Get Mystery Box with random crypto!

hunger games ይሉት ነገር ከ 12 ወረዳዎች(በእርግጥ 13 ናቸው) የተመረጡ 12 ወንድ እና | ከፍልስፍና ዓለም

hunger games ይሉት ነገር ከ 12 ወረዳዎች(በእርግጥ 13 ናቸው) የተመረጡ 12 ወንድ እና 12 ሴት የሚሳተፉበት የመገዳደል ጨዋታ ነው ዝግናኔውን ህዝቡ በቀጥታ ስርጭት ይመለከተው ዘንድ ይቀርበለታል በዚህ ደርሰት ውስጥ ታሪኩ የሰውልጅ የሞራል ልእልና ቆም ብለን እንድንመረምረው ይጋብዘናል ፕሬዝዳንት ስኖ ስለጨዋታው አስፈላጊነት እንዲህ ሲል ያብራራል War, terrible war. Widows, orphans, a motherless child. This was the uprising that rocked our land. Thirteen districts rebelled against the country that fed them, loved them, protected them. Brother turned on brother until nothing remained. And then came the peace, hard fought, sorely won. A people rose up from the ashes and a new era was born. But freedom has a cost. When the traitors were defeated, we swore as a nation we would never know this treason again. And so it was decreed that, each year, the various districts of Panem would offer up, in tribute, one young man and woman to fight to the death in a pageant of honor, courage and sacrifice. The lone victor, bathed in riches, would serve as a reminder of our generosity and our forgiveness. This is how we remember our past

ከጦርነት የመትረፋችንን ነገር የጦርነቱን ስቆቃ በሚያስታውስ ጨዋታ እንዘክረው እንደማለት

ጨዋታው የሰውልጅን ወደ ጫካው ስርአት ይመልሰዋል ለመትረፍ መግደል ይኖርብሃል ካልገደልክ ትገደላለህ መቼስ መትረፍ ማንስ አይፈልግም የብዙዎቻች የሞራል ድንጋጌዎች እዚህ ጋር ጉልበት ያጣሉ ቅድስናችን እተርፍ ዘንድ መግደል ነውር ነው ብሎ ሊሰብከን አቅሙን ያጣል....የመግደል ነውርነት እነዚች ነጥብ ላይ ወደ ፅድቅ ይቀየራል መግደል ወንጀል ባይሆን የምንገለው ሰው ብዛት ዝርዝር አንድ ጥራዝ አይወጣውምን....ይህን ነገር ዘመነኞቹ የህግ ሊቃውንት ራስን መከላከል ብለው ያሽሞነሙኑታል.....የሞራል እና የስነምግባር ህጎች ቋሚ በነገሮች እና በሁኔታዎች የማይቀያየሩ መሆን የለባቸው ወይስ እንደየሁኔታው እና እንደፍላጎቶቻችን ቅርፅ እየሰጠን የምንከተላቸው ናቸውን??

ይህንን የሚያጠናክርልኝ ምን ላይ እንዳነበብኩት ትዝ የማይለኝን ፅሁፍ እንሆ ስሙት መንገደኛ የጫነ አይሮፕላን የበረዶ በረሃ ላይ ይከሰከሳል አብዛኛው ሲሞት ጥቂቱ ይተርፍል የተረፉትም በረሃብ ለሚሞቱ ሆነ እዚህ ጋር አንድ ጉብል ይነሳ እና ወደ ሞቱት እያመላከተ እነዚህ አሁን ሰው መሆን አቁመዋል ስጋቸው እንመገው እና ህይወታችንን እናቆይ አላቸው በህብረት አወገዙት ሲወል ሲያድር ግን ሞት ሸተታቸው የሞትን ክርፋት መቋቋም አቃተን ይሉ ጀመር ከጉብሉ የምግብ ጥቆማ በስተቀር ሌላ ነገር አጡ ህይወታችንን እስካቆየለን ድረስ የዘመዶቻችን አስክሬን ብንበላ ምንስ ክፋት አለው ብለው ተማከሩ ፈጣሪ የሰጠንን ህይወት ከመጠበቅ በላይ ምንስ ቅድስ ይህ አስክሬን የተቀደሰ በፈጣሪ የተላከ መና እስከማለት...በህብረት ሳይሆን አንድ በአንድ ወደ ሞቱት ሄዱ (ዝርዝር ታሪኩ ጠፍቶኛል ቅር ላለው)