Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Digital Library

Alamat saluran: @ethiopian_digital_library
Kategori: Pekerjaan
Bahasa: Bahasa Indonesia
Pelanggan: 64.54K
Deskripsi dari saluran

በዚህ ቻናል
👉ትምህርታዊ መፅሐፎችን
👉ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎችን
👉የሶሻልና የናቹራል መጽሐፎችን
👉የዩኒቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
👉የጥያቄና መልስ ወርክ ሽቶችን እና
👉ልዩ ልዩ መጽሐፎችን በነፃ ያገኛሉ!
For any comments: @ethiodlbot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


Pesan-pesan terbaru 16

2024-01-19 16:10:44
የ2016 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና (የ12ኛ መልቀቂያ ፈተና)

በአጠቃላይ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርት ሪፎርም መሠረት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት ወደ ሙሉ ትግበራ መግባቱ ይታወሣል፡፡

በዚህም መሠረት ደረጃ ትምህርት የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች ተለይተው የመማር ማስተማር ሂደቱ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በ2016 ዓም በሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችን መወሰን በማስፈለጉ በሁለቱም ዘርፎች ዕድስት፣ ስድስት የትምህርት አይነቶች እንዲሆኑ እንደሚከተለው ተወስኗል፡፡

የተፈጥሮ ሣይንስ
እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ከሚስትራ፣ ባዮሎጂ፣ ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ

የማህበራዊ ሣይንስ
እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ጂኦግራ፣ ፊታሪክ፣ ኢኮኖሚክስ፣ ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ

ከላይ በተጠቀሰው መሠረት የ2016 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ዝግጅት
1. የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ፣ ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9ኛ እስከ 11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ-ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሆኑን

2. ሰኮላስቲክ አኘቲቲውድ ቴስት ወደፊት ጥናት ተጠንቶ እስከሚለይ ድረስ በነበረው አሠራር መሠረት ውጤት ተደምሮ የሚገለጽ መሆኑን

3. የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ለወላጆች ለመምህራን እና ለትምህርት ማህበረሰቡ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወዲሁ እንዲያውቁት እንዲደረግ እናሳስባለን።

ትምህርት ሚኒስቴር

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
14.7K viewsedited  13:10
Buka / Bagaimana
2024-01-18 14:44:09
ለመንግስት እና ለግል ት/ቤቶች በሙሉ

አርብ ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም በከተራ በዓል ምክንያት መንገዶች ስለሚዘጋጉ በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በሙሉ ትምህርት የማይኖር መሆኑን ለተማሪዎችና ለወላጆች መልእክት እንዲተላለፍላቸው እያሳወቅን የመንግስት ት/ቤት የተማሪ መጋቢ እናቶች በእለቱ ምግብ እንዳያዘጋጁ ከወዲሁ እንድታሳወቁ እናሳስባለን ፡፡

የአቃቂ ቃሊቲ ት/ጽ/ቤት

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
15.2K viewsedited  11:44
Buka / Bagaimana
2024-01-18 14:15:56 ብሄራዊ መታወቂያ ያላገኘ ሰው የማህበራዊ አገልግሎት አያገኝም በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች የተሳሳቱ መሆናቸው ተገለጸ

የብሄራዊ መታወቂያን የያዘ ማንኛውም ማህበረሰብ የትኛዉንም አገልግሎት እና ማንነቱን ማረጋገጥ የሚፈልግበት አገልግሎት ላይ መጠቀም እንደሚችሉ ተነግሯል።

የብሄራዊ መታወቂያ ኮሚንኬሽን ዳይሬክተር አቶ አቤኔዘር ፈለቀ፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት  ይሄንን መታወቂያ እንደ አንድ የአገልግሎት አማራጭ አድርገው ይጠቀሙበታል ማለት  እንጂ፣ ማህበረሰቡ ብሄራዊ መታወቂያ ከሌለው ምንም አይነት አገልግሎት አያገኝም ማለት እንዳልሆነ  ተናግረዋል።

እስካሁን ባለዉ መረጃ ከሶስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን በላይ ሰው የብሄራዊ መታወቂያን ለማግኘት ምዝገባ እንዳከናወነ ታውቋል።

የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ አቤኔዘር፣ማህበረሰቡ ስለብሄራዊ መታወቂያ ትክክለኛውን መረጃ ከትክክለኛው ምንጭ ማግኘት እንዳለበትም አሳስበዋል።
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
12.9K views11:15
Buka / Bagaimana
2024-01-17 18:16:23
#Ads

For general knowledge questions and answers please join our YouTube channel!

https://www.youtube.com/@hablen/videos
13.1K views15:16
Buka / Bagaimana
2024-01-17 09:50:49 ለፍቅረኛው ፈተና ለመፈተን ሲል ሊፒስቲክ እና ሜክአፕ ተሰርቶ ወደ መፈተኛ ክፍል የገባው አፍቃሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

አንድ ህንዳዊ በፑንጃብ ዩኒቨርሲቲ በሴት ጓደኛው ስም ሊፒስቲክ፣ ሜካፕ እና የሴት ልብስ ለብሶ ፈተና ለመውሰድ ሲሞክር ተይዟል።

በፑንጃብ ፋሪድኮት አውራጃ የሚገኘው የባባ ፋሪድ የጤና ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ባለስልጣናት በቅርቡ አንድ ህንዳዊ ወጣት የሴት ጓደኛዋ ወክሎ ሁለገብ የጤና ባለሙያዎችን ፈተናን ለመፈተን ፍቅረኛውን በመምሰል እና የውሸት ሰነዶችን ሲጠቀም ተይዟል። የፋዚልካ አንግሬዝ ሲንግ በመባል የሚታወቀው ይህው ወጣት ጥር 7 ቀን በኮትካፑራ በሚገኘው የፈተና ማእከል ውስጥ  ሙሉ የሴት አልባሳት ለብሶ፣ ሜክአፕ እና ሊፕስቲክ ተቀብቶ ይገኛል።

በተጨማሪም በፍቅረኛው የሴት ስም ሰነዶችን ይዞም ነበር። የማስመሰል ሂደቱ የመፈተኛ ጣቢያ ሰራተኞቹን ሊያታልል ቢችልም መረጃ ቋቱ ውስጥ ካለው ጋር የያዘው የገፅታ ግን የባዮሜትሪክ ስካነሮችን ማታለል ባለመቻሉ በቁጥጥር ስር ውሏል። ግለሰቡ ወደ ፈተና አዳራሽ ቢገባም በማመልከቻ ቅጹ ላይ ያለው የፍቅረኛውን የፓራምጄት ካኡር ምስል ከእርሱ ፊት ጋር በመሳሪያው ስላልተመሳሰለ የዩኒቨርሲው ባለስልጣናት ይጠራጠራሉ።

ህንድ ኤክስፕረስ እንደዘገበው በባዮሜትሪክሱ መሰረት በመዝገቦቹ ውስጥ ከተቀመጠው ምስል ጋር አይዛመዱም። በዚህም አንግሬዝ ሲንግ ፍቅረኛው የሆናችውን ካውርን እንዳስመሰለ ለማወቅ ተችሏል። በፓራምጄት ካውር ስም የተሰራ የውሸት ካርድ፣ የፈተና ካርድ በፍተሻ ወቅት ተገኝቶበታል። መጀመሪያ ላይ የዩንቨርስቲው ሰራተኞች አንግሬዝን ወደ ቤቱ እንዲሄድ ሸኝተውት የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ በበርካታ ክሶች በምርመራ ላይ ይገኛል።

ያለ ፍቅረኛውው ካውር ፍቃድ በእሷ ቦታ ፈተናውን መስሎ መፈተን ስለማይችል ከሲንግ ጋር በማሴር ወንጀል ተከሷል።የ34 ዓመቷ ፓራምጄት ካውር ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ፈተና ወስዳ ማለፍ ስላልቻለች የ26 ዓመቱ ፍቅረኛዋ አንግሬዝ ፈተናውን በመውሰድ ፍቅረኛውን ለማሳለፍ ተስፋ አድርገው ነበር። ወጣቱ መጀመሪያ ላይ ከካኡር ጋር ዘመድ እንደሆኑ ለፖሊስ ተናግሮ ነበር፣ ነገር ግን ይህ ውሸት መሆኑን ፖሊስ ባደረገው ምርመራ አረጋግጧል።

አንግሬዝ እንደ ሴት መስሎ የሚታይበት ምስል በህንድ ማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል።እኤአ በ2015 ዓመት በተመሳሳይ በካዛኪስታን አንድ ሰው ለፍቅረኛው የዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ለመፈተን በማሰብ ተመሳሳዩን ድርጊት ማድረጉ ይታወሳል። #ዳጉ_ጆርናል
@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.3K viewsedited  06:50
Buka / Bagaimana
2024-01-17 09:49:42
13.0K views06:49
Buka / Bagaimana
2024-01-17 09:29:09 ዲላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች

በ2016 ዓ.ም ዲላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥር 23 እና 24/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ (ኦዳያኣ ካምፓስ) በሚገኘው ሬጂስትራር ጽ/ቤት

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ 3x4 የቅርብ ጊዜ ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ፣አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ፡፡#DillaUniversity

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.9K viewsedited  06:29
Buka / Bagaimana
2024-01-16 15:07:22
12.9K views12:07
Buka / Bagaimana
2024-01-16 09:49:20
#Update

የሪሚዲያል ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ጊዜ በቅደም ተከተል

#Today

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ: በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳቹህ ለሪሚዲያል ፕሮግራም በ2016 የትምህርት ዘመን ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 27 እና 28/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ: በ2016 ዓ.ም በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥር 15 እና 16/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ: በ2016 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥር 20 እና 21/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ጭሮ ከተማ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ካምፓስ

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ: በ2016 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥር 20 እና 21/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ ትምህርት ጥር 22/2016 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

N.B:
ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሰርትፊኬት ዋናውና ኮፒው፣ ከ9ኛ አስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣ የቅርብ ጊዜ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ብርድ ልብስ፣ አንሶላና ትራስ ጨርቅ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
13.2K viewsedited  06:49
Buka / Bagaimana
2024-01-15 17:22:25 23 Best Apps for Students to Study Efficiently

App Blocker Apps: Stay Focused, AppBlock
Best Planner Apps: myHomework Student Planner, Google Calendar
Best Task Managers: Todoist, Microsoft To Do, Any.do
Best Note-Taking Apps: OneNote, Google Keep, Evernote
Best Word Processor Apps: Google Docs, Microsoft Word
Best Dictionary Apps: Merriam-Webster Dictionary, Oxford Dictionary of English
Best Learning Apps: Khan Academy, Google Translate, Duolingo
Best Organizer Apps: Office Lens, Adobe Scan
Best Cloud Storage Apps: Google Drive, Dropbox
Best Calculator Apps: GeoGebra Graphing Calculator, RealCalc

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library
12.8K viewsedited  14:22
Buka / Bagaimana