Get Mystery Box with random crypto!

ከፍልስፍና ዓለም

Logo saluran telegram philosphyloves — ከፍልስፍና ዓለም
Logo saluran telegram philosphyloves — ከፍልስፍና ዓለም
Alamat saluran: @philosphyloves
Kategori: Tidak terkategori
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 1.85K
Deskripsi dari saluran

" አዋቂ ሰው ማለት ፍላጎቱን የመግታት እውቀቱ ከፍተኛ የሆነ ማለት ነው ። በሕይወት ዝቅተኛው ደረጃ ራስን በፍላጎት አጥር ውስጥ ማስቀመጥ ነው ። አብዛኛው የሰው ልጅ በብዙ ፍላጎትና በጥቂት እውቀት የተሞላ ነው ፤ አዋቂነት ግን ብዙ እውቀትና ጥቂት ፍላጎት ብቻ ይበቃታል ። " / አርተር ሾፐንሀወር /

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


Pesan-pesan terbaru

2023-06-07 04:38:49 የኢትዮጵያ ፖሌቲካ ውስብስብ ነው የሚመስልህ? have you tried የአማራን የውስጥ ለውስጥ ፖሌቲካ? quantum physics ማረኝ
13 viewsMUSSIE. S, 01:38
Buka / Bagaimana
2023-06-05 11:23:54 አልጋ የማንጠፍ ፍልስፍና

......ሆ ሀገሩ ሁሉ ምነካውን ነክነትን አእምሯቸው ላይ የዘራው የእብደት ገበሬ ማነው .....እቺን ነገር ስሟት እንዲህም ሆነ......እናት የተባለች ሴት፣ ልጅ ለተባለ ፍጥረት የአልጋ አነጣጠፍ ቴክኒክ ማስማር ዘወትር ልማዷ ከሆነ ሰነበ ልጁ እንደሆነ አይሰማ

"አንደው እንዴት ብነግር ይገባህ ይሆን አንተዬ" እሷው ነች አዎ እናት ተብዬዋ ወለጂ ብለው ያስገደዷት ይመስል ንጭንጯ

መኝታህን ሳታነጥፍ አትውጣ ብዬ እምነግርህ ስንት ጊዜ ነው

"ማታ እተኛበት የለም እንዴ ባነጥፈውም መልሶ መበላሸቱ መች ይቀራል" ልጅ የተባለ ፍጥረት ይመልሳል ሞጥሟጣ ነገር... ሲመሽ እንደሚፈርስ የሚያውቀውን ነገር አሁን ላይ የመገንባቱ ትርጉም ሊገባው አልቻለም

ህይወታችን አልጋ በማንጠፍ እና እሱኑ መልሶ በማበላሸት የቀነበበ ሲሲፈሳዊ ጉዞ ነው አለ አሉ አድጎ.......



