Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

Alamat saluran: @ethiopian_digital_library
Kategori: Pekerjaan
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 64.47K
Deskripsi dari saluran

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru

2024-05-16 16:33:30 ትምሕርት ቤቶች በተዘጉባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሴት ተማሪዎች በግዳጅ እየተዳሩ ነው

በምስራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደሩ ሴት ተማሪዎችን ያለሀይባይነት ወደ ትዳር እየገፏቸው ነው፤ወላጆች ከፍተኛ ድግስ በመደገስ የኢኮኖሚ ችግር እንደደረሰባቸውም ተናግረዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን የይልማና ዴንሳ ወረዳ ነዋሪም ወላጆች ልጆቻቸውን ከት/ቤት እያስወጡ እየዳሩ ነው፤እስከ 10 ዓመት ህጻናት መዳራቸውን ማየታቸውን ገልጠዋል።

በአማራ ክልል የሰላም እጦት ሰበብ በአንዳንድ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው፣ ሴት ተማሪዎች ወደ ጋብቻ እየገቡ እንደሆነ ነዋሪዎችና ወላጆች አመልክተዋል፤ የክልሉ ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በበኩሉ በ9ወሩ ውስጥ ከ1000 በላይ ያለእድሜ ጋብቻ ጥቆማዎች ደርሶኛል ብሏል።

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ዶይቼ ቬሌ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደሚሉት በአንዳንድ አካባቢዎች ባሉ የፀጥታ ችግር ምክንቶች ትምህርት ቤቶች በአግባቡ ሥራ ባለመጀመራቸው እድሜያቸው ያልደረሰ ሴቶች ጭምር እየተዳሩ ነው፡፡ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን የደጋዳሞት ወረዳ ነዋሪ በተለያዩ የክፍል ደረጃ ያሉ ተማሪዎች ወደ ትዳር እየገቡ ነው፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን የእነማይ ወረዳ ነዋሪም አርሶ አደሩ ሴት ተማሪዎችን ያለሀይባይነት ወደ ትዳር እየገፏቸው ነው፡፡ ከፍተኛ ድግስ ስለሚያደርጉም አርሶ አደሮች የኢኮኖሚ ችግርም እየደረሰበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ጎጃም ዞን የይልማና ዴንሳ ወረዳ ነዋሪም እንዲሁ ወለጆች ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት እያስወጡ እያዳሩ ነው፤ እንደአስተያየት ሰጪው፣ እስከ 10 ዓመት ህፀናት መዳራቸውን ማየታቸውን ገልጠዋል፡፡

የሰሜን ጎጃም ዞን ጎንጂ ቆለላ ነዋሪ ለትምህርት ያላቸው ፍላጎት ባለው ወቅታዊ ሁኔታ እየቀነሰ በመሄዱ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ በትምህርት ላይ ያሉ ወጣት ተማሪዎች ወደ ትዳር እየገቡ ነው፡፡

በአማራ ክልል ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የህፃናት መብትና ድህንነት ማስጠበቅ ዳይሬክተር አቶ አሻግሬ ዘውዴ ባለፉት 9 ወራት 1 ሺህ አንድ መቶ 32 መዳር ከሚገባቸው እድሜ በታች የሆኑ ሴቶች ለመዳር መዘጋጀታቸውን ጥቆማ እንደደረሳቸው አመልክተዋል፡፡

በዚህም መሰረት የ335ቱ ተማሪዎች የጋብቻ ዝግጅት እንዲቋረጥ የተደረገ ሲሆን 216 ደግሞ የእድሜ ምርመራ ተደርጎ እድሜያቸው ባለመድረሱ የትዳር ዝግጅቱ ተቋርጧል ብለዋል፡፡ያም ሆኖ 192 ሴቶች ከእድሜያቸው በታች መዳራቸውን የገለጡ ሲሆን ድርጊቱን ለመከላከል አሁን ያለው የፀጥታ ሁኔታ አንድ አንቅፋት ነው ብለዋል፡፡

