Get Mystery Box with random crypto!

ኒርቫና ምንድን ነው? ኒርቫና የሚለው ቃል በተለይ በሂንዱይዝም እና በቡዲዝም እምነት ተለታዮች | ከፍልስፍና ዓለም

ኒርቫና ምንድን ነው?


ኒርቫና የሚለው ቃል በተለይ በሂንዱይዝም እና በቡዲዝም እምነት ተለታዮች ዘንድ የሚታወቅ እና የሕይወታቸው መርሕ አድርገው የሚከተሉት ፍልስፍናቸው ነው ። አንዳንድ መጽሔቶች ኒርቫና ማለት #ቅድስና ማለት ነው ሲሉ ይተረጉሙታል ።


የቡድሂዝም የእምነት ፍልስፍና መስራች የሆነው ጉተማ ቡተማ አጊንቶታል ብለው የሚያምኑት የቅድስና የመጨረሻው ንፃሬ ኒርቫና ይባላል ። አንድ ሰው ኒርቫና ላይ ደረሰ የሚባለው...ፍላጎቶቹን ወደ መጨረሻው ደረጃ ማውረድ ሲችል ነው...የሚል የሕይወት ፍልስፍናም አላቸው ።



ኒርቫና ደረጃ ላይ የደረሰ ሰው ሰውን አይጎዳም...ሰዎች ቢጎዱትም ውስጣዊ ማንነታቸው መልካም መሆኑን ስለሚያውቅ መልሶ ሰዎችን አይጎዳም ይላሉ ። ለዚህም ነው እንዲህ ሲሉ የሚያስተምሩት...

" የምድር ውሀ ከሚበክሉት ነገሮች ሲፀዳ ሽታ አልባ ፣ ጣዕም አልባ ፣ ቀለም አልባ...ይሆናል ። እናንተም ውስጣችሁን ከሚበክሉት ነገሮች ነፃ ስትወጡ ለሰው የምትስማሙ ትሆኑ እና ከተጽእኖዎች ነፃ ማንነትን ትላበሰላችሁ ኒርቫና የሚባለውም ይኸው ነው ። "

እያሉ ያስተምራሉ...

የኒርቫና ትርጉም ጥልቅ የሆነና ብዙ ትንታኔን የሚሻ ቢሆንም ትንሽ ጠብታን ለመስጠት ያህል እቺን ጀባ አልናችሁ...።


ምንጭ ፦ world philosophical magazine እንዲሁም
ጥበብ ከጲላጦስ