Get Mystery Box with random crypto!

ከፍልስፍና ዓለም ለምንድን ነው ሌሎች ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ፍልስፍናን ማፍለቅ ያልቻሉት? ፍልስ | ከፍልስፍና ዓለም

ከፍልስፍና ዓለም


ለምንድን ነው ሌሎች ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ፍልስፍናን ማፍለቅ ያልቻሉት?

ፍልስፍና የተጀመረው በ6ኛው ክ/ዘ (BC) በግሪክ ነው ምንም እንኳ በወቅቱ አክሱምን ጨምሮ ሌሎች ጥንታዊ ሥልጣኔዎች የነበሩ ቢሆንም አንዳቸውም ግን ፍልስፍናን ማፍለቅ አልቻሉም  ለምን ይሆን? ‹‹Thales of Miletus and the Birth of Greek Philosophy ›› በሚለው የቪዲዮ ሌክቸር Leonard Peikoff ‹‹ሌሎች ጥንታዊ ሥልጣኔዎች ፍልሰፍናን እንዳያመነጩ የከለከላቸው ሁለት ምክንያቶች አሉ›› ይላል

* የመጀመሪያው፣ ‹‹በዚህ ዓለም ላይ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም ፤ በዚህ ዓለም ላይ ያሉ ክስተቶች በሙሉ በሌላ በማይታይ ኃይል የሚዘወሩ ናቸው›› ብለው ማመናቸው ነው ይሄ እንግዲህ እኛም በተደጋጋሜ ‹‹ማህበረሰባችን አእምሮ ውስጥ በጥልቀት የሰረፀው የተአምራዊነት እሳቤ የነገሮችን መንስኤ ለማወቅ ጭራሽ ፍላጎቱ እንዳይኖረን አድርጎናል፤ መንስኤን ሳናውቅ ደግሞ ፍልስፍናም ሆነ ሳይንሳዊ ዕውቀትን ማመንጨት አንችልም›› ያልነው ነው፡፡
"""""
* ሁለተኛው ደግሞ፣ ‹‹ይህ ህይወት እና መኖሪያዋ ምድር የማይታወቁ ብቻ ሳይሆን ‹‹እርኩስ ናቸው›››› ብለው ማሰባቸው ነው፡፡
እነዚህ ሁለት እሳቤዎች ግን በግሪክ አልነበሩም  ከዚህም በተጨማሪ፣ ሁለት ተያያዥ ነገሮች ከሌሎች ሥልጣኔዎች በተለየ ግሪኮች ሳይንስንና ፍልስፍናን እንዲያፈልቁ እረድቷቸዋል፡፡

* የመጀመሪያው፣ ፖለቲካዊ ምክንያት ነው  እንደሚታወቀው ሄለናውያን ከሌሎች አጎራባች ህዝቦች በተለየ የፖለቲካ ነፃነት ነበራቸው ይሄም በነፃነት ለማሰብ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮላቸዋል የፖለቲካ ነፃነት ያልነበራቸው የአቴንስ ጎረቤቶች (ለምሳሌ ስፓርታ) ፍልስፍናን ማፍለቅ አልቻሉም


* ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ሃይማኖታዊ ነው  እንደ ሌሎች ህዝቦች ሁሉ ግሪኮችም ሃይማኖት የነበራቸው ቢሆንም፣ ሃይማኖታቸው ግን የተለየ ነበር ግሪኮቹ ብዙ አማልክት የነበራቸው ቢሆንም፣ እነዚህ አማልክት ግን የዩኒቨርሱ ፈጣሪም ሆነ አስተዳዳሪ ወይም ገዥ አይደሉም  ግሪኮቹ፣ ‹‹ዩኒቨርስ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ተፈጥሯዊ ክስተት ነው›› በማለት የሚያምኑ ሲሆን፤ ‹‹አማልክቱም ልክ እንደ ሰዎችና ሌሎች ፍጡራን የዚህ ተፈጥሯዊ ክስተት ውጤት ናቸው እንጂ ፈጣሪ አይደሉም›› ይላሉ  ለዚህም ነው የግሪክ አማልክቶች ለሰዎች በጣም ቅርብና ወዳጅ የሆኑት  ስለዚህ፣ አማልክቱ በዩኒቨርሱ ሥራ ውስጥ ጣልቃ አይገቡም፤ ደግሞም አይችሉም ይሄም ማለት የግሪኮቹ አማልክቶች ‹‹ሁሉን ቻይ›› እና ‹‹ሁሉን አዋቂ›› አይደሉም፡፡
በዚህም የተነሳ፣ ለግሪኮቹ ይሄ ዓለም ‹‹ሊታወቅ የሚችል›› እና ‹‹ለመኖር መልካም የሆነ ሥፍራ ነው›› ይሄም ማለት፣ ሌላ የተስፋ ዓለም ሳትናፍቅ በዚህ ዓለም ላይ ስኬታማና ደስተኛ ሆነህ መኖር ትችላለህ ምንም እንኳ ግሪኮቹ በነፍስ ዘላለማዊነት የሚያምኑ ቢሆንም ምድርን የደስታ ቦታ ማድረጋቸው ግን ‹‹ከሞት በኋላ ህይወት›› የሚል ናፍቆት እንዳይጠናዎታቸው አድርጓቸዋል፡፡

‹‹በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች…›› ይላል Peikoff ‹‹በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ግሪኮቹ ‹‹ዕውቀትን የሚቻል ብቻ ሳይሆን የሚወደድና ልናገኘውም የሚገባ (the Love of Wisdom)›› በማድረጋቸው የተነሳ ምድራችን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ አሳቢያን የተከማቹባትን ሥልጣኔ (a Civilization of Thinkers) ከወደ ግሪክ ማግኘት ችላለች፡፡


Philosophy


The sound of peasants philosopher !