በ9 ወሩ 41 ጠለፋ በክልሉ የተመዘገበ ሲሆን 354 ደግሞ አስገድዶ መድፈር ሪፖርት እንደደረሳቸው ተናግረዋል፡፡ በድርጊቱ የተሳተፉ 79 ግለሰቦች ከ3 አስከ 14 ዓመት በሚደርስ የፍርድ ቤት የእስር ቅጣት እንደተወሰነባቸውም ገልጠዋል፡፡

በአማራ ክልል መመዝገብ ከነበረባቸው 6.2 ተማሪዎች መካከል 2.6 የሚሆኑት ወደትምህርት ቤት እንዳልመጡ፣ 350 የአንደኛና 225 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስራ እንዳልጀመሩ በመጋቢት 2016 ዓ ም የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ገልፀው እንደነበር ይታወሳል ። #DW_AMHARIC

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
5.1K viewsedited  13:33
Buka / Bagaimana
2024-05-13 12:39:38 በሬና አህያ

አንድ በሬ ወደ አንድ አህያ ሄዶ እንዲህ አለው፡፡ “በጣም ሰልችቶኛል፡፡ ያለምንም እረፍት ብዙ እሰራለሁ፡፡ ምን ባደርግ ይሻለኛል?”

አህያውም “እንግዲያው ነገ እንዲህ አድርግ፡፡ በጀርባህ ተኛና አሞኛል፣ ሆዴ ተነፍቷል፣ እያልክ እህ! እህ ብለህ አቃስት” አለው፡፡ በሬውም ይህንን አደረገ፡፡ በሚቀጥለውም ቀን ጌታው መጥቶ እንዲህ አለ “አይይ! በሬዬ ታሟል፡፡ ስለዚህ አህያው ይረስ፡፡” እናም አህያው የበሬውን ስራ በመስራቱ እጅግ ደከመው፡፡

በሬውም ወደ አህያው ጠጋ ብሎ ተጨማሪ ጥሩ ምክሮችን በደስታ ለማግኘት ካጠገቡ አረፍ አለና “ትናትና በጣም ጥሩ ቀን ነበር፡፡ ዛሬም አርፋለሁ፤ ነገም ስራ አልሄድም፡፡ ስለዚህ ገበሬውን እንዴት ማሳመን እንዳለብኝ ንገረኝ፡፡” ብሎ ጠየቀው፡፡

አህያውም “አዬዬ! እንደዚያ ይሻላል ብለህ ነው? ካልሰራህ እንደምትታረድ ሲያወሩ ሰምቻለሁ፡፡” አለው፡፡ በዚህም ምክንያት በሬው ወደ ስራው ለመመለስ ወሰነ፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
12.4K viewsedited  09:39
Buka / Bagaimana
2024-05-13 10:46:22 የሪሚዲያል ፈተና ከሰኔ 1-7/2016 ዓ.ም ወይም ከሰኔ 8-14/2016 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
11.6K views07:46
Buka / Bagaimana
2024-05-12 16:44:05 በየመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እጅግ ዘመናዊ የሆነ የመልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ ግንባታ ተከናውኗል

ስቱዲዮቹ በትምህርት ሚኒስቴር፣ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን፣ አሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ እና ሻያሾኔ ኩባንያ ትብብር በተተገበረ e-SHE የተባለ ፕሮግራም አማካኝነት የተገነቡ ናቸው።

ስቱዲዮቹ በ'ሪሶርስ ማዕከልነት' የሚያገለግሉ ሲሆን የዲጂታል ትምህርትን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ይኖራቸዋል።

ስቱዲዮቹ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መቋቋማቸው ተገልጿል።

እነዚህ ስቱዲዮች የከፍተኛ ትምህርት ሽግግርን በአምስቱ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በቅርብ ርቀት በሚገኙ አስር ክላስተር ዩኒቨርሲቲዎች ለማምጣት እንደሚያስችሉ ይጠበቃል።

መምህራን ስቱዲዮቹን በመጠቀም ለe-learning የሚጠቀሟቸውን ኮርሶች ማዘጋጀት ይችላሉ። እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች የተዘጋጁትን ኮርሶች ለመደበኛ እና የርቀት ትምህርት ፕሮግራሞች መጠቀም ይችላሉ።

e-SHE 'ኢ-ለርኒግ ከፍተኛ ትምህርትን ለማጎልበት' የአምስት ዓመት ፕሮጀክት ሲሆን በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዲጂታል ትምህርትን ተቋማዊ ለማድረግና ለማጎልበት ግብ ያደረገ ነው።

በፕሮጀክቱ የአምስት ዓመት ቆይታ 35 ሺህ መምህራን እና 800 ሺህ ተማሪዎች የዲጂታል ትምህርት አቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.3K viewsedited  13:44
Buka / Bagaimana
2024-05-12 09:50:59 " ቤቢ ሻወር " ወይስ "የአጥር ወፍ አትስማሽ?"

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የጋብቻ ጊዜዋ የተቃረበችን ሴት እና የመውለጃ ጊዜዋ የደረሰችን ሴት "Bridal Shower , Baby Shower " እየተባለ በቅርብ ወዳጆቿ ትጎበኛለች። ለሠርጓ ጊዜ እና በወለደች ወቅት የምትጠቀምባቸውን የተለያዩ ስጦታዎች ያቀርቡላታል ፡ መልካም ምኞታቸውን ገልፀው ቅርበታቸውን በተግባር ያረጋግጡላታል።

እርግጥ ነው በፈረንጅኛ ልሳን መጠራታቸው ባህላዊ መሰረታቸው ከውጭ የተኮረጀ ይምሰል እንጅ በተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ ስያሜዎች በአገራችን የሚተገበሩ ናቸው። እርግጥ ነው ከሳይንስ ዝማኔ ጋር የመጣውና ዘመን አመጣሹ የተረገዘ ልጅን የ" ፆታ ማወቂያ ሸብረብ " ወይም "Gender Reveal Party" በአገራችን ብዙ አልተለመደም።

ሌሎቹ ግን በአገራችን ይከወናሉ። እናቶች በተለይ ለእርግዝና ትልቅ ቦታ አላቸው። እኔ ባደኩበት አካባቢ የሰፈር ሴቶች ተሰብስበው የገንፎ እህል ያዘጋጁላታል። ገብሱ ተፈትጎ ፣ ተወቅጦና ተፈጭቶ የገንፎ እህል ማዘጋጀት ፣ ቅንጨ ከበቆሎ ወይ ከስንዴ ወይ ከአጃ እህል ማዘጋጀት ፣ ቆሎና ኑግ ማዘጋጀት ፣ የዳቦ እህል ማዘጋጀት በጥቅሉ ነፍሰ ጡሯ ወልዳ አራስ ቤት ስትቀመጥ ራሷ የምትመገባቸውንና ጠያቂ እንግዳ የሚቀማምሳቸውን ሁሉ ማሰናዳት የወዳጆች ስራ ነው።

ታዲያ ተዘጋጅቶ ሲያልቅ ዘመን አመጣሹ "ቤቢ ሻወር" ላይ እንደሚደረገው ልብስ፣ የጨቅላ ማጠቢያ ሳህን ወይም ዳይፐር / በኛ አካባቢ የሽንት ጨርቅ / አይሁን እንጅ ቅቤ፣ እርጎና ሌሎች ባህላዊ መጠየቂያዎችን ከየቤታቸው አምጥተው ይሰጧታል ፣ ይቀቧታል። እንዲሁም የሰሩትን ገንፎ ቅምሻ አዘጋጅተው ይመርቋታል ፡ በሰላም እንድትገላገል ይመኙላታል።

"ነፍሰጡር ሴት መውለጃዋ ሲዳረስ እና የገንፎ እህል ተፈጭቶ ወደቤት ሲገባ ሴት ጎረቤቶች፣ጓደኞችና ዘመድ አዝማድ ተጠርቶ ገንፎ ይበሉና "የአጥር ወፍ አትስማሽ" ብለው ይመርቃሉ። አጥር ላይ ያለች ወፍ ከጎረቤትም በጣም የቀረበች ስትሆን ድምፅን ቶሎ ትሰማለች።

ምጥ በመጣ ግዜ ነፍሰጡሯ ህመሙ ሳይፀናባት፣እንኳን ጩኸቷን ሌላ ሰው ይቅርና የቅርቧ የአጥር ወፍ እንኳን ሳትሰማት በሰላም ትውለድ ማለት ነው። ባጭሩ ምጧን ቀላል እንዲያደርግላት መመኘት ነው":: እና የከተማ እህቶቻችን የምን " ቤቢ ሻወር " ነው። ይልቅ "የአጥር ወፍ አትስማሽ!" በሉ። እናንተንም የአጥር ወፍ አትስማችሁ !!
#ደመቀ_ከበደ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
11.5K viewsedited  06:50
Buka / Bagaimana
2024-05-12 09:25:16
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትግራይ ክልል ተፈታኞ መርሃ ግብር

በቀድሞ ስርዓተ ትምህርት የተማሩና በ2013 እና በ2014 የትምህርት ዘመን መፈተን የነበረባቸው የትግራይ ክልል ተፈታኞ በ2016 ትምህርት ዘመን በወረቀትና በበይነ መረብ የሚፈተኑበት መርሃ ግብር

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
9.8K viewsedited  06:25
Buka / Bagaimana
2024-05-12 08:20:23
እንኳን ለእናቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ !

በምዕራቡ ዓለም ሚያዝያ ወር በገባ በሁለተኛዉ ሳምንት እሁድ የእናቶች ቀን በሚል፤ እናትን በማወደስ ለእናት ልዩ ምስጋና በማቅረብ፤ በድምቀት የማክበር፤ የማሰብ ባህልና የተለመደ ነዉ።

የእናት ቀን አከባበር መነሻዉ ከዩኤስ አሜሪካ መሆኑና፤ በአሁን ግዜ በበርካታ ሀገሮች ቀኑን የማክበር ባህል መለመዱን ዘገባዎች ያመላክታሉ።

እናት ለዘላለም ትኑር!

መልካም የእናቶች ቀን


@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
10.7K viewsedited  05:20
Buka / Bagaimana
2024-05-11 17:32:21
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መርሐ ግብር ይፋ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡ የፈተና መርሐ ግብሩ በወረቀትና በበይነ መረብ የሚሰጠውን የፈተና የሚወስዱ ከትግራይ ክልል ውጭ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ላሉ ተፈታኞች ነው ይፋ የተደረገው፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኞች እና የሚመለከታቸው አካላት ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
18.8K viewsedited  14:32
Buka / Bagaimana
2024-05-11 09:45:13
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
11.9K viewsedited  06:45
Buka / Bagaimana
2024-05-11 09:08:48 “ መምህራን እየቆዘሙ፣ ቅሬታ ተሸክመው ክፍል ውስጥ ገብተው ትውልድን ለመቅረጽ ይቸገራሉ ”  - ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር)

በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ለሚነሱ ደመወዝን መሠረት ያደረጉ ቅሬታዎች ትልቁ መንስኤ የመልካም አስተዳደር ችግር መሆኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ገለጸ። በተለይ መምህራን ላይ የሚከሰተው ችግር ከትውልድ ጋር የተያያዘ ነው። መምህራን እየቆዘሙ፣ እያዘኑ፣ ቅሬታ ተሸክመው ክፍል ውስጥ ገብተው ትውልድን ለመቅረጽ ይቸገራሉ። ችግሩ በፍጥነት መታረም አለበት።

መቼም መምህራን የመንግስት ሠራተኞች ናቸው። የወር ደመወዝ በጊዜ ማግኘት መቻል አለባቸው። ለልማት ሲባል መምህራንን ሳያሳምኑ ደመወዝ የመቁረጥ አይነት ቅሬታዎች አልፈው አልፈው ይመጣሉ። በጦርነት ምክንያት የወደሙ ትምህርት ቤቶች አሉ። በዚህም የተፈናቀሉ ተማሪዎችና መምህራን ይኖራሉ። በተቻለ መጠን ሰላም ወርዶ ወደ ቦታቸው ተመልሰው ስራቸውን እንዲሰሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እያደረግን ነው ” ብለዋል ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር)።

Credit: Tikvah

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
12.9K viewsedited  06:08
Buka / Bagaimana