የመምህራን ደመወዝ በመከፈሉ በወላይታ ዞን የተቋረጠው ትምህርት ተጀምሯል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን፣ ላለፉት ሁለት ወራት ያህል ታጉሎ የቆየው የመምህራን ደመወዝ በመከፈሉ የተቋረጠው የመማር ማስተማር ሒደት መቀጠሉን፣ የክልሉ የመምህራን ማኅበር አስታወቀ፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ዐማኑኤል ጳውሎስ፣ ችግሩ ተፈጥሮባቸው የነበሩት የአንድ ከተማ አስተዳደር እና የ20 ወረዳዎች ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ መመለሳቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡ ለደኅንነታቸው ስለሚሰጉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ውስጥ የሚያስተምሩ የአካባቢ ሳይንስ መምህር፣ ለሁለት ወር ያህል የታጎለባቸው ደመወዝ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በመከፈሉ ከሚያዝያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. አንሥቶ ተቋርጦ የቆየው ትምህርት መቀጠሉን በስልክ ተናግረዋል፡፡ መምህራን ወደ ሥራቸው የተመለሱት፣ የሁለት ወር ደመወዛቸው በከፊል እና ሙሉ በሙሉ በመከፈሉ መኾኑን፣ ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁት ሌላው መምህር ገልጸዋል፡፡ #VOA @Ethiopian_Digital_Library @Ethiopian_Digital_Library 15.4K viewsedited 13:46