ጥናት ተከትሎ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ሲሆን በ2015 ዓ.ም ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ዘመን እንዲገደብ የሚፈልገው ቁጥር እያሻቀበ መጥቷል ብሏል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት እንዲቀየር የሚፈለገው ቁጥርም ከፍ እያለ መምጣቱን ተቋሙ ይፋ አድርጓል።
< የፌዴራል መንግስቱ የስራ ቋንቋ እንዲጨመር እና ሌሎች ቋንቋዎች እንዲካተቱበት የሚፈልጉት ቁጥርም ክፍተኛ ነው > ብሏል።
ባለፉት ሶሶት አመታት ያካሄደውን ዳሰሳ ጥናት አስመልክቶ መግለጫ የሰጠው አፍሮባሮሜር አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባን ደረጃ ወደ ክልል ከፍ እንዲል ወይም የፌዴሬሽኑ አባል ክልል እንዲሆን እንደሚሹም አክሎ ጠቁሟል።
በተጨማሪም ህገ መንግስቱን ሙሉ ለሙሉ ከመተካት ወይም አሁን ባለበት እንዲቀጥል ከማድረግ ይልቅ ወቅታዊ የኢትዮጵያን ፍላጎት ለማንፀባረቅ እንዲያስችል መሻሻል አለበት የሚሉት ኢትዮጵያውያን በርካቶች መሆናቸውን አመላክቷል።
አፍሮ ባሮ ሜትር ያወጣው የዳሰሳ ጥናት የፖለቲካ ልሂቃኑን በሚያወዛግቡ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎች ላይ የህዝቡ አስተያየት ምን እንደሚመስል ያካተተ ሲሆን በአንድ በኩል ህዝባዊ ድጋፍ ያለው በሌላ በኩል ደግሞ ጉልህ ተቃውሞ እንዳለው ለማረጋገጥ ችያለሁ ባይ ነው።
ልዩነቶች ከተስተዋሉባቸው ጉዳዮች መካከልም የኢትዮጵያ ህዝቦች ብሄሮችና ብሄረሰቦች የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት የሚሰጠውን አንቀፅ 39ኝን ከህገ መንግስቱ ይወገድ ወይስ ይቀመጥ የሚለው ይገኝበታል።
በተጨማሪም በብሔራዊ ሰንደቅ አላማው ላይ ያለው አርማ ይነሳ ወይም ይቀጥል የሚለው እንደሚገኝበት ነው የተመላከተው።
በተመሳሳይ አዲስ አበባን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል እንድትሆን የሚፈልጉት ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ35 በመቶ ወደ 53 በመቶ ከፍ ማለቱን ተቋሙ ያወጣው የዳሰሳ ጥናት አረጋግጦ ይፋ አድርጎታል።
በሌላ በኩል ፌዴራላዊ የአስተዳደራዊ ስርዓቱን በሚመለከት አስጠንቼ ደርሸበታለሁ ያለውን ውጤት ይፋ ያደረገው አፍሮባሮሜትር ፌዴራላዊ ስርዓቱን በሚመለከትም ኢትዮጵያዊ ከሁለት መከፈሉን ይፋ አድርጓል።
ግማሽ ያህሉ ኢትዮጵያዊ ማለትም 49 በመቶ የሚሆነው ፌዴራላዊ አወቃቀሩ መሆን የሚገባው ብብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦችን ማንነት መሰረት ባደረገ አግባብ ነው ሲል ሌላኛው 48 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ክልልሎች በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጣቸውና ገፅታቸው እንጂ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች በሚኖሩበት መልኩ መሆን የለበትም ባይ መሆናቸውን አመልክቷል።
በተመሳሳይ ከተሜው ኢትዮጵያዊ መልክዓ ምድራዊ ገፅታዎችን ማዕከል ያደረገ የፌዴራል ስርዓት የመምረጥ ዝንባሌ ያሳዩት ቁጥር 54 በመቶ የሚሆኑት ሲሆኑ በገጠር የሚገኙ ነዋሪዎች ማለትም 51 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ በበኩላቸው ማንነትን መሠረት ያደረገ የፌዴራል ስርዓትን መርጠዋል ብሏል።
አሻም
አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-
#Youtube:- Ashara Tv - https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng#facbook:- https:www.facebook.com/asharamed4
#ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedi#instagram:- https://instagram.com/asharamediaofficial?utm_source=qr&igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg==
#ዋትስአፕ :-https://whatsapp.com/channel/0029Va5CGsH2ER6bIAUd2L1T#
13.6K viewsG T, edited 07:50