መኖርና እና መሞት ከሚለው የስጦታው ሀይሉ መፅሃፍ የተወሰደ(ገፅ 143)
259 viewsNatty שלום, edited  08:23
Buka / Bagaimana
2023-06-05 10:44:36 ..........."ሐገራችሁ ደግ ነበረች፣
ቸርም ነበረች።
ለናንተ ግን አይደለችም።
በስንፍናችሁ ያስጨከናችኃትም እናንተ ናችሁ።
ኢትዮጵያ፣ በስብሳና አጎንቁላ የምታፈራ ፍሬ ሳትሆን በጎተራ የምትሞሸር የደደረች ዘር ሆናለች።
"ኢትዮጵያውያን፣
ሬሣ እንዳይፈርስ አዘውትረው የሚታትሩትን የጥንት ግብፃውያንን ይመስላሉ። እናንተ ከእመቤት ኢትዮጵያ አስክሬን ጋር ከነህይወታችሁ የተቀበራችሁ ባሮች፣የሞተን እንቅልፍ ለማስወገድ ያዘጋጃችሁትን ዝማሬ አታውርዱ፣
እናንተ የሙት ሞግዚቶች
ኢትዮጵያ የሚለው መውድሳችሁ ያብቃ!
ኢትዮጵያ በረጅም እረፍት ውስኝ ያለ ጣዕር ሞታለች። መወድሳችሁን አቁሙ እና ለፍታት መቋሚያችሁን አንሱ፣
መቃብር ቆፉሪውን ቁስቅሱና እያፏጨ ይቅበራት። የታማሚ ሞት የአስታማሚ ነፃነት እንደሆነ አታውቁምን?
እናንተ አስክሬን አስታማሚዎች ፣ እናንተን በመጠበቅ የቀብር መልስ ንፍሯቹ ነፍስ ዘራ፣
ጉዝጓዛችሁ መሬት ዋጠው..."
"ኡ ኡ ኡ!"
"ሁሉን ዘረፈን!"
"አድባር መስሎ የለም እንዴ?" አለ አንድ ሰላላ ድምፅ
"መቼም ከድንጋይ አይሻልም እና አንገታችሁን ቆርጣችሁ ጭንቅላቱን ትከሉልን። ቅቤ እንቀባው..."
"ኢትዮጵያዊያን" ሲል በአካባቢው ያለ ድምፅ እረጭ አለ
"ሀገር ይዘው ህዝብ ይፈልጋሉ። እንደ እስራኤልሎች ህዝብ ይዘው ሀገር በፈለጉ እንዴት ደግ ነበር፣............

የተጠላው እንዳልተጠላ
269 viewsNatty שלום, 07:44
Buka / Bagaimana
2023-06-04 20:25:47 ኒርቫና ምንድን ነው?


ኒርቫና የሚለው ቃል በተለይ በሂንዱይዝም እና በቡዲዝም እምነት ተለታዮች ዘንድ የሚታወቅ እና የሕይወታቸው መርሕ አድርገው የሚከተሉት ፍልስፍናቸው ነው ። አንዳንድ መጽሔቶች ኒርቫና ማለት #ቅድስና ማለት ነው ሲሉ ይተረጉሙታል ።


የቡድሂዝም የእምነት ፍልስፍና መስራች የሆነው ጉተማ ቡተማ አጊንቶታል ብለው የሚያምኑት የቅድስና የመጨረሻው ንፃሬ ኒርቫና ይባላል ። አንድ ሰው ኒርቫና ላይ ደረሰ የሚባለው...ፍላጎቶቹን ወደ መጨረሻው ደረጃ ማውረድ ሲችል ነው...የሚል የሕይወት ፍልስፍናም አላቸው ።



ኒርቫና ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው ሰውን አይጎዳም...ሰዎች ቢጎዱትም ውስጣዊ ማንነታቸው መልካም መሆኑን ስለሚያውቅ መልሶ ሰዎችን አይጎዳም ይላሉ ። ለዚህም ነው እንዲህ ሲሉ የሚያስተምሩት...

" የምድር ውሀ ከሚበክሉት ነገሮች ሲፀዳ ሽታ አልባ ፣ ጣዕም አልባ ፣ ቀለም አልባ...ይሆናል ። እናንተም ውስጣችሁን ከሚበክሉት ነገሮች ነፃ ስትወጡ ለሰው የምትስማሙ ትሆኑ እና ከተጽእኖዎች ነፃ ማንነትን ትላበሰላችሁ ኒርቫና የሚባለውም ይኸው ነው ። "

እያሉ ያስተምራሉ...

የኒርቫና ትርጉም ጥልቅ የሆነና ብዙ ትንታኔን የሚሻ ቢሆንም ትንሽ ጠብታን ለመስጠት ያህል እቺን ጀባ አልናችሁ...።


ምንጭ ፦ world philosophical magazine እንዲሁም
ጥበብ ከጲላጦስ
323 viewsPeter, 17:25
Buka / Bagaimana
2023-06-01 17:45:59 #Repost

በአሁኑ ጊዜ እንዴት የሰው ልጅ በማይታይ ፈጣሪ ሊያምን ቻለ ? በሚለው ጠቅላይ እንቆቅልሽ ዙሪያ ሶስት አንኳር ንድፈ-ሀሳቦች በስፋት ይቀነቀናሉ። እነዚህም :-

1) ግለኛ ንድፈ-ሀሳብ (Subjective theory)  2)የዝግመተ ለውጥ ሀሳብ (Evolution theory) እና 
3) የአሀዱ አምላክ ንድፈ ሀሳብ (original monotheism theory) ናቸው


1 )ግለኛ ንድፈ-ሀሳብ (Subjective theory)

በዚህ ንድፈ  ሀሳብ እምነት መሰረት ሃይማኖት ከሰዋዊ (ግለሰባዊ) ተፈጥሮ የሚመነጭ ነው ሰዎች በዚህ ውጥንቅጡ በወጣና በጥያቄዎች በተሞላ ምድር ተስፋና ትርጉም የሚጭርባቸውን ሀይማኖትን መፍጠር ግላዊ ስነ-ልቦናዊ ተፈጥሯቸው ያስገድዳቸዋል የዚህ ንድፈ-ሀሳብ አቀንቃኞች እንደሚሉት ይህ የእምነት ስሪት ቅንጣት (religious element) ልብ በማንለው የአእምሯችን ክፍል ያለ ፍቃዳችን በራሱ ጊዜ የሚፈጠር ነው ባህልና አስተሳሰብ ከቦታ ቦታ ይለያያል። ፈጣሪን መፈለግና እምነትን ማበጀት ግን ሰዋዊና ዓለም አቀፋዊ ተፈጥሮ ነው:: ሲያጠቃልሉም ! ይህ ሀይማኖትን የማበጀት ተግባር ሰዎች በግላችን ከባህልና ከአካባቢያችን የምንቀዳው ይመስለናል እንጂ እውነተኛ መፍለቂያው ግን ከግላዊ የአእምሯችን ጓዳ ነው
ፍሬድሪክ ሼሬልማኬር የዚህ ንድፈ ሀሳብ ሁነኛ አቀንቃኝ ሲሆን ሀይማኖት ከሰው ልጅ የጥገኝነት ባህሪ የሚፈልቅ ነገር እንደሆነ ይሞግታል የሰው ተፈጥሮና ፍላጎት ምሉዕ ስላልሆኑ ለዚህ የምሉዕነት ስብዕና ፍላጎትና ናፍቆት አጋዥ የሚሆን አካል ያስፈልገናል ያን ፍላጎታችንን ፈጣሪ (God) ለሚባል ነገር አስተላለፍነው ይለናል፡፡
ሌላው ሉድዊ ፈርባች የተባለ ተመራማሪ እንደሚለው ደግሞ ፈጣሪ የሚለው ፅንስ - ሀሳብ ፍፁም ሰብ (perfect human) ከመፈለግ የመነጨ ነው ሲግመን ፍሮይድም ተቀራራቢ ትንታኔን ይስጣል እንደ ፍሩድ እምነት የፈጣሪ በሰዎች መፈጠር መነሻቸው ፍፁም ምሳሌ ኣባት (father irnage) ከመሻቱ ጋር የተሳሰረ ነው ይለናል።

2. የዝግመተ ለውጥ ንድፈ-ሀሳብ (Evolution theory)

ይህ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኝ ንድፈ-ሀሳብ ልክ እንደ ግለኛ (subjective) ሀሳብ አቀንቃኞች ሁሉ የሀይማኖት ምንጭ የሰው ልጅ ልቦና እንደሆነ ቢቀበልም የሀይማኖት እድገትና ሰፊ ቅቡልነት የተረጋገጠው ግን በሰው ልጅ የታሪክ መስተጋብር ዝግመተ ለውጥ ሂደት ነው ብሎ ያምናል  በቀደምት ጥንታዊ ሰው ዘንድ አንድ » ጉልበት ያለው መንፈስ እንዳለ ጥርጣሬ ነበረ፡፡ ይህ ሀይል ግን ጨካኝና ተፈጥሮን .... አንበርክኮ የሚገዛ እንደሆነ ያምኑ ነበር ከማሌኔዥያ ጥንታዊ ህዝቦች ስያሜ በመነሳትም ለዚህ ወዳጃዊ ላልሆነ መንፈሳዊ ሀይል «ማና» (Maana) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል ማና በብዛት ሊገኝባቸው የሚችሉ ቦታዎች እንዳሉም ይታመን ነበር ለምሳሌ በታላላቅ ዛፎች በተለያዩ ዓለቶች በውስን የእንስሳት ዝርያዎች ወዘተ በብዛት ተከማችቶ ይገኛል ተብሎ ይታመን ነበር የጥንቱ ሰው ዓላማ የነበረው ይህን ጠንካራ መንፈስ (ማና) ላኑሮአቸው በሚመች መልኩ እንዲያግዛቸው ማድረግ ነበር  በኋላም ይህን መንፈስ በጣኦታትና በተወሰኑ የተፈጥሮ ሀይሎች ብቻ እንዲቀመጥና እንዲመለክ አደረጉ፡፡ ቀጣዩ ደረጃ ደግሞ ይህን መንፈስ ሰዋዊ ማድረግ ነበር የተወሰኑ ሰዎች ላይ ይህ መንፈስ እንደተገለጠላቸው ታመነ ይህም አኒሚዝም (Animism) ይባላል እየቆየ ሲሄድ መንፈሱ የሚያርፍባቸው ሁለት ጎራዎች ተለዩ የተፈጥሮ መንፈስ (nature spirit) እና የቅ/አያቶች መንፈስ (Ancestor spirit) ናቸው
የተፈጥሮ መናፍስት ሰዋዊ ገጽታ ያላቸውና በተክሉች፣ በዓለቶች፣ በሀይቆች ወዘተ ራሳቸውን ተቀማጭ ያደረጉ ናቸው የቅ/አያቶች መንፈስ ግን በጣኦታት ወይም ባሉና በሌሉ ሰዎች ሊወከል ይችላል ስለዚህ እነዚህ ሁለት አይነት መናፍስት ተቆጥተው ሊያደርሱ ከሚችሉት አደጋ ለመጠበቅ ጥንታዊው ሰው ከመናፍስቱ ጋር መልካም ወዳጅነትን ለመመስረት ጣረ
በዝግመተ - ለውጡ ሂደት መሰረት በብዙ አማልክት ( መናፍስት) ማመን (polytheism) ቀጥሎ የሚመጣ ደረጃ ነው በተለያዩ መናፍስት አማኝ የነበሩ ህዝቦች ቀስ በቀስ የብዙ መናፍስትን ወካይ በሆኑ አማልክት (ጣኦታት) ተገዙ  ቀጠሉና በሂደት ከአማልክቶቹ ውስጥ ለተወሰኑቱ አማልክት ብቻ መገዛት (henotheism) ደረጃ ተደረሰ፡፡ በዚህ ደረጃ ሁሉም አማኝ ለብዙ (ለተወሰኑ) አማልክት ይምበርከክ እንጂ ጥያቄው በነዚህ አማልክት ውስጥ ትልቁን አንድ አምላክ ማግኘት ነበር በመጨረሻም ከረጅም ዝግመታዊ የአምልኮ ሂደት በኋላ በአንድ ፍፁምና ጠቅላይ አምላክ ማመን (monotheism) ተሸጋገረ ይህም ሀይማኖት ተፀንሶ ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ሲሆን ወደ ፊት ደግሞ በዝግመተ- ለውጥ (Evolution) ሌላ መልክና ይዘት እንደሚይዝ ይጠበቃል፡፡

3) የአሀዱ አምላክ ንድፈ-ሀሳብ (Original Monotheism)

ይህ ንድፈ - ሀሳብ የብዙ ሀይማኖቶችን አቋም የሚያንፀባርቅ ሲሆን እምነት የመነጨው ፈጣሪ ራሱን ለሰው ልጅ ስለገለፀ ነው የሚል መቋጫ ያስቀምጣል፡፡ በዚህም መሰረት ጥንታዊው የሰው ልጅ የመጀመሪያው እምነት አሀዳዊ አምልኮ (monotheism) ነበር ሲል ይሞግታል፡፡ የዚሁ ንድፈ - ሀሳብ አቀንቃኝ ከሆኑት መሀል ዶ/ር ዊንፍሬድ ኮርዶን የጥንታዊው ሰው እምነት መገለጫ ነበሩ ያላቸውን ዘጠኝ ባህርያት አስቀምጧል፡፡ እነዚህም

1) ፈጣሪ ሰዋዊ አምላክ ነው (ወዳጃዊ ያልሆነ ነው ብለው ያምኑ ነበር ከሚሉት በተለየ መልኩ

2) ፈጣሪ ተባዕታይ ይዘትና መገለጫዎች አሉት
3) ፈጣሪ ነዋሪነቱ በሰማይ ነው፡፡
4) ፈጣሪ ታላቅ ጥበብና ሀይል አለው
5) ፈጣሪ መልካምና እኩይ ብሎ ለነገሮች ክፍፍል ሰጥቷል
6)ፈጣሪ ዓለምን ፈጥሯል
7) የሰው ልጆች የተፈጠሩት በፈጣሪ ስለሆነ የሱን ፍላጎት መከተል አለባቸው
8) የሰው ልጆች ከፈጣሪ አፈንግጠዋል
9) ፈጣሪ የሰው ልጆች ከሀጥያት የሚነፁበትን መንገድ አበጅቶላቸዋል የሚሉት ናቸው፡፡

የጥንታዊ ህዝቦች በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ እነዚህን ዘጠኝ ነጥቦች በአምል ኳቸው አንፀባርቀው እንደነበረ የሚሞግቱት የዚህ ንድፈ-ሀሳብ አቀንቃኞች ከዚህ ፍፁም አህዳዊ አምልኮ ተነስተው የሰው ልጆች ወደ ብዙ አማልክት ማመን (polytheism) እና በፈጣሪ ጭራሽ አለማመን (Atheism) እንደተሸጋገሩና እንደተሰነጣጠቁ ያስረዳሉ ለዚህ ትንታኔአቸው አስረጅ አድርገው የሚያቀርቡት አሁን በዓለም ላይ ያሉ ሁሉም ሀይማኖቶች ታሪኮቻቸው የፀሎት ስርዓታቸው ቀኖናቸው ወዘተ መመሳሰል የዚሁ ከአንድ ምንጭ መቀዳታቸው ነፀብራቅ እንደሆነ አስረግጠው ይናገራሉ

ዳሰሳ ዘ ሀይማኖት
516 viewsPeter, 14:45
Buka / Bagaimana
2023-05-31 19:55:38 ከፍልስፍና ዓለም


ለምንድን ነው ሌሎች ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ፍልስፍናን ማፍለቅ ያልቻሉት?

ፍልስፍና የተጀመረው በ6ኛው ክ/ዘ (BC) በግሪክ ነው ምንም እንኳ በወቅቱ አክሱምን ጨምሮ ሌሎች ጥንታዊ ሥልጣኔዎች የነበሩ ቢሆንም አንዳቸውም ግን ፍልስፍናን ማፍለቅ አልቻሉም  ለምን ይሆን? ‹‹Thales of Miletus and the Birth of Greek Philosophy ›› በሚለው የቪዲዮ ሌክቸር Leonard Peikoff ‹‹ሌሎች ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ፍልሰፍናን እንዳያመነጩ የከለከላቸው ሁለት ምክንያቶች አሉ›› ይላል

* የመጀመሪያው፣ ‹‹በዚህ ዓለም ላይ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም ፤ በዚህ ዓለም ላይ ያሉ ክስተቶች በሙሉ በሌላ በማይታይ ኃይል የሚዘወሩ ናቸው›› ብለው ማመናቸው ነው ይሄ እንግዲህ እኛም በተደጋጋሜ ‹‹ማህበረሰባችን አእምሮ ውስጥ በጥልቀት የሰረፀው የተአምራዊነት እሳቤ የነገሮችን መንስኤ ለማወቅ ጭራሽ ፍላጎቱ እንዳይኖረን አድርጎናል፤ መንስኤን ሳናውቅ ደግሞ ፍልስፍናም ሆነ ሳይንሳዊ ዕውቀትን ማመንጨት አንችልም›› ያልነው ነው፡፡
"""""
* ሁለተኛው ደግሞ፣ ‹‹ይህ ህይወት እና መኖሪያዋ ምድር የማይታወቁ ብቻ ሳይሆን ‹‹እርኩስ ናቸው›››› ብለው ማሰባቸው ነው፡፡
እነዚህ ሁለት እሳቤዎች ግን በግሪክ አልነበሩም  ከዚህም በተጨማሪ፣ ሁለት ተያያዥ ነገሮች ከሌሎች ሥልጣኔዎች በተለየ ግሪኮች ሳይንስንና ፍልስፍናን እንዲያፈልቁ እረድቷቸዋል፡፡

* የመጀመሪያው፣ ፖለቲካዊ ምክንያት ነው  እንደሚታወቀው ሄለናውያን ከሌሎች አጎራባች ህዝቦች በተለየ የፖለቲካ ነፃነት ነበራቸው ይሄም በነፃነት ለማሰብ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮላቸዋል የፖለቲካ ነፃነት ያልነበራቸው የአቴንስ ጎረቤቶች (ለምሳሌ ስፓርታ) ፍልስፍናን ማፍለቅ አልቻሉም


* ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሃይማኖታዊ ነው  እንደ ሌሎች ህዝቦች ሁሉ ግሪኮችም ሃይማኖት የነበራቸው ቢሆንም፣ ሃይማኖታቸው ግን የተለየ ነበር ግሪኮቹ ብዙ አማልክት የነበራቸው ቢሆንም፣ እነዚህ አማልክት ግን የዩኒቨርሱ ፈጣሪም ሆነ አስተዳዳሪ ወይም ገዥ አይደሉም  ግሪኮቹ፣ ‹‹ዩኒቨርስ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ተፈጥሯዊ ክስተት ነው›› በማለት የሚያምኑ ሲሆን፤ ‹‹አማልክቱም ልክ እንደ ሰዎችና ሌሎች ፍጡራን የዚህ ተፈጥሯዊ ክስተት ውጤት ናቸው እንጂ ፈጣሪ አይደሉም›› ይላሉ  ለዚህም ነው የግሪክ አማልክቶች ለሰዎች በጣም ቅርብና ወዳጅ የሆኑት  ስለዚህ፣ አማልክቱ በዩኒቨርሱ ሥራ ውስጥ ጣልቃ አይገቡም፤ ደግሞም አይችሉም ይሄም ማለት የግሪኮቹ አማልክቶች ‹‹ሁሉን ቻይ›› እና ‹‹ሁሉን አዋቂ›› አይደሉም፡፡
በዚህም የተነሳ፣ ለግሪኮቹ ይሄ ዓለም ‹‹ሊታወቅ የሚችል›› እና ‹‹ለመኖር መልካም የሆነ ሥፍራ ነው›› ይሄም ማለት፣ ሌላ የተስፋ ዓለም ሳትናፍቅ በዚህ ዓለም ላይ ስኬታማና ደስተኛ ሆነህ መኖር ትችላለህ ምንም እንኳ ግሪኮቹ በነፍስ ዘላለማዊነት የሚያምኑ ቢሆንም ምድርን የደስታ ቦታ ማድረጋቸው ግን ‹‹ከሞት በኋላ ህይወት›› የሚል ናፍቆት እንዳይጠናዎታቸው አድርጓቸዋል፡፡

‹‹በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች…›› ይላል Peikoff ‹‹በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ግሪኮቹ ‹‹ዕውቀትን የሚቻል ብቻ ሳይሆን የሚወደድና ልናገኘውም የሚገባ (the Love of Wisdom)›› በማድረጋቸው የተነሳ ምድራችን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ አሳቢያን የተከማቹባትን ሥልጣኔ (a Civilization of Thinkers) ከወደ ግሪክ ማግኘት ችላለች፡፡


Philosophy


The sound of peasants philosopher !
520 viewsPeter, edited  16:55
Buka / Bagaimana
2023-05-31 19:55:02
412 viewsPeter, 16:55
Buka / Bagaimana
2023-05-30 19:00:23 እልፍ ጊዜያት ጥሩ መፅሐፍ የትኞቹ እንደሆኑ እንጠየቃለን ሰው ቢያነባቸው በብዙ ያተርፍባቸዋል ብለን የምንጋብዛቸው መፅሃፍትን አያሌ ናቸው እኔያቹ ደሞ ተቃራኒ ነገሮችን ማሰስ ትንሽ ይማርከኛል እናም የምትጠሏቸውን መፅሐፍት ሰው አይንብባቸው የምትሉት፦ በአጠቃላይ አይረቡም የምትሏቸውን መፅሐፍ ዘርዘር አድርጉልን እስኪ ምክንያታችሁንም አያይዛችሁ
505 viewsNatty שלום, 16:00
Buka / Bagaimana
2023-05-29 15:50:30 ፈረንሳዊው ደራሲ ኤሚል ዞላ እንዲህ ይላል። " civilization will not attain iys perfection until the last stone from the last church falls on the last priest" ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባ ሰሞን በአክሱም ስልጣኔ ላይ የደረሰውን መጠን የለሽ ውድመት ያነበበ ሰው ዞላ ስህተተኛ ነው ለማለት አይደፍርም። ደክተር ነጋ ጌጡ የተባሉ ጸሐፊ 'የቅማንት ሕዝብ ታሪክ' በተሸኘ መጽሐፋቸው በዝርዝር እንደገለፁት ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የገባ ሰሞን በአክሱም የሆነው የቻይናን የባህል አብዮት አመታትን የሚያስቅ ነበር።
.
.
.

"ብሩህ አለምነህ 'የኢትዮጵያ ፍልስፍና' በሚል ርዕስ በ2010 ዓ.ም ባሳተመው ለዚህ መጣጥፍ በብዙ ነገር ግብዓት በሆነልኝ መጽሐፉ እንዲህ ይላል"...." በ1500 ዓመታት የብሕትውና ዘመናችን ውስጥ ተቃርኖን አጥፍተን በአንድ ዓይነት የአንብሮ ሐሳብ ላይ ብቻ ተቸንክረን ስለቀረን አስተራረሳችን፣ አመጋገባችን፣ የቤት ቁሳቁሶቻችን፣ የሥራና የመጓጓዣ መሣሪያዎቻችን፣ የቤት አሠራራችን፣ አመጋገባችን፣ አስተሳሰባችን ሁሉ ለውጥ አይታይበትም። ሙያችን ሁሉ የምንኩስና ክርስትናን መተንተን ሆነ።ለ1500 ዓመታት መጽሐፍ ቅዱስ ስንጠቅስ እና ስናብራራ ከራሳችን አንድ ሙያ እንኳን ሳናፈልቅ ዘመናችንን በላነው። ዕውቀትም - ሥነምግባርም፣ ሕይወትም -እስትንፋስም፣ ርዕይም - ሕልምም ሁሉ መንፈሳዊ ሕይወት ብቻ ሆነ ። መንፈሳዊ ሕይወት የማናቸውም ነገር መጨረሻ እና መደምደሚያ ሆነ

ከባዶ ላይ መዝገን ያዕቆብ ብርሃኑ "እውን ኢትዮጵያ ሥልጡን ሀገር ነበረች?"
603 viewsNatty שלום, 12:50
Buka / Bagaimana
2023-05-29 08:58:59 hunger games ይሉት ነገር ከ 12 ወረዳዎች(በእርግጥ 13 ናቸው) የተመረጡ 12 ወንድ እና 12 ሴት የሚሳተፉበት የመገዳደል ጨዋታ ነው ዝግናኔውን ህዝቡ በቀጥታ ስርጭት ይመለከተው ዘንድ ይቀርበለታል በዚህ ደርሰት ውስጥ ታሪኩ የሰውልጅ የሞራል ልእልና ቆም ብለን እንድንመረምረው ይጋብዘናል ፕሬዝዳንት ስኖ ስለጨዋታው አስፈላጊነት እንዲህ ሲል ያብራራል War, terrible war. Widows, orphans, a motherless child. This was the uprising that rocked our land. Thirteen districts rebelled against the country that fed them, loved them, protected them. Brother turned on brother until nothing remained. And then came the peace, hard fought, sorely won. A people rose up from the ashes and a new era was born. But freedom has a cost. When the traitors were defeated, we swore as a nation we would never know this treason again. And so it was decreed that, each year, the various districts of Panem would offer up, in tribute, one young man and woman to fight to the death in a pageant of honor, courage and sacrifice. The lone victor, bathed in riches, would serve as a reminder of our generosity and our forgiveness. This is how we remember our past

ከጦርነት የመትረፋችንን ነገር የጦርነቱን ስቆቃ በሚያስታውስ ጨዋታ እንዘክረው እንደማለት

ጨዋታው የሰውልጅን ወደ ጫካው ስርአት ይመልሰዋል ለመትረፍ መግደል ይኖርብሃል ካልገደልክ ትገደላለህ መቼስ መትረፍ ማንስ አይፈልግም የብዙዎቻች የሞራል ድንጋጌዎች እዚህ ጋር ጉልበት ያጣሉ ቅድስናችን እተርፍ ዘንድ መግደል ነውር ነው ብሎ ሊሰብከን አቅሙን ያጣል....የመግደል ነውርነት እነዚች ነጥብ ላይ ወደ ፅድቅ ይቀየራል መግደል ወንጀል ባይሆን የምንገለው ሰው ብዛት ዝርዝር አንድ ጥራዝ አይወጣውምን....ይህን ነገር ዘመነኞቹ የህግ ሊቃውንት ራስን መከላከል ብለው ያሽሞነሙኑታል.....የሞራል እና የስነምግባር ህጎች ቋሚ በነገሮች እና በሁኔታዎች የማይቀያየሩ መሆን የለባቸው ወይስ እንደየሁኔታው እና እንደፍላጎቶቻችን ቅርፅ እየሰጠን የምንከተላቸው ናቸውን??

ይህንን የሚያጠናክርልኝ ምን ላይ እንዳነበብኩት ትዝ የማይለኝን ፅሁፍ እንሆ ስሙት መንገደኛ የጫነ አይሮፕላን የበረዶ በረሃ ላይ ይከሰከሳል አብዛኛው ሲሞት ጥቂቱ ይተርፍል የተረፉትም በረሃብ ለሚሞቱ ሆነ እዚህ ጋር አንድ ጉብል ይነሳ እና ወደ ሞቱት እያመላከተ እነዚህ አሁን ሰው መሆን አቁመዋል ስጋቸው እንመገው እና ህይወታችንን እናቆይ አላቸው በህብረት አወገዙት ሲወል ሲያድር ግን ሞት ሸተታቸው የሞትን ክርፋት መቋቋም አቃተን ይሉ ጀመር ከጉብሉ የምግብ ጥቆማ በስተቀር ሌላ ነገር አጡ ህይወታችንን እስካቆየለን ድረስ የዘመዶቻችን አስክሬን ብንበላ ምንስ ክፋት አለው ብለው ተማከሩ ፈጣሪ የሰጠንን ህይወት ከመጠበቅ በላይ ምንስ ቅድስ ይህ አስክሬን የተቀደሰ በፈጣሪ የተላከ መና እስከማለት...በህብረት ሳይሆን አንድ በአንድ ወደ ሞቱት ሄዱ (ዝርዝር ታሪኩ ጠፍቶኛል ቅር ላለው)
596 viewsNatty שלום, 05:58
Buka / Bagaimana