Get Mystery Box with random crypto!

አልጋ የማንጠፍ ፍልስፍና ......ሆ ሀገሩ ሁሉ ምነካውን ነክነትን አእምሯቸው ላይ የዘራው የእ | ከፍልስፍና ዓለም

አልጋ የማንጠፍ ፍልስፍና

......ሆ ሀገሩ ሁሉ ምነካውን ነክነትን አእምሯቸው ላይ የዘራው የእብደት ገበሬ ማነው .....እቺን ነገር ስሟት እንዲህም ሆነ......እናት የተባለች ሴት፣ ልጅ ለተባለ ፍጥረት የአልጋ አነጣጠፍ ቴክኒክ ማስማር ዘወትር ልማዷ ከሆነ ሰነበ ልጁ እንደሆነ አይሰማ

"አንደው እንዴት ብነግር ይገባህ ይሆን አንተዬ" እሷው ነች አዎ እናት ተብዬዋ ወለጂ ብለው ያስገደዷት ይመስል ንጭንጯ

መኝታህን ሳታነጥፍ አትውጣ ብዬ እምነግርህ ስንት ጊዜ ነው

"ማታ እተኛበት የለም እንዴ ባነጥፈውም መልሶ መበላሸቱ መች ይቀራል" ልጅ የተባለ ፍጥረት ይመልሳል ሞጥሟጣ ነገር... ሲመሽ እንደሚፈርስ የሚያውቀውን ነገር አሁን ላይ የመገንባቱ ትርጉም ሊገባው አልቻለም

ህይወታችን አልጋ በማንጠፍ እና እሱኑ መልሶ በማበላሸት የቀነበበ ሲሲፈሳዊ ጉዞ ነው አለ አሉ አድጎ.......



መኖርና እና መሞት ከሚለው የስጦታው ሀይሉ መፅሃፍ የተወሰደ(ገፅ 